Australian citizenship test book - Ahmaric
Australian citizenship test book - Ahmaric Australian citizenship test book - Ahmaric
ክፍል 4 አውስትራሊያ በዛሬ ቀን በዓለም ሰፊ ከሆኑት አገሮች አውስትራሊያ አንዷ ናት። በዓለም ውስጥ ስድስተኛዋ ትልቅ አገር ናት። 38 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
- Page 2 and 3: የዛሬቱ አውስትራሊያ
- Page 4 and 5: የፑርኑሉሉ ብሄራዊ መ
- Page 6 and 7: የአውስትራሊያ ማንነ
- Page 8 and 9: ቲያትርና ፊልም የአው
- Page 10 and 11: ታላቅ የሆነችው አገራ
- Page 12 and 13: ኢድት ኮዋን/Edith Cowan (18
- Page 14 and 15: የአውስትራሊያ ህዝብ
- Page 16 and 17: የአውስትራሊያ ተደና
- Page 18 and 19: የአውስትራሊያ ታሪካ
- Page 20 and 21: አዲስ እድሎች በአውስ
- Page 22 and 23: ሰፋሪዎችና አቅኝዎች
- Page 24 and 25: ለምርጫ መብት/Suffrage ‘
- Page 26 and 27: ይሁን እንጂ አውሮፓ
- Page 28 and 29: ታላቅ የኢኮኖሚ ውድቀ
- Page 30 and 31: ሰር ኢድዋርድ ‘ዊርይ
- Page 32 and 33: ስለአገር ተወላጁ አያ
- Page 34 and 35: የአገሬው ተወላጅ ህዝ
- Page 36 and 37: ለአገር ተወላጅ ስእላ
- Page 38 and 39: መንግሥታዊ ያልሆኑ ድ
- Page 40 and 41: p40 - የማኳሪ ደሴት/Macqua
- Page 42 and 43: ማስታወሻ
- Page 44: ማስታወሻ
ክፍል 4

አውስትራሊያ በዛሬ ቀን

በዓለም ሰፊ ከሆኑት አገሮች አውስትራሊያ አንዷ ናት።

በዓለም ውስጥ ስድስተኛዋ ትልቅ አገር ናት።

38

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
የዛሬቱ አውስትራሊያ

በነዚህ ገጾች ላይ ስለዚህ አገር ልዩ የሚያደርገን ይማራሉ። ስለ ባህላችን፣ ስለ መስራቾቻችን፣ ያለን ብሄራዊ ማንነታችን በበለጠ ይማራሉ።

ዛሬ በዓለም ውስጥ አውስትራሊያ አስደናቂ የሥራና የንግድ ባለቤት እንደሆነችና ዓለም አቀፋዊ የሆኑ ዜጎች የሚከበርባት አገር ናት።

በአገራችን እድገትና ተሀድሶ ላይ የአዲስ መጤዎች ለሚያበረክቱት ዋጋ እንሰጣለን።

መሬት

አውስትራሊያ በብዙ መልኩ የተለየች ናት። ከዓለም ሰባት አህጉሮች ውስጥ በአንድ አገር የተጠቃለለች አውስትራሊያ ብቻ ናት። በዓለም

ውስጥ አነስተኛ የህዝብ ብዛት ያለን እኛ ስንሆን በአንድ ኪሎ ሜትር ስኮር ክልል ውስጥ ሁለት ሰዎች ብቻ ይኖራል።

በዓለም ውስጥ ጥንታዊ ከሆኑት የመሬት ስፋቶች ውስጥ አውስትራሊያ አንዷ ናት። ይህ በዓለም ትልቅ ከሆኑት አገሮች አውስትራሊያ

ስድስተኛ ነች። እንዲሁም በጣም ደረቅ የሆነ መሬቶች ስላሏት ስለዚህ በአብዛኛው የአውስትራሊያ ክፍል ያለው ውሀ በጣም ጠቃሚ ድንቅ

የሆነ ንብረት ነው።

አብዛኛው መሬት ጥሩ አፈር እንደሌለውና ከመቶ 6 እጅ መሬት ብቻ ነው ለእርሻ ተስማሚነት ያለው። በውሀ የተከበበው ደረቅ መሬት

‘ከአገር የራቀ’ ተብሎ ይጠራል። በነዚህ በጣም የራቁና የማይመች አካባቢ ለሚኖሩ ሰዎች ከፍተኛ ክብረት ይሰጣቸዋል። ለብዙዎቹ

የአውስትራሊያ ቤተሰብ ባህሎች ኣካል እንደሆነ ነው።

አውስትርሊያ ትልቅ አገር በመሆኗ በተለያዩ ክፍለ ቦታዎች የአየር ሁኔታው ይለያያል። በሰሜን አውስትራሊያ የትሮፒካል ክልሎችና በመሀል

አገር ደግሞ ምድረ በዳ በርሀ ናቸው።

ወደ ደቡብ አገር ሲሄዱ ያለው አየር በክረምት ቀዝቃዛና በተራሮች ላይ በረዶ ሲኖር በበጋ ወራት ደግሞ የሙቀት ወለፈን ይሆናል።

ከስድስቱ የመስተዳድር ግዛቶች እና ከሁለት በውሀ ያልተከበበ ተሪቶሪስ በተጨማሪ የአውስትራሊያ መንግሥት የሚያስተዳድረው እንደ

ተሪቶሪስ፣ አሽሞር/Ashmore እና ካርተር አይላንድስ/Cartier Islands፣ ክሪስማስ አይላንድ/Christmas Island፣ ዘኮኮስ (ኪሊንግ)

አይላንድ/the Cocos (Keeling) Islands፣ ጀርቪስ ባይ ተሪቲርይ/Jervis Bay Territory፣ ዘኮራል ሲ አይላንድ/the Coral Sea

Islands፣ ሂርድ አይላንድ/Heard Island እና ኣብ ኣውስትራሊያ ኣንታርቲካ ተሪቶርይ ውሽጢ ማክዶናልድ አይላንድስን/McDonald

Islands፣ ኖርፎልክ አይላንድ/Norfolk Island ናቸው።

ክፍል 4 – አውስትራሊያ በዛሬ ቀን 39
የዓለም ቅርስ ቦታዎች

የአህጉራችን ከመቶ 11 እጅ በላይ ለአገሬው ተወላጅ መሬት፣ ለተቀመጠ ስፍራ ወይም ለብሄራዊ መናፈሻ የሆኑ ቦታዎች፣ በዓለም አቀፍ

ደረጃ ጥበቃና ቁጥጥር መሰረት እንክብካቤ ይደረጋል። በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንሳዊና ባህላዊ የሆነ ድርጅት (UNESCO)

ላይ ለዓለም ቅርሶች የሚሆኑ አስራ ሰባት የአውስትራሊያ ቦታዎች ተመዝግበዋል።

የአውስትራሊያ ጡት አትቢ ቅሬተ አካል/Australian

Fossil Mammal ያሉበት፣ ቦታዎች በሳውዝ

አውስትራሊያ እና በኩዊንስላንድ

የጎንድዋና ተፈጥሮ ጫካ/Gondwana Rainforests፣

በኒው ሳውዝ ዌልስ እና በኩዊንስላንድ

የካካዱ/Kakadu ብሄራዊ መናፈሻ ፓርክ በኖርዘርን

ተሪቶርይ

የፍራሰር ደሴት/Fraser Island ጠረፍ ወጣ ያለ፣

በሳውዘርን ኩዊንስላንድ

የታላቁና ዛጎላማው የባህር ጠረፍ/Great Barrier

Reef፣ በኩዊንስላንድ

የሎርድ ሆው ደሴት/Lord Howe Island ጠረፍ

ወታያለ፣ በኒው ሳውዝ ዌልስ

የትክቁ ሰማያዊ ተራሮች/Greater Blue

Mountains፣ በምእራብ ስይድነይ

የሂራድ ደሴት/Heard Island እና የማክዶናልድ

ደሴቶች/McDonald Islands፣ በአውስትራሊያ

አንታርክቲክ ተሪቶርይ

የማኳሪይ ደሴት/Macquarie Island ወደ ሳውዝ

ታስማኒያ

40

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
የፑርኑሉሉ ብሄራዊ መናፈሻ ፓርክ/Purnululu

National Park በዌስተርን አውስትራሊያ

የስይድነይ ኦፐራ ህውስ/Sydney Opera House

የዝንናማው በርሀማ ክፍል/Wet Tropics

በኩዊንስላንድ

የሮያል ኤግዚቪሽን ህንዳ/Royal Exhibition

Building እና የካልቶን አትክልት ቦታ/Carlton

Gardens በመልበርን

የ Tasmanian Wilderness

የዊላንድራ ሀይቆች/Willandra Lakes በኒው ሳውዝ

ዌልስ

በአውስትራሊያ ላይ ያለዎትን ተመክሮ

ለማስፋፋት እነዚህንና ሌሎች

ድንቅ የሆኑ ቦታዎችን እንዲያዩ

እናበረታታለን። በምድረ በዳ በርሀ

ወይም ባህር ዳርቻ፣ በተራሮች ወይም

በተፈጥሮ ጫካዎች ላይ በእግር መጓዝ

ይችላሉ። ለነዚህ ሰፊና ወኔ ቀስቃሽ

በሆኑ ቦታዎች ለማየት የሚወስዱት

እያንዳንዱ ደረጃ ወሳኝ ይሆናል።

የሽርክ ሰላጤ/Shark Bay በዌስተርን አውስትራሊያ

የዩሉሩ-ካታ ትጁታ/Uluru-Kata Tjuta ብሄራዊ

መናፈሻ ፓርክ፣ በኖርዘርን ተሪቶርይ

ክፍል 4 – አውስትራሊያ በዛሬ ቀን 41
ስፊ አገር

የአውስትራሊያ ሰፊ መሆን ለወረራና ለፈጠራ ግኝትን እድል

እንደጨመረ ነው።

ቀደም ባሉ ቀናት ከከተማ ራቅ ባለ ቦታ የሚኖሩ ሰዎች በአቅራቢያ

ያለን ሀኪም ለማየት ብዙ ቀናት ይጓዛሉ። በጫካ ውስጥ ያሉ ብዙ

ህጻናት በቀን ት/ቤት ለመሄድ በጣም ይርቃቸዋል።

ከከተማ እርቆ ያለ ቤተሰብ ገለልተኛ በመሆኑ ይከብዳል። ትላልቅ

የከብቶች ማርቢያ ጣቢያዎች በሺዎች የሚቆጠር ስኮር ኪሎ

ሜትር ስፋት ሊኖራቸው ይችላል። በዚህ ቦታ የሚኖሩ ሴቶችና

ህጻናት በወራት የሚቆጠር ጊዜ ሌላ ሰው ማየትና ምግነት

አይችሉምስ። የተሌፎን ስልክ ባለመኖሩ ሰዎች በጣም ገለልተኛ

እንደሚሰማቸውና ለአደጋ የተጋለጡ ነበር።

ታላቁ የአውስትራሊያ ህዝብ በጋራ በመሆን ግኝቶችን በመፍጠር

እነዚህ ችግሮች ሊፈቱ ችለዋል።

የፐዳል ራዲዮ

Alfred Traegar የተባሉት ከአደላይድ የመጀመሪያ በእግር

የሚሰራ የመጀመሪያውን ራዲዮ በ1929 ዓ.ም አወጡ።

ተጠቃሚዎች በሁለት ዘዴ የሚሰራ ራዲዮን በእግራቸው ፐዳሉን

በመጫን ይሆናል። ከቤት ውስጥ ለሚውሉ ብቸኞች፣ ለገጠር

መልእክተኛ ጣቢያዎችና ለአቦርጂናል ማህበረሰባት በዚህ ግኝት

ውጤት ይጠቀማሉ። በአሁኑ ጊዜ ገለልተኛ የሁኑ ሴቶች በአየር

መተላለፊያው አማካንነት ጓደኝነትን መፍጠር ይችላሉ።

የአየር መተላለፊያ ትምህርት ቤት

እስከ 1950’ዎቹ ድረስ በገጠር የሚኖሩ ህጻናት ወደ አዳሪ ት/ቤት

ስኢሄዱ ወይም ትምህርታቸውን በኢሜል በኩል ያጠናቅቃሉ።

በሳውዝ አውስትራሊያ ውስጥ Adelaide Miethke የተባሉት፤

የሮያል በረራ ዶክተር አገልግሎት ምክትል ፕሬዚደንት ይህ የበረራ

ዶክተር ራዲዮ አገልግሎት ለህጻናት በቤታቸው ከአስተማሪዎቻቸው

ጋር እንዲነጋገሩ ይረዳል። በአሊስ ስፕሪንግስ/Alice Springs

እነዚህ የራዲዮ አየር ትምህርት የጀመሩት በ1948 ዓ.ም ነው።

በራዲዮ የሚሰጠው መደበኛ ትምህርት ቤት የተቋቋመው ከጥቂት

ዓመታት በኋላ ነው። በአውስትራሊያ የአየር ትምህርት ቤት

አቅርቦት ለብዙ አገሮች የራሳቸውን ፕሮግራም እንዲያወጡ

እረድቷቸዋል።

በአሁን ጊዜ አሮጌው የፐዳል ራዲዮ በዘመናዊ የከፍተኛ

ፍረኩወንሲ ያለው የተቀየረ ሲሆን ነገር ግን በአውስትራሊያ ገጠር

ውስጥ ለሚገኙ የማህበረሰባት አባላት ጥቅም ሲባል በአውስትራሊያ

ሮያል በራሪ ዶክተር አገልግሎትና በአየር መተላለፊያ ት/ቤት

የሚቀርበው አገልግሎት አያቋርጥም።

የፔዳል ራዲዮ ለሁለት የአውስትራሊያ ተቋማት እንዲመሰረቱ

ሲረዳ፣ እነሱም የሮያል ብራሪ ዶክተር አገልግሎትና በአየር

መተላለፊያ ትምህርት ቤቶች ናቸው።

የሮያል በራሪ ዶክተር አገልግሎት

Reverend John Flynn የተባሉት ሰው በገጠር ማህበረሰብ

ካሉ ሰዎች ጋር በመኖር ሰርተዋል። በገጠር አካባቢ ላሉ በሽተኖች

የሚረዳ ሀኪም በተቻለ ፍጥነት በአየር ለማምጣት ዓላማቸው ነበር።

ከመንግሥት፣ Qantas/ኳንታስ አየር መንገድና እርዳታ ለጋሽ

ከሆኑ ድርጅቶች እርዳታ እንዳገኙ ነው። የሮያል በራሪ ዶክተር

አገልግሎት የተጀመረው በ1928 ዓ.ም ሲሆን ነገር ግን አሁንም

አገልግሎት እንዲያገኙ ለመደወል በጣም እሩቅ ቦታ የሚኖሩ ሰዎች

እንዳሉ ነው። በጣም ሩቅ በሆነ ጣቢያ ያሉ ሰዎች በአስቸኳይ

ሀኪም ስለመጥራት በዚህ የፐዳል ራዲዮ ማረጋገጥ ይቻላል።

በኒው ሳውዝ ዌልስ ውስጥ ህጻናት በአየር መተላለፊያ ት/ቤት በኩል ይማራሉ

42

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
የአውስትራሊያ ማንነት መለያ

የአውስትራሊያ ማንነት የተቀረጸው ልዩ በሆነው ቅርሳችን፣ ባህላችንና በህዝባችን ጠንካራ መንፈስ ይሆናል።

ስፖርትና መዝናኛ

አብዛኛው አውስትራሊያዊ ስፖርት እንደሚወድና ብዙዎቹ በዓለም

አቀፍ ደረጃ አስደናቂ ውጤት እንዳገኙ ነው።

ዝነኛ የሆነ የብሄራዊ ‘ጥሩ ስፖርቶች’ በመኖራችን ያኮራናል።

የአውስትራሊያ ስፖርት ወንዶችና ሴቶች እንደ አምባሳደር መጠን

ለሚያበረክቱት ከባድ ሥራ፣ ጥሩ ጨዋታና የቡድን ሥራ ምስጋና

ይድረሳቸው።

በታሪካችን ውስጥ ስፖርት ለአውስትራሊያ ህዝብ መንፈስ

በማጠናከር ወደ አንድነት ያመጣናል። ሰፈራ ሲጀመር ቀደም ብሎ

ከነበረ ከባድ አኗኗር ሁኔታ ለመላቀቅ ስፖርት ይረዳል። በጦር

ውጊያ መስክ ላይ ከሚፈጠር ጭንቀት ለመላቀቅ ሲባል በጦርነት

ጊዜ ቢሆንም የስፖርት ውድድር በአውስትራሊያ መከላከያ ሀይል

አባላት ይቀናጃል።

እንዲሁም ስፖርት ለተጫዋቾችና ለተመልካቾች ስሜት የጋራ

መድረክ በመፍጠር ለአውስትራሊያ ሕብረተሰብ ጠቃሚ የሆነ ክፍል

ነው።

በቡድን በተደራጀ ስፖርት ላይ ብዙ አውስትራሊያን ይሳተፋሉ።

በአብዛኛው ከታወቁት ጨዋታዎች ውስጥ የክሪኬት፣ ቅርጫት ኳስ፣

የመረብ ኳስ፣ የገና ጨዋታ እና የእግር ኳስ ናቸው።

ኢያን ቶርፐ/Ian Thorpe የተባለው አምስት ጊዜ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳይ ተሸላሚ

መዋኘት፣ የቴኒስ፣ የሩጫ፣ ጎልፍና የብስክሌታ ከታወቁት የመዝናኛ

እንቅስቃሴዎች ናቸው። እንዲሁም በአለም አቀፍ ውድድሮች ውስጥ

ለየት ያሉ የአውስትራሊያ የስፖርት ውድድሮች አሉ። ሌሎቹ

የአካል እንቅስቃሴዎች ደግሞ በጫካ የእግር ጉዞ፣ በማእበል

የመሰለ ላይ መንሳፈፍና በበረዶ ላይ መንሸራተት ያካተተ ይሆናል።

በተጨማሪም አውስትራሊያኖች የእግር ኳስ ጨዋታን፣ ራግብይ/

rugby ቡድን፣ ራግብይ/rugby ማሕበርና የአውስትራሊያ እግር

ኳስን መጫወትና መከታተል ይወዳሉ። ‘የአውሲ ደንቦች/Aussie

Rules’ በአውስትራሊያ ልዩ የሆነ ጨዋታ ነው።

አውስትራሊያ በክሪኬት ጨዋታ ባላት ዓለም አቀፋዊ ልዩ የሆነ

ጥሩ ውጤት ያኮራታል። ከ19’ኛው ምእተ ዓመት መጨረሻ አንስቶ

የአውስትራሊያና የእንግሊዝ ክሪኬት ቡድኖች ከባድ የመፎካከር

ስሜት ነበራቸው።

የመልበርን ዋንጫ ውድድር/Melbourne Cup፣ ‘መንግሥትን

ማቆም የሚችል ውድድር’፤ ይህ በዓለም ላይ ሃብታምና

በጣም አስቸጋሪ የሆነ ፈረስ ውድድር ይሆናል። በ1861 ዓ.ም

የመጀመሪያው መልበርን ዋንጫ ተካሂዷል። ከ1877 ዓ.ም ጀምሮ

በቪክቶሪያ ውስጥ ህዳር/November ወር በመጀመሪያው ማክሰኞ

ላይ የመልበርን ዋንጫ ውድድር የሚከበርበት ህዝባዊ የእረፍት

ቀን ይሆናል።

በአውስትራሊያ የሴቶች ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን አባል

ክፍል 4 – አውስትራሊያ በዛሬ ቀን 43
Sir Donald Bradman (1908 – 2001)

Sir Donald Bradman ሁልጊዜ በክሪኬት አገልጋይነት ታላቅና በአውስትራሊያ ስፖርት ዝናን ያተረፉ

ናቸው።

በኒው ሳውዝ ዌልስ ውስጥ ቦውራል/Bowral ያደገው ዶናልድ ብራግማን/Donald Bradman

በአውስትራሊያ ቡድን የክሪኬት ጨዋታ በ1928 ዓ.ም እንደጀመረ ነው።

እሱም በፍጥነት እግር በመትከሉ የሚያስደንቅ ነበር። በ1930 ዓ.ም ወደ እንግሊዝ አገር የመጀመሪያ

ጉዞ ላይ ሁሉንም የውድድር ሪኮርድ እንዳሸነፉ ነው። እድሜያቸው 21 ዓመት ሲሆነው የአውስትራሊያ

ታዋቂ ሰው ሆኑ።

በ1948 ዓ.ም የብራድማን/Bradman’s መጨረሻ ጉዞ ላይ ቡድናቸው ከእንግሊዝ ጋር በተደረገው

ግጥሚያ አንድም ጨዋታ ሳይሸነፉ ስለነበሩ ቡድናቸው ‘የማይታይ ረቂቅ/The Invincible’ ተብሎ

ይጠራል።

Sir Donald Bradman, የሚታወቁት በ ‘The Don’ ሲሆን በዓለም እጅግ የታወቀ አገልጋይ ነበሩ። የሚያሸንፉትም በአማካኝ ከመቶ

99.94 እጅ ነበር።

ስነ ጥበባት

አውስትራሊያ ስሜት ቀስቃሽ የሆነ ስነ ጥበባት ትርኢት ሲሆን

ይህም በባለአገሩ የብሄራዊ ባህላዊ ልምዶችን እና ከመጤ/ስደተኛ

የተውጣጣ ባህሎችን ያካተተ ነው። በአውስትራሊያ የሚታዩና

በመድረክ ላይ የሚቀርቡ ስነ ጥበባት በሞላ ማለት ፊልም፣ ስነ

ጥበብ፣ ቲያትር፣ ሙዚቃና ዳንስ፣ በውጭ አገርና በዚህ ያለ የስእል

አድንቆትን ያካተተ ይሆናል።

ስነ ጽሁፍ

አውስትርሊያ በባህል ልምድ ላይ ጠለቅ ያለ የስነ ጽሁፍ እንዳላትና

ይህም ስለ የአውስትራሊያ ተወላጆችና ከዚያም በ18ኛው ምእተ

ዓመት መጨረሻ ላይ የወንጀለኞች አገባብ በተመለከተ አፈ ታሪክ

ይሆናል።

ቀደም ሲል የነበረው የአውስትራሊያ ጽሁፍ ብዙውን ስለ ጫካ

ኑሮና ከባድ ስለሆነ የዚህ አካባቢ የኑሮ ችግርን በተመለከተ ነው።

እንደ ሀንርይ ላውሶን/Henry Lawson እና ሚለስ ፍራንክሊን/

Miles Franklin ያሉ ጸሀፊዎች ስለ ጫካና የአውስትራሊያዊ

የኑሮ ዘዴ ግጥሞችንና ታሪኮችን ጽፈዋል።

በአውስትራሊያ የኖበል ባለቤት የሆኑት ፓትሪክ ዋይት/

Patrick White፣ በ1973 ዓ.ም የጽሁፍ ኖብል ሽልማት አገኙ።

በአውስትራሊያ የታወቁ ሌሎች ዘመናዊ የኖብል ባለቤትነት

የሚካተቱት Peter Carey, Colleen McCullough እና Tim

Winton ናቸው።

Judith Wright (1915 – 2000)

ጁዲት/Judith Wright

የተባሉት ስለ አቦርጂናል

መብቶች መከበር በሚደረግ

ዘመቻ ላይ የታወቆ ባለቅኔ

ነበሩ።

በአውስትራሊያ ከታወቁት

ባለቅኔዎች ውስጥ የእሳቸው

ኣንዱ ነው። ለአውስትራሊያ

የነበራቸውን ፍቅር

በቅኔ ግጥማቸው ውስጥ

ተገልጿል። ብዙ ሽልማቶችን

እንዳገኙ ሲሆን ስለ ጽሁፋቸው የአውደ ጥበብ ጽሁፍ ብሪታኒካ/

Encyclopaedia Britannica Prize ሽልማትን እና ለግጥም

ቅኔው ደግማ የንግሥት ወርቅ ሜዳል/Queen’s Gold Medal

ያካትታል። እሳቸው የአውስትራሊያ ተቆጣጣሪ ኮሚቴ እና

የአቦሪጂናል ውል ስምምነት ኮሚቴ ውስጥ አባል ነበሩ።

ጁዲት ራይት/Judith Wright ስለነበራቸው የግጥም ችሎታ፣

የአውስትራሊያን ስነ ጽሁፍና ማሕበራዊ አካባቢን በማሻሻላቸው

ይታወሳሉ።

44

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
ቲያትርና ፊልም

የአውስትራሊያ ጨዋታዎች፣ ፊልሞችና የፊልም ተዋናያን እዚህም

ሆነ በውጭ አገር ተወዳጅና ተቀባይነት አላቸው። የአውስትራሊያ

ተዋናዮች ማለት እንደ Cate Blanchett እና Geoffrey Rush

ያሉት እንዲሁም የፊልም ተዋናዮች እንደ ፐተር ዌር/Peter

Weir በፊልም ሥራ ስላበረከቱት ጥሩ ተግባር ብዙ ዓለም አቀፋዊ

የሆነ ሽልማቶችን አግንተዋል።

ስነ ጥበብ

የተወላጁን ምስል ቅርጽ መሳልና የ19ኛው ምእተ ዓመት የጫካ

ሁኔታ ትእይንት ሰአሊዎች እንደ Tom Roberts, Frederick

McCubbin እና Arthur Streeton በጣም ተቀባይነት ያላቸ

የአውስትራሊያ ሥራ ውጤቶች ይሆናሉ። በ20ኛው ምእተ ዓመት

አጋማሽ ላይ ሩሰል ድርይስዳል/Russell Drysdale እና ሲድነይ

ኖላን/Sidney Nolan በተባሉት ተዋናዮች የገጠሩን አስቸጋሪነት

በደማቅ ቀለም ይገልጻል። በቅርቡ ጊዜ ብረት ዋይትለይ/Brett

Whiteley ልዩና ግልጽ የግጥም ዘይቤ በዓለም አቀፍ ከፍተኛ

አድናቆትን አግንቷል።

ሙዚቃና ዳንስ

አውስትራሊያ ምርጥ የሆኑ የሙዚቃ አይነት ያቀፈና በክላሲካል

ሙዚቃ፣ በካንትሪና ሮክ ሙዚቃ ላይ አስተዋጽኦ ስለተደረግ

በዓለም አቀፍ ተቀባይነት አግንቷል። ወዲያውኑ ተቀባይነት ያገኘው

የአውስትራሊያ ድምጽ ዲድገሪዶ/didgeridoo ሲባል ይህም ጥንት

የአውስትራሊያ ህዝብ መጫወቻ መሳሪያ ነው።

የአውስትራሊያ ዳንስ እያማረ የመጣው በታላቅ ዳንሰኞቿ ጥረት

እና ኮረግራፈርስ/choreographers እንደ Sir Robert

Helpmann, Meryl Tankard እና Stephen Page ባሉት

እንደተሻሻለ ነው።

ሳይንሳዊ ግኝቶችና ፈጠራዎች

አውስትራሊያ ውስጥ በመዳህኒት፣ በተክኖሎጂ፣ በእርሻ፣ በማእድ

አወጣጥና በፋብሪካ ውጤት ስራ ላይ ስለሳይንሳዊ ግኝት ፈጠራና

መሻሻል በተመልተ ጠንካራ ሪኮርድ እንድለ ነው።

በሳይንሳዊና በሜዲካል ፈጠራዎች ላይ አስር አውስትራሊያኖች

ለኖብል ሽልማት አግንተዋል።

በተጨማሪም በሳይንሳዊ ጥሩ ውጤት ላስገኙት የአውስትራሊያን

የዓመቱ ሽልማቶች ያገኛሉ። በ2005 ዓ.ም ሽልማቱ ለፕሮፈሶር

ፊዮና ውድ/Professor Fiona Wood እንደተሰጠና ይህም

ለተቃጠሉ ሰዎች ህክምና በቆዳ ላይ የሚረጭ ስላወጡ ነው።

በ2006 ዓ.ም ሽልማቱ ለፕሮፌሰር ኢያን ፍራዘር/Ian Frazer

ለማህጸን ነቀርሳ መከላከያ የሚሆን ክትባት ስላወጡ ነው። በ2007

ዓ.ም ሽልማት ላይ ደግሞ የአካባቢ ሳይንሳዊ አመራር ላይ ለሆኑት

ፕሮፈሶር ቲም ፍላነርይ/Tim Flannery ሽልማቱን እንዳገኙ ነው።

ፕሮፈሶር ውድ/Professor Wood እና ፕሮፈሶር ፍራዘር/

Professor Frazer ሁለቱም ከብሪቴን ወደ አውስትራሊያ

የመጡ/የተሰደዱ ናቸው። የፕሮፈሶር ፍራዘር/Professor Frazer

ረዳት ተፈላሳፊ የነበሩት ድ/ር ጂያን ዝሁ Dr Jian Zhou

ቀጣዩ ትሸላሚ ሲሆኑ እሳቸውም ከቻይና የተሰደዱና ከዚያም

የአውስትራሊያ ዜጋ ሆነዋል።

ከዌስተርን አውስትራሊያ የኦከስትራ ሙዚቃ ሲሞፎኒ አማካሪና በአሁኑ ጊዜ ዜግነት

ያላቸው ቭላዲሚር ቨርቢትስክይ/Vladimir Verbitsky ናቸው፡

ፕሮፈሶር ፍረድ ሆሎውስ/Professor

Fred Hollows (1929 – 1993)

ፕሮፈሶር ፍረድ ሆሎውስ/

Fred Hollows በጣም

ጠንካራ የሆኑ የአይን ህክምና

ባለሙያ/ophthalmologist

(የአይን ሀኪም) ሲሆኑ

በአውስትራሊያ ውስጥና በታዳጊ

አገሮች ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ

በላይ የታወሩ ሰዎችን እንደገና

እንዲያዩ እረድተዋል።

ፍረድ ሆሎውስ/Fred

Hollows በኒው ዚላንድ ውስጥ

ተወለዱ። በ1965 ዓ.ም ወደ

አውስትራሊያ እንደሄዱና ከዚያም በስይድነይ ሆስፒታል የዓይን

ህክምና መምሪያ ሀላፊ ሆኑ።

በሰዎች መካከል እኩልነት ላይ ከፍተኛ እምነት እንደነበራቸውና

የመጀመሪያውን የአቦርጂናልን ህክምና መስጫ አገልግሎት

እንዲመሰረት የረዱ ሰው ናቸው። በአሁኑ ጊዜ በአውስትራሊያ

ውስጥ 60 የአብርጂናል ሜዲካል አገልግሎት መስጫዎች ይገኛሉ።

ፍረድ ሆሎውስ/Fred Hollows በታዳጊ አገሮች የዓይን ጤና

ጥበቃ ፕሮግራሞችን ለማቀናጀት እርዳታ ሲሉ በ1980 ዓ.ም

በሞላው ዓለም ውስጥ ተዘዋወሩ። ሚያዚያ/April 1989 ዓ.ም

የአውስትራሊያ ዜጋ ሆኑ።

የፕሮፈሶር ሆሎውስ ጥሩ ሥራ በሚስታቸው፣ ጋቢ/Gabi, እና

በፍረድ ሆሎውስ ፋውንዴሽን በኩል እንደቀጠለ ነው Fred

Hollows Foundation።

ክፍል 4 – አውስትራሊያ በዛሬ ቀን 45
በአውስትራሊያ የዓመቱ ተሸላሚዎች

ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ በአውስትራሊያ ስኬታማ ሥራ አመራር ላይ አስተዋጽኦ ላደረጉ በአውስትራሊያ የዓመቱ ተሸላሚ ክብረ በዓል

ይደረጋል። ማንኛውም ሰው በኑሮ ሁኔታ ላይ ለሽልማት የሚበቃ አውስትራሊያዊን በእጩነት ማቅረብ ይችላል። አግሪቷን በተለየ ችሎታ

ሥራ ላገለገሉ ሰዎች፤ በአውስትራሊያ የዓመቱ ተሸላሚ ይሆናሉ።

2009 Professor Michael Dodson AM

የተወላጁ መሪ

2008 Lee Kernaghan OAM

ዘማሪ፣ ሙዚቀኛና ‘በባርኔጣ ዙሪያ ማለፍ/Pass the

Hat Around’ ለሚለው ጉዞ መሥራች

2007 Professor Tim Flannery

ሳይንቲስት፣ ደራሲና ለተፈጥሮ ሀብት ተቆርቋሪ

2006 Professor Ian Frazer

በህክምና የበሽታ መከላከያ ባለሙያ

2005 Professor Fiona Wood AM

የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና የቃጠሎ ህክምና ልዩ ባለሙያ

2004 Steve Waugh

የክሪኬት ምርመራs/Test Cricket አዛዥ እና

ሰብዓዊነት አድራጊ

2003 Professor Fiona Stanley AC

የህጻንና የተላላፊ በሽታ ህክምና ባለሙያ

2002 Patrick Rafter

የ US Open Tennis Champion እና ‘Cherish

the Children Foundation’ መሥራች

2001 Lt General Peter Cosgrove AC MC

የአውስትራሊያ ጦር ሀይል አዛዥ 2000-2002 ዓ.ም

2000 Sir Gustav Nossal AC CBE FAA FRS

የባዮሎጂ ተመራማሪ

1999 Mark Taylor

የተስት ክሪከት/Test Cricket አዛዥ

1998 Cathy Freeman

የዓለምና የኦልይምፒክ አትሌቲክስ አሸናፊ እና የአገሬው

ተወላጅ አምባሳደር

1997 Professor Peter Doherty

በህክምና ከፍተኛ ማእረግ ኖብል የተከበረ

1996 Doctor John Yu AM

ሀኪም/Paediatrician

1995 Arthur Boyd AC OBE

አርቲስት/Artist

1994 Ian Kiernan OAM

‘ጥራት በአውስትራሊያ/Clean Up Australia’

አዝማች

1992 Mandawuy Yunupingu

የአገሬው ተወላጅ መሪ

1991 Archbishop Peter Hollingworth AO OBE

የማህበራዊ ፍትህ ጠበቃ

1990 Professor Fred Hollows AC

የዓይን ህክምና ተመራማሪ/Ophthalmologist

1989 Allan Border AO

የክሪከት ካፕቴን/Test Cricket Captain

1988 Kay Cottee AO

በሴት የብቸኛ ጀልባ ቀዘፋ ላይ ከፍተኛ ውጤት ያስገኙ

1987 John Farnham

ዘማሪና ሙዚቀኛ

1986 Dick Smith

በበጎ አድራጎት ፍሳሚነት የታወቁ ዝነኛ

1985 Paul Hogan AM

ተዋናይ/Actor

1984 Lowitja O’Donoghue CBE AM

የአገሬው ተወላጅ መሪ

1983 Robert de Castella MBE

የዓለም ማራቶን ሩጫ ውድድር አሸናፊ

1982 Sir Edward Williams KCMG KBE

የሮያል አውስትራሊይ ኮሚሽነር

ስለ መድሃኒት ጥያቄ ተግባር ማስፈጸም

1981 Sir John Crawford AC CBE

ከጦርነት በኋላ የአውስትራሊያ አርክተክት/Architect

ባለሙያ

1980 Manning Clark AC

የታሪክ ጸሐፊ

46

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
ታላቅ የሆነችው አገራችን በታሪክ ጸሐፊዎች የተገኘን ውጤት ባለማቋረጥ ለወደፊት በበለጠ ምን ማድረግ እንደምንችል ለማሰብ ይረዳናል።

በአሁን ጊዜ ሽልማት የሚካተቱት በአውስትራሊያ የዓመቱ ወጣት፣ በአውስትራሊያ የዓመቱ አንጋፋ ሹም እና በአውስትራሊያ የአካባቢ ጀግና

ተሸላሚ ናቸው።

1979* Senator Neville Bonner AO

የመጀመሪያ አቦርጅናል ህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል

1979* Harry Butler CBE

የተፈትሮ ሀብት ቁጠባ ባለሙያ/Conservationist and

Naturalist

1978* Alan Bond

ለንግድ ድርጅት ሀላፊ/Entrepreneur

1978* Galarrwuy Yunupingu AM

የአገሬው ተወላጅ መሪ

1977* Sir Murray Tyrrell KCVO CBE

ለጠቅላይ ገዥው የጥበቃ ቢሮ

1977* Dame Raigh Roe DBE

ለገጠር ሴቶች ማህበር መሪ

1976 Sir Edward ‘Weary’ Dunlop AC CMG OBE

ለጦር ሰራዊት ቀዶ ጥገና ሀኪም

1975* Sir John Cornforth AC CBE

በከሚስትሪ የከፍተኛ ማእረግ ኖብል የተከበረ

1975* Major General Alan Stretton AO CBE

ከCyclone Tracy በኋላ በዳርዊን ችግርን ለማስወገድ

ሥራ ኮማንደር

1974 Sir Bernard Heinze AC

የሙዚቃ መሪና ሙዚቀኛ

1973 Patrick White

በስነ-ጽሁፍ የከፍተኛ ማእረግ ኖብል የተከበረ

1972 Shane Gould MBE

በኦሎምፒክ የዋና ውድድር አሸናፊ

1971 Evonne Goolagong Cawley AO MBE

በWimbledon እና French ክፍት የሜድ ተኒስ

ጨዋታ አሸናፊ

1969 The Rt Hon Richard Gardiner Casey Baron

of Berwick, Victoria and of the City of

Westminister KG GCMG CH

የአውስትራሊያ ጠቅላይ ገዥ/Governor-General

1965-69

1968 Lionel Rose MBE

የዓለም የቦክስ ውድድር አሸናፊ

1967 The Seekers

የሙዚቃ ቡድን

1966 Sir Jack Brabham OBE

የዓለም ሞተር አነዳድ ውድድር አሸናፊ

1965 Sir Robert Helpmann CBE

ተዋናይ፣ ደናሽ፣ የዘፈን አዘጋጅና አፍላቂ

1964 Dawn Fraser MBE

የኦሎምፒክ ዋና ውድድር አሸናፊ

1963 Sir John Eccles AC

በህክምና ከፍተኛ ማእረግ ኖብል የተከበረ

1962 Alexander ‘Jock’ Sturrock MBE

በአሜሪካ የዝላይ ዋንጫ ውድድር

1961 Dame Joan Sutherland OM AC DBE

ከፍተኛ ድምፅ ያለው ዘፋኝ

1960 Sir MacFarlane Burnet OM AK KBE

በህክምና ከፍተኛ ማእረግ ኖብል የተከበረ

* እንዲሁም በ1975 እና 1979 ዓ.ም መካከል ያለውን የካንበራ

አውስትራሊያ ቀን ምክር ቤትን በአውስትራሊያ ዓመታዊ በዓል

በኩል አድናቆቱን ይገልጻል።

ሽልማቱ በሚሰጥበት ጊዜ የተሸላሚው ስም ከታወቀ በኋላ

የእጩዎች ስም ይለጠፋል።

1970 His Eminence Cardinal Sir Norman

Gilroy KBE

የመጀመሪያ አውስትራሊያ ተወላጅ ታላቅ ቄስ

ክፍል 4 – አውስትራሊያ በዛሬ ቀን 47
የአውስትራሊያ ገንዘብ

የእኛ ገንዘብ ስለአውስትራሊያ ጠቃሚ የሆኑ የህዝብ ምስልና ምልክቶችን የያዘ ነው። በአውስትራሊያ ታዋቂ ዝነኛ የሆኑትን ሰዎች

በመምረጥ በገንዘቡ ላይ እንዲታዩ ሲደረግ እነዚህም በማሕበራዊ ምስረታ፣ ሳይንስ፣ ፖለቲካ፣ በውትድርና አፈጻጸም እና በስነ-ጥበብ

አጀማመር ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ናቸው።

አሮጌና አዲስ የፓርሊያመንት ስርወ መንግሥት

ንግሥት ኢሊዛበት/Queen Elizabeth II

(1926 ዓ.ም ተወለዱ)

የ $5 ዶላር የወረቀት ገንዘብ በካንበራ ውስጥ ያለን ሁለቱን

የአሮጌና አዲስ ፓርሊያመንት ስርወ መንግሥትን ያሳያል።

ዳመ ማርይ ጅልሞር/Dame Mary Gilmore

(1865 – 1962)

ንግሥት ኢሊዛበት/Queen Elizabeth II የአውስትራሊያ

መስተዳድር ዋና ሹም ናቸው። የአውስትራሊያና የዩናይትድ

ኪንግዶም/United Kingdom ንግሥት ሲሆኑ ኑሯቸው

በእንግሊዝ አገር/England ነው። በነበራቸው የረጅምና ታዋቂ

ዘመነ ንግሥት ጠንካራና ቋሚ የሆነ አቋም እንደነበራቸው ነው።

አንድረው ባርተን ፓተርሶን/AB ‘Banjo’ Paterson

(1864 – 1941)

ዳመ ማርይ ጅልሞር/Dame Mary Gilmore ደራሲ፣ ጋዜጠኛ፣

ግጥም ገጣሚና ለማሕበራዊ ምስረታ የዘመቱ ሴት ነበሩ። ሴቶችን፣

የአገር ተወላጅ የሆኑትን አውስትራሊያኖችና ድሀዎችን በመወከል

ለጻፉትና ለተናገሩት ይታወሳሉ።

ረቨረንድ ጆን ፍልን/Reverend John Flynn

(1880 – 1951)

አንድረው ባርቶን ፓተርሶን/Andrew Barton Paterson

የግጥም፣ የዘፈን ደራሲና ጋዜጠኛ ነበሩ። ‘Banjo’ በሚል ስያሜ

እንደጻፉና በአውስትራሊያ ውስጥ በጣም ዝነኛ የሆነ የባህል

ሙዚቃ/መዝሙር ‘Waltzing Matilda’ የሚለውን በመጻፋቸው

ይታወሳሉ።

ማርይ ሪበይ/Mary Reibey (1777 – 1855)

ረቨረንድ ጆን ፍልይንግ/Reverend John Flynn በዓለም

የመጀመሪያውን የአየር ወለድ ህክምና አገልግሎት፣ ሮያል ፍልይንግ

ዶክተር አገልግሎት የሚለውን የጀመሩት ናቸው። በአውስትራሊያ

ገጠር አካባቢ የህክምና አገልግሎትን በመጀመር የብዙ ህይወትን

ስላዳኑ ይታወሳሉ።

ማርይ ሪበይ/Mary Reibey በኒው ሳውዝ ዌልስ ቅኝ ግዛት

ውስጥ ሀሳብ በማመንጨት ለሴት ነጋዴ መንገድ ቀዳጅ ነበሩ።

አውስትራሊያ በወጣትነታቸው እንደገቡ ሰፋሪ በመሆን በማህበረሰቡ

ውስጥ የተከበሩ መሪ ሆኑ።

48

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
ኢድት ኮዋን/Edith Cowan (1861 – 1932)

ዳቪድ ዩናፖን/David Unaipon (1872 – 1967)

ኢድት ኮዋን/Edith Cowan የማሕበራዊ ሠራተኛ፣ ፖለቲከኛና

ለሴቶች እኩልነት መብት ተከራካሪ ነበሩ። በማንኛውም

የአውስትራሊያ ፓርሊያመንት ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡ ሴት

ነበሩ።

ዳቪድ/David Unaipon ጸሀፊ፣ የህዝብ ቃለ አቀባይና ፈላስፋ

ነበሩ። የአቦርጂናል ህዝብን ሁኔትዎች ለማሻሻል ሲባል በሳይንስና

በስነ-ጽሁፍ ላደረጉት አስተዋጽኦ ሲታወሱ ይኖራሉ።

ሰር ጆን ማናሽ/Sir John Monash

(1865 – 1931)

ዳመ ነሊ መልባ/Dame Nellie Melba

(1861 – 1931)

Sir John Monash ኢንጂነር፣ አስተዳዳሪ እና በአውስትራሊያ

ከታወቁት ታላቅ ኮማንደሮች ውስጥ አንደኛው ነበሩ። ባደረጉት

አመራር፣ መረጃ አሰባሰብና አንደበተኛ በመሆናቸው ሲታወሱ

ይኖራሉ።

Dame Nellie Melba በዓለም ዝነኛ የድምጽ ዘፋኝ ነበሩ።

በዓለም ዙሪያ ‘የዘፈን ንግሥት/Queen of Song’ በሚል

መጠሪያ ሲታወቁ፤ በዓለም አቀፍ ከታወቁት የመጀመሪያ

አውስትራሊያዊት ዘፋኝ ነበሩ።

ክፍል 4 – አውስትራሊያ በዛሬ ቀን 49
ብሄራዊ ቀናትና ክብረ በዓላት

ያለን የክርስቲያን ቅርሳችን/Judaeo-Christian የሚንጸባረቀው በአውስትራሊያ ብሄራዊ ክብረ በዓላት በኩል ሲሆን አውሮፓኖች

እስከሰፈሩበት ጊዜ ለአውስትራሊያዊነት ታሪካዊ አመጣጥ ማክበር ይሆናል።

የተወሰኑ ቀናት

የአዲስ ዓመት ቀን ጥር/January 1

ለአዲስ ዓመት መጀመሪያ እናከብራለን።

የአውስትራሊያ ቀን ጥር/January 26

ይህንን የምናከብርበት ምክንያት አውስትራሊያዊነት ምን እንደሆነ

ለማሳየትና በ1788 ዓ.ም የመጀመሪያው ጦር መርከቦች ሲይድነይ

የገቡበትን ለማስታወስ ነው።

የአንዛክ/Anzac Day ሚያዚያ/April 25

በአንደኛ የዓለም ጦርነት ጊዜ የጦር ብርጌድ ከጋሊፖሊ/Gallipoli

ተነስቶ በአውስትራሊያና በኒው ዚላንድ መሬት ላይ ያረፈበትን

እናስታውሳለን። እንዲሁም በዚህ ግጭት ጊዜ ላገለገሉና ለሞቱ

አውስትራሊያኖች በሞላ በዚህ በቀን ክብራችንን እንገልጻለን።

የገና ቀን/Christmas Day ታህሳስ/December 25

ጌታ እየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት በመሆኑ ስጦታ የሚሰጥበት ቀን

ይሆናል።

የቦክስ ቀን/Boxing Day ታህሳስ/December 26

የገና በዓል አንዱ ክፍል ይሆናል።

የተለያዩ ቀናት

የወዛደሩ ቀን/Labour Day ወይም የስምንት ሰዓት ቀን/Eight

Hour Day

በዓለም የመጀመሪያ የሆነን – በአውስትራሊያ ሠራተኞች በቀን

የስምንት ሰዓት ሥራ ስለማሸነፍ ማክበር ይሆናል።

ፋሲካ/Easter

የጌታ እየሱስ ክርስቶች የሞትና ትንሳኤ የሆነውን የክርስቲያን

ታሪክ መታሰቢያ ለማክበር ነው።

የንግሥት ልደት/Queen’s Birthday

በአውስትራሊያ መስተዳድር ዋና አዛዥ የሆኑትን የንግሥት

ኤልዛቤት/Queen Elizabeth II ልደት ቀን ይከበራል። ይህ

ክብረ በዓል በሰኔ/June ወር በሁለተኛው ሰኞ ቀን ከዌስተርን

አውስትራሊያ በስተቀር በእያንዳንዱ መስተዳድር ግዛትና ተሪቶርይ

ይከበራል።

ሌላ ህዝባዊ በዓላት

እነዚህ ህዝባዊ በዓላት በተለያዩ መስተዳድር ግዛቶች፣ ተሪቶርይስን

ከተማዎች ይካሄዳሉ። ለምሳሌ፡ የአውስትራሊያ ተሪቶርይ ዋና

ከተማ የካንበራ ቀን/Canberra Day አለው፣ ሳውዝ አውስትራሊያ

የፈቃደኞች ቀን/Volunteers Day ሲኖረው እንዲሁም ዌስተርን

አውስትራሊያ ደግሞ የመስራች ቀን/Foundation Day ህዝባዊ

በዓላት ይሆናሉ።

በአዲስ ዓመት ዋዜማ ምሽት ርችት በስይድነይ ሀርቦር/Sydney Harbour 2005 ላይ

50

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
የአውስትራሊያ ህዝብ

አውስትራሊያ ወደ 22 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ብዛት እንዳላትና

በዓለም ውስጥ በጣም ብዛትና የተለያዩ ሕብረተስቦች የሚገኝባት

አገር ናት። የተወላጁ አውስትራሊያዊ ህዝብ ብዛት ከአግሪቷ ጠቅላላ

ህዝብ ከመቶ 2.5 እጅ ይሆናል። ከአውስትራሊያ ነዋሪዎች አንድ

አራተኛው በውጭ አገር የተወለዱ ሲሆን ከ200 አገሮች በላይ

ተሰደው የመጡ ናቸው። የአውስትራሊያ ህዝብ ከተለያየ አገር

በመሆኑ ብዛት ያለው ቋንቋዎች፣ እምነቶች፣ ልምዶችና ባህሎች

እንዲኖራት አድርጓል።

ከታላቋ ብሪቴን ጋር የአውስትራሊያ መደበኛው መተሳሰር ከጊዜ

ጋር እያከተመ ሲሆን ነገር ግን በአውስትራሊያ ተቋማት ውስጥ

የታላቋ ብሪቴን ተጽእኖ ይኖራል። እንዲሁም በመድብለ ባህላችን

ውስጥ እንደሚገኝና የብሄራዊ ቋንቋችን ያካትታልስ። በአገሪቷና

በማህበረሰቡ ውስጥ ከ200 በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች (ብዙ የአገር

ተወላጁን ቋንቋዎች ያካተተ) ቢነገርም፣ ነገር ግን እንግሊዝኛ

ጣቃሚና አስፈላጊ የሆነው ብሄራዊ ቋንቋችን ይሆናል።

የአውስትራሊያ ኢኮኖሚ

አውስትራሊያ የማይቀያየርና ተወዳዳሪነት ያለው ኢኮኖሚ አላት።

ንቁና በሙያ ለተካኑ ሠራተኞቻችን ክብር ዋጋ እንሰጣለን። ስዎች

በአውስትራሊያ ውስጥ ያላቸው የኑሮ ደረጃ ጥራት በዓለም ውስጥ

ካለው ከፍተኛ ደረጃ አንዱ ይሆናል።

ዲክ ስሚዝ/Dick Smith (born 1944)

Dick Smith በአውስትራሊያ የወንድ ነጋዴ ታዋቂ፣ ጀብደኛና

ለበጎ አድራጎት ሥራ ታዋቂ ሰው ናቸው።

የመገበያያ ቦታ

በአውስትራሊያ ዘመናዊና የማይለወጥ የፋይናሻል ተቋማት ሲኖሩ

የንግድ ሥራ እንቅስቃሴን በማያሰጋ ሁኔታ ለማካሄድ ደንቦች

ይኖሩታል እንዲሁም በግብር/ቀረጥ ላይ ጥብቅ ናቸው። የአገልግሎት

አቅራቢ ኢንዱስትሪዎች ማለት ቱሪዝም፣ ትምህርትና የፋይናሻል

አገልግሎትን ያካተተ ከመቶ 70 እጅ የሚሆነው የአውስትራሊያ

ጠቅላላ ውጤት (GDP) ከነዚህ አገልግሎቶች ይሆናል።

የአውስትራሊያ ኢኮኖሚ ያለመለዋወጥ ኢንቨስተሮች እንዲመጡ

ያደርጋል። በአውስትራሊያ የሽያጭ ገበያ ከኤሽያ-ፓስፊክ/Asia-

Pacific ክልል በትልቅነት ሁለተኛው ሲሆን ይህም ከጃፓን ቀጥሎ

ይሆናል።

ንግድ

የአውስትራሊያ ንግድ አጋሮች በብዛትs ጃፓን/Japan፣ ቻይና/

China፣ ዩናትድ ስታትስ/the United State፣ ሳውዝ ኮሪያ/

South Korea፣ ኒው ዚላንድ/New Zealand እና ዩናይትድ

ኪንግዶም/the United Kingdom ናቸው። በብዛት ወደ ውጭ

ለንግድ የምናቀርበው ስንዴ፣ ሱፍ፣ የብረት አፈር/አለት፣ ማእድናት

እና ወርቅ ናቸው። እንዲሁም የተፈጥሮ ጋዝንና የከሰል ስብርባሪ

በፈሳሽ መልክ ሆኖ ወደ ውጭ ይላካል። ኢኮኖሚያችን ግልጽ

እንደሆነና የንግድ ሥራ ሁልጊዜ በኢኮኖሚ ክፍል ጠቃሚ የሆነ

እድል ይከፍታል። በአሁኑ ጊዜ የአውስትራሊያ ኤክስፖርት ንግድ

በአጠቃላይ ደህና ሲሆን ከ $200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው።

የማእድን ቁፋሮ

አውስትራሊያ በተፈጥሮ ሀብት ያከበተች ስትሆን እንደ የድንጋይ

ከሰል፣ ኮፐር፣ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝና የማእድን ስብርባሪ ያሉ

ናቸው። እነዚህ ከፍተኛ ተፈላጊነት እንዳላቸውና በተለይ በኤሽያ

የኢኮኖሚ እድገት ላይ ይፈለጋሉ።

Dick Smith የመጀመሪያ

እድላቸውን በኤሌክትሮኒክ

ንግድ አድርገዋል። ሀብት

ንብረታቸውን ለአውስትራሊያ

እድገት አውለውታል።

በአውስትራሊያ ብቻ ላለ

የምግብ ኩባንያ እንደጀመሩና

በሚሊዮኖች የሚቆጠር

ዶላር ገንዘብ ንብረትነታቸው

የአውስትራሊያ ለሆኑ

ኩባንያዎች ሥራ አውለውታል።

በ1986 ዓ.ም የዓመቱ

አውስትራሊያዊ የሚል ስም እንደተሰጣቸውና ለአካባቢ ጥበቃና

ለቴክኒካል መሻሻል በተዘጋጀ ሽልማት አሸንፈዋል። በሞቃት አየር

በተሞላ የመንሳፈፊያ ፉኛ ውስጥ ሆነው አውስትራሊያንና የታዝማን

ባህርን ያቋረጡ የመጀመሪያው ሰው ነበሩ። በንግድ ሥራቸው

መሳካትና ለአውስትራሊያ ባላቸው ልባዊ ፍቅር ስላደረጉት ጀግንነት

ይታወቃሉ።

የአውስትራሊያ ትልቁ የኤክስፖርት ንግድ በማእድናትና በነዳጅ ይሆናል

ክፍል 4 – አውስትራሊያ በዛሬ ቀን 51
አውስትራሊያ እንደ ዓለም

አቀፍ ዜጋ

አውስትራሊያ የዓለም አቀፍ ዜጋ ለመሆን በምታካሂደው ተግባር

ያኮራታል። ለዚህም በዓለም ዙሪያ ከእኛ ያልተሻሉትን አገሮች

በመርዳት እናሳያለን።

የአውስትራሊያ ዓለም አቀፋዊና የሰብዓዊ ጥረት

ታዳጊ አገሮች ድህነትን ለመቀነስና የተረጋጋ ልማትን ለማነጽ

ይረዳ ዘንድ በአውስትራሊያ መንግሥት የዓለም አቀፋዊ እርዳታ

ፕሮግራም በኩል ድጋፍ ይድረግላቸዋል። ይህንን እርዳታ

በክልላችን እና በዓለም ዙሪያ ሆኖ ህዝብንና መንግሥትን መርዳት

ይሆናል።

በአገራችን ወይንም በውጭ አገር የመአት አደጋ ሲፈጠር

አውስትራሊያኖች ከፍተኛ ልግስና በማበርከት ያሳያሉ። እንዲሁም

ቀጣይ የሆነ ችግር ላጋጠማቸው አገሮች ብዙጊዜ ምፅዋት

እንለግሳለን። በምናደርገው የእርዳታ ፕሮግራም የአውስትራሊያን

ባህሪ ይዘት ያንጸባርቃል።

በ1971 ዓ.ም አውስትራሊያ የኢኮኖሚክ ማሕበርና እድገት ድርጅት

(OECD) ሙሉ አባል እንደሆነች ነው። የድርጅቱ/OECD ዓላማ

በራሷ 30 አባል በሆኑ አገሮችና ሌሎች ታዳጊ አገሮች ውስጥ

በኢኮኖሚ፣ ማሕበራዊና በሥራና ሠራተኛ ሁኔታ ላይ እንዲሻሻል

ማድረግ ነው። እንዲሁም እግረ መንገዱንም የድርጅቱ ዓላማ

በዓለም ንግድን ለመዘርጋትን ልማስፋፋት ነው።

በኤሽያ-ፓስፊክ ክልል ውስጥ አውስትራሊያ በቅርበት ተባባሪ ሆና

በጣም ትረዳለች። በኤሽያ-ፓስፊክ ኢኮኖሚ ተባባሪ (APEC)፣

በኢስት ኤሽያ ጉባኤ/East Asia Summit (EAS)፣ በአሲን

ክልላዊ ጉባኤ/the ASEAN Regional Forum (ARF) እና

በፓስፊክ አይላንድ ጉባኤ/(PIF) ላይ አውስትራሊያ ተሳታፊ አባል

ናት።

ዶ/ር ካትሪነ ሀምሊን/Dr Catherine

Hamlin AC (በ1924 ዓ.ም ተወለዱ)

Dr Catherine Hamlin

የማህጸን ህክምና ባለሙያ

ሲሆኑ ወጣት ኢትዮጵያውያን

ሴቶችን ከስቃይ በማትረፋቸው

ይታወቃሉ።

ካተሪን/Catherine Hamlin፤

ከ1959 ዓ.ም ጀምሮ

‘ላልተለመደ ማዋለድ ህክምና/

obstetric fistula’ በተባለ

ከመውለድ ጋር የተዛመደ ጉዳት

የኢትዮጵያ ሴቶችን በመርዳት

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ እንደሠሩ ነው። የዚህ ዓይነት ችግር

ያለባቸው ሴቶች የሰውነት አሰራር ሁኔታ ሊቆጣጠሩ ባለመቻላቸው

ከሕብረተሰቡ እንዲገለሉ ያደርጋቸዋል።

ከ2004 ዓ.ም የህንድ ውቂያኖስ ማእበል/ tsunami በኋላ የአውስትራሊያ ችግር

አቃላይ ተግባር በኢንዶኖዝያ አገር

ተሳትፎ

የተባበሩት መንግሥታት (UN) ሲጀመር ከ1945 ዓ.ም ጀምሮ

አውስትራሊያ ትተሳፊ አባል እንደሆነች ነው። በ1951 ዓ.ም

የተባበሩት መንግሥታት ስደተኛ ስምምነት መሠረት፤ ለ1951

ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታት ስደተኛ ደንብ ላሟሉ ሰዎች

አውስትራሊያ የመከላከያ መብታቸውን ታስጠብቃለች። እንዲሁም

በታዳጊ አገሮች ላይ ለተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ

ጥረትና ለሰብዓዊና በድንገተኛ ችግር ጊዜ አስተዋጽኦ እናደርጋለን።

በተጨማሪም በተባበሩት መንግሥታት ለትምህርት፣ ሳይንሳዊና

ባህላዊ ለሆነ ድርጅት ከፍተኛ ተሳትፎ ይኖረናል።

ካትሪን/Catherine እና ባለቤታቸው የአዲስ አበባን ፊስቱላ/ማዋለጃ

ሆስፒታል አቋቁመዋል። በነሱ ጥረት ለብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ

ሴቶች ወደ ገጠር ቤታቸው ተመልሰው ጤናማ የሆነ ኑሯቸውን

እንዲያካሂዱ ረድቷል።

በ1995 ዓ.ም Dr Catherine Hamlin የአውስትራሊያ ትእዛዝ/

Order of Australia ተባባሪ በመሆናቸው ለከፍተኛ አውስትራሊያ

ሽልማት በቅተዋል። ለኢትዮጅያ ሴቶች ለመሥራት እንደቀጠሉ ነው።

በዓለም አቀፋዊ ሸንጎ ላይ የአውስትራሊያ ንቁ

ዛሬ አውስትራሊያ ሰፊና የምታድግ አገር እንደሆነችና በስፖርት፣

በስነ-ጥበባትና ሳይንስ ያላት ግኝት ያኮራል። የህዝባችንን የኑሮ

ጥራት ዋጋ ብንሰጠውም ነገር ግን ሁልጊዜ የበለጠ እንመኛለን።

አውስትራሊያ በዓለም አቀፋዊ የምታደርገው እርዳታና ልማት

የተነሳ በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የምታደርገው የስፖርት ጨዋታ

የተሳካ ይሆናል።

52

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
የአውስትራሊያ ተደናቂ ከፍተኛ ማእረጎች

አውስትራሊያ በሳይንሳዊና ህክምና ምርምር ጥናት የታወቀች ናት። በዚህ መስክ ላይ አስር የአውስትራሊያ ተደናቂ ከፍተኛ ማእረጎች

ተሰጥተዋል።

Professor William Bragg (1862 – 1942) እና Lawrence Bragg (1890 – 1971) የህክምና

ሊቃውንት።

William Bragg (አባት) እና Lawrence Bragg (ወንድ ልጅ) በ1915 ዓ.ም የፊዚክስ ተደናቂ ሽልማት አሸናፊ ሲሆኑ ይህም ‘በራጂ

ምርመራ/X-rays አድርጎ ግልጽ ትንታኔ ስለማድረግ ላደረጉት አገልግሎት’።

Sir Howard Walter Florey (1898 – 1968) የበሽታ ተመራማሪ/Pathologist ነበሩ።

በሳውዝ አውስትራሊያ፣ አደላይድ ውስጥ የተወለዱ ሲሆን፣ ሆዋርድ ፍሎረይ/Howard Florey ‘ለብዙ ተላላፊ በሽታ የሆነውን ለማዳን

ፔኒሲሊን የተባለን መድሃኒት ስላወጡ’ በ1945 ዓ.ም (በጣምራ) በ Physiology ወይም በመድሃኒት ታዋቂነት ሽልማት አግንተዋል።

Sir Frank Macfarlane Burnet (1899 – 1985) የህክምና ሳይንቲስት እና ባዮሎጂስት/Scientist and

Biologist ተመራማሪ ንቸው።

በቪክቶሪያ ውስጥ ተወለዱ፣ ፍራንክ ቡርነት/Frank Burnet ‘የበሽታ መከላከል ሀይል ለመቋቋም መድሃኒት በማግኘታቸው’ በ1960 ዓ.ም

(በጣምራ) በ Physiology ወይም በመድሃኒት ታዋቂነት ሽልማት አግንተዋል።

Sir John Carew Eccles (1903 – 1997) የሰውነት አሰራር ባለሙያ ፊዚዮሎጂስት።

እኒህ ባለሙያ በመልበርን ውስጥ እንደተወለዱና ‘በሰውነት ነርቭ የህብረ ዋህስ ማእከልና ሽፋን ዙሪያ ያለን የአሰራር ችግር በማግኘታቸው’

በ1963 ዓ.ም (በጣምራ) በPhysiology ወይም በመድሃኒት ታዋቂነት ሽልማት አግንተዋል።

Professor John Warcup Cornforth (1917 – 2007) ከሚስት/Chemist.

John Cornforth በስድነይ ውስጥ እንደተወለዱና ‘በስተሪኦ ኬሚስትሪ ስለ ንጥረ ነገሮች ውህድነት ኬሚካላዊ ለውጥ ስላደረጉት ሥራ’

በ1975 ዓ.ም (በጣምራ) በኬሚስትሪ ታዋቂነት ሽልማት አግንተዋል።

Professor Peter Doherty (በ1940 ዓ.ም ተወለዱ) የበሽታ መከላከያ ባለሙያ/Immunologist.

Peter Doherty በኩንስላንድ ውስጥ እንደተወለዱና ‘ብተለይ ስለ በሽታ መቋቋሚያ ሀይል ተከላካይ ሴል በተመለከተ ላስገኙት ጥሩ ውጤት’

በ1996 ዓ.ም (በጣምራ) በ Physiology ወይም በመድሃኒት ታዋቂነት ሽልማት አግንተዋል።

Professor Barry Marshall (በ1951 ዓ.ም ተወለዱ) የሆድ እቃ ባለሙያ/Gastroenterologist እና ዶክተር

ሮቢን ዋረን/Doctor Robin Warren (በ1937 ዓ.ም ተወለዱ) የበሽታ ባለሙያ/Pathologist.

Barry Marshall እና Robin Warren በጋራ ሆነው ‘ስለ ባክቴርም/bacterium Helicobacter pylori ችግርና የሚያስከትለው የጨጓራ

በሽታና የምግብ መፍጨት ቁስለት በሽታን በማወቃቸው’ በ2005 ዓ.ም በ Physiology ወይም በመድሃኒት ታዋቂነት ሽልማት አግንተዋል።

Professor Elizabeth Helen Blackburn (በ1948 ዓ.ም ሲወለዱ) የባዮሎጂ/Biologist ሊቅ ናቸው።

ኤልዛበት ብላክበርን የተወለዱት በሆባር/Hobart ውስጥ ሲሆን ይርኖብል ሽልማት ያገኙት በፊዚዮሎጂ ወይም በ2009 ዓ.ም ከህክምና

ጋር ‘ባደረጉት ምርምር ጥናት ሲሆን እንዴት የተሎመርስ እና የተሎማርስ ኢንዛይም ንጥረ ነገሮች የክሮሞሶምስ ውህደትን እንደሚከላከሉ

ይሆናል’።

እንዲሁም አውስትራሊያ በስነ-ጽሁፍ አንድ ታዋቂ ማእረግ አለ።

Patrick White (1912 – 1990) የኖቭል ተሸላሚና የቲያትር ደራሲ ነበሩ።

አውስትራሊያዊ ከሆኑ ወላጆች ሎንዶን ውስጥ ተወለዱ፤ Patrick White ‘አዲስ አርእስት የሆነውን የጀግንነት ግጥምና ስሜት ቀስቃሽ

ደራሲ በመሆናቸው’ በ1973 ዓ.ም በስነ-ጽሁፍ ደራሲ ታዋቂነት ሽልማት አግንተዋል።

ክፍል 4 – አውስትራሊያ በዛሬ ቀን 53
ክፍል 5

የአውስትራሊያችን ታሪክ

በአውስትራሊያ የአገር ተወላጁ ባህሎች በዓለም ላይ የጥንት የዱሮ እንደሆኑና ቀጣይነትም አላቸው።

54

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
የአውስትራሊያ ታሪካችን

ይህ የአውስትራሊያ አጭር መግለጫ ምንም ይሁን እንደ ሙሉ

ታሪክ አይሆንም፣ ነገር ግን ለአገራችንና ባህላችን መልክ መቀየር

ሀሳብ ሊሰጥዎ ይችላል። መሬቷ ለብዙ ሺህ ዓመታት በአገር

ተወላጆች የተያዘችና እንክብካቤ ይደረግላት እንደነበረ ነው።

በ1788 ዓ.ም የመጀመሪያው ጦር መርከብ ሲደርስ ከዚያም በኋላ

ኑሯቸውን እንደቀየሩ ነው። አውስትራሊያ ባለፉት 200 ዓመታት

ውስጥ ወደ መድብለ ባህላዊነት የሚመራ መንገድና የእርቅ ድርድር

በተመለከት የሰብዓዊ መብቶች እኩልነት ትምህርት እንዳገኘች

ነው። ያደረግነው ምስረታ ማለት አሁን ላለንበት የአውስትራሊያ

ማህበረሰብ እያንዳንዱን ሰው በማካተት ዋጋ እንዲሰጠው

አድርጓል።

የአውስትራሊያ አገሬው ተወላጆች

የአውስትራሊያ አገሬው ተወላጅ ባህሎች በዓለም ውስጥ የጥንት/

የድሮና ቀጣይነት ያለው ባህሎች ይሆናሉ። የአውስትራሊያ አገሬ

ተወላጆች ከ40 000 እስከ 60 000 ዓመታት ኖረዋል።

አቦርጂናልና ቶረስ ስትሬት አይላንደር እያንዳንዱ የተለያየ ባህሎች

ይኖረዋል። የራሳቸው የሆኑ ቋንቋዎችና የባህል ልምዶች አላቸው።

የአቦርጂናል ሰዎች በታሪክ በውሀ ካልተከበበ የአውስትራሊያና

ታዝማኒያ መሬት የመጡ ናቸው። የቶረስ ስትሬርት አይላንደርስ

ሰዎች ደግሞ በኩዊንስላንድና ፓፑዋ ኒው ጉኒያ/Papua New

Guinea መካከል ካሉ ደሴቶች የመጡ ናቸው። የቶረስ ስትሬርት

አይላንደርስ ባህሎች ከፓፑዋ ኒው ጉኒያ/Papua New Guinea

እና ከሌሎች የፖሲፊክ ደሴቶች/Pacific islands ጋር ብዙዎቹ

ባህሎች ተመሳሳይ ናቸው።

ቋንቋዎች

ከብሪቲሽ ሰፋሪዎች በፊት በአቦሪጅናልና ቶረስ ስትሬት አይላንደር

ህዝብ ከ700 በላይ ቋንቋዎችና የአነጋገር ዘይቤዎች ይጠቀሙ

እንደነበር ነው። በአሁኑ ጊዜ ወደ 145 የሚሆኑ ቋንቋዎች ጥቅም

ላይ ይገኛሉ። የጽሁፍ ቋንቋ አልነበረም። የአገር ተወላጁ ባህሎች

በአፈ ታሪክ ማውራቱ እጅግ አስፈላጊ ሲሆን ምክንያቱ ስለ ህዝብና

መሬቷ ታሪክ ስለሚናገሩ ነው። ለምሳሌ፡ በቪክቶሪያ የፖርት ፊሊፕ

ባይ/Port Phillip Bay ጎርፍ ሲወራ ይህ የሚያሳየው ከ10 000

ዓመታት በፊት ስለተፈጠረው ችግሩ ይገልጻል።

የአገሬ ተወላጁ ስነ-ጥበባትና የወደፊት ምኞች

የተለያዩ የአገሬው ተወላጅ ጎሳዎች የራሳቸው የሆነ ስም ሲኖራቸው

ይህም በእንግሊዝኛ ‘ምኞት/Dreaming’ ይባላል። የአገሬውን

ተወላጅ ሕይወት ለመምራት ምኞት ወይም የህልም እንጀራ

የእውቀት፣ የእምነትና የተግባር መግለጫ ዘዴ ይሆናል። ይህም

ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩና እራሳቸውን ከክፉ ማራቅ እንዳለባቸው

ያሳያል። ደንቦችን የማይከተሉ ሰዎች ይቀጣሉ።

ካካዱ የአቦርጂናል ስነ-ጥበብ/Kakadu Aboriginal art

ህጻናት የምኞት ታሪኮችን በወላጆችና በእድሜ ትልቅ በሆኑ ሰዎች

ይነገራቸው ነበር። እንዴት መሬታቸው መልክ እንደያዘና መኖሪያና

እንዴት/ለምን አደብ መያዝ እንዳለባቸው፣ ህጻናት በነዚህ ታሪኮች

በኩል ይማራሉ። እንዲሁም ህጻናት ጠቃሚና ተግባራዊ የሆነ

ትምህርቶችን በነዚህ ታሪኮች ሲያገኙ፤ ለምሳሌ፡ ምግብ የት

እንደሚያገኙ።

የአገሬው ተወላጅ ሙዚቃ፣ ዘፈንና ዳንስ የሚያሳየው የወደፊት የእለት

ኑሮን ታሪካዊ ምኞትን ይሆናል። የአገሬ ተወላጁ ሲደንስና ሲዘፍን

ከነሱ የትውልድ ሀረግ ጋር በጥልቀት በማተይያዘ ስሜት ነው።

የመጀመሪያው የአቦርጂናል ስነ-ጥበብ የተሰራው በድንጋይ ላይ

ቅርፅ ወይም ቀለም መቅባትና በወለል መሬት ላይ የንድፍ ጥበብ

በማውጣት ነበር። ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ 30 000 ዓመታት

እድሜ አላቸው። በማእከላዊ አውስትራሊያ ያሉ ሰዎች ነጠብጣብና

በክብ ቀለማት በማድረግ መሬትን ወይም ታሪኮችን በመወከል

ምኞትን ይገልጻሉ። በሰሜናዊ አውስትራሊያ ክፍሎች ደግሞ የሰው

ልጆችን፣ እንስሳትንና ምኞትን ስእል በመሳል ይገልጻሉ።

ምኞት ዛሬም ቢሆን ለአገሬው ተወላጅ ጠቃሚና የሚቀጥል

እንደሆነ ነው።

ክፍል 5 – የአውስትራሊያችን ታሪክ 55
የመጀመሪያ አውሮፓውያን ወደ

አውስትራሊያ

የመጀመሪያው የአውሮፓ ተዘዋውሮ ማጥናት

በ17ኛው ምእተ ዓመት፣ የፖርቱጉስ/ Portuguese እና የዱትች/

Dutch አሳሾች በደቡብ ክፍል የማይታወቀውን መሬት ‘ተራ

አውስትራሊስ ኢንኮግኒታ/Terra Australis Incognita’ የተባለውን

ተዘዋውረው በማጥናት አግንተዋል። በ1606 ዓ.ም የዱትች ሰው

የሆኑት፣ ዊለም ጃንስዙን/ Willem Janszoon፣ በሰሜናዊ

አውስትራሊያ ጫፍ በምዕራባዊ በኩል ያለን ካፕ ዮርክ ፐኒንሱላ/

Cape York Peninsula ካርታ ሠርተዋል። በዚህን ጊዜ አካባቢ

ሉስ ቫዝ/Luis Vaez de Torres ከፖርቱጋል/ Portugal

በመርከብ አቋርጠው ወደ ሰሜናዊ አህጉር የባህር ወሽመጥ ደርሰዋል።

ከዚያም በኋላ በ1600ዎች ዓመታት፣ የደትች መርከብ ተጓዦች

በምዕራብ አውስትራሊያ ባህር ጠረፍ ያለውን ተዘዋውረው

አጥንተዋል። ደትች ይህንን መሬት ‘ኒው ሆላንድ/New Holland’

የሚል ስም ሰጥተውታል።

በ1642 ዓ.ም አበል ታዝማን/Abel Tasman የተባሉት በባህር

ጠረፍ ላይ አዲስ መሬት እንዳገኙና ስሙንም ‘ቫን ዴመንስ ላንድ/

Van Diemen’s Land’ (የአሁኑ ታዝማኒያ) ብለውታል።

እንዲሁም በሺዎች ማይልስ ርቀት የሚቆጠር የአውስትራሊያን ጠረፍ

በካርታ ላይ አስፍረዋል። የኒው ሆላንድ/New Holland ማፕ/

ካርታን ያላጠናቀቁበት ምክንያት መሬቱ ከስሜናዊ ፓፑ ኒው ጉኒ/

Papua New Guinea ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ ለማሳወቅ ነው።

ወንጀለኛን ስለማጓጓዝ

አውስትራሊያን ልዩ የሚያደርጋት ቢኖር የመጀመሪያ

አውሮፓውያን ሰፋሪዎች ወንጀለኞች ስለነበሩ ነው። የተባበሩት

አሜሪካ (USA) ነጻነቷን ካገኘች በኋላ ግሬት ብሪቴን እስረኞቿን

ወደ አሜሪካ መላክ አቆመች። በብሪቴን ያለው እስር ቤት በታም

እንደተጣበበ ነው። በብሪቴን አገር የወንጀለኛ ቁጥር በጣም

ስለጨመረ ለእስረኞች የሚሆን መንግሥት አዲስ ቦታ መፈለግ

አለበት። በ1786 ዓ.ም አዲስ ቅኝ ግዛት ወደሆነችው ኒው ሳውዝ

ዌልስ/New South Wales እስረኞችን ለመላክ ታላቋ ብሪቴን

ወሰነች። ይህ ‘ማጓጓዝ/transportation’ በሚል ይጠራል።

የመጀመሪያ ቅኝ ግዛት

የመጀመሪያ ኒው ሳውዝ ዌልስ/New South Wales ቅኝ ግዛት

ገዥ ካፕቴን አርቱር ፊሊፕ/Captain Arthur Phillip ይባላሉ።

የመጀመሪያውን 11 የጦር መርከቦች ያለችግር ከብሪቴን ወደሌላ

የዓለም ክፍል ያመጡ ሰው ናቸው። ወንጀለኞችን በመቀለብና

ደህንነታቸውን በጣም ይንከባከቡ እንደነበርና በጣም አነስተኛ የሆኑ

በጉዞ ላይ እንደሞቱ ነው።

Captain Phillip የመጀመሪያ የጦር መርከብ አዛዥ ሆነው ወደ

ስይድነይ ባህር ወሽመጥ/Sydney Cove ጥር/January 26

ቀን 1788 ዓ.ም ደረሱ። ይህም በመታሰቢያ በዓላት ውስጥ ያለና

እኛም በየዓመቱ የአውስትራሊያ ቀን በሚል እናከብራለን።

ዊሊአም ዳምፔር/William Dampier የተባሉት በአውስትራሊያ አፈር

ለመጀመሪያ የረገጡ ኢንግሊዛዊ ሰው ነበሩ። በ1684 ዓ.ም በሰሜን

ምዕራብ ጠረፍ ደረሱ። መሬቱ ደረቅና አቧራማ ስለነበር ታዲያ

ለንግድ ወይም ለሰፈራ ይሆናል ብለው ግምት ውስጥ አላስገቡትም።

ካፒቴን ጃመስ ኮክ/Captain James Cook

የምሥራቅ አውስትራሊያ ጠረፍ እንግሊዛዊ የሆኑት ጃመስ ኩክ/

James Cook፣ ‘ኢንዲቮር/Endeavour’ በተባለው መርከባቸው

በ1770 ዓ.ም ከመድረሳቸው በፊት በኢሮፓውያን ተዘዋውሮ ጥናት

እንዳልተደረገ ነው። ኩክ/Cook የደቡባዊ ፓሲፊክን ተዘዋውረው

እንዲያጠኑ በሚል የብሪቲሽ መንግሥት ለረዥም ጉዞ ልኳቸዋል።

በቦታንይ ባህር ወሽመጥ/Botany Bay ላይ በማቆም የምሥራቅ

ጠረፍ ካርታ ሲያነሱ፣ ይህም በዘመናዊ ስይድነይ ደቡባዊ ክፍል

ይገኛል። ጃመስ ኩክ/James Cook ይህንን መሬት ‘New

South Wales’ በሚል እንደሰየሙትና በንጉስ ጂወርጅ/King

George III ተብሎ እንዲጠራ ጠየቁ።

የመጀመሪያ ጦር መርከብ ከብሪቴን ተነስቶ ሲድነይ የባህር ወሽመጥ ላይ በ1788

ዓ.ም ደረሰ

የመጀመሪያዎቹ ዓመታት

የመጀመርያ ዓመታት የሰፈራ ሁኔታ በጣም ከባድ ነበር። ገዥ

ፊሊፕ እራሳቸውንና መኮንኖቻቸው ጨምሮ፣ እያንዳንዱ ሰው

ተመሳሳይ የምግብ መጠን በማግኘት እንዳይራቡ ለማድረግ

ያረጋግጣሉ። በቅኝ ግዛት ያሉትን የመጀመሪያ ዓመታት ችግር

ለመወጣት የርሳቸው ቅን አስተሳሰብና ውሳኔ እረድቷል።

የመጀመሪያዎቹ የሰፈራ ዓመታት ከባድ ሥራዎች በወንጀለኛ

የጉልበት ሀይል ተፈጽሟል። ወንጀለኞቹ በጣም ካልሠሩ ወይም

ክሥራ ካፈገፈጉ ወይም ከሰከሩ ይገረፉ እንደነበር ነው። ከባድ

ወንጀል ከፈጸሙ ወደ በርሀ የሰፈራ ቦታ ይላካሉ ወይንም

ይታነቃሉ። የእስር ጊዚያቸውን ያጠናቀቁ ወንጀለኞች በማህበረሰቡ

ውስጥ ገብተው ለመሥራትና ቤተሰብ ለመመስረት ነጻ ናቸው።

የኒው ሆላንድ አበል ታስማን/Abel Tasman’s ማፕ/ካርታ፣ 1644 ዓ.ም

56

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
አዲስ እድሎች

በአውስትራሊያ የመጀመሪያ አውሮፓ ህዝብ ከእንግሊዝ፣ ስኮቲሽ፣

ወልሽና አይሪሽ አገር የመጡ ሰዎች ናቸው። ስኮቲሽ፣ ወልሽና

አይሪሽ ብዙጊዜ ከእንግሊዝ ጋር ጦርነት የነበሩ ሲሆን ነገር

ግን በአውስትራሊያ ውስጥ አራቱም ቡድኖች አብረው ለመኖርና

ለመሥራት ይቀራረባሉ።

በቅኝ ግዛት ውስጥ ለወንጀለኛ እና ወንጀለኛ ለነበረ ለመለየት አዲስ

እድል ተጀመረ። የጦር መኮንኖች ገንዘብ ለማግኘት ጊዚያቸውን

ወንጀለኛ እና ወንጀለኛ ለነበረ ለመቅጠር መርዳት በሚል ይነግዱ

ነበር። አንዳንድ ወንጀለኛ ያልነበሩት ወዲያውኑ በራሳቸው የንግድ

ሥራ ላይ እንደ ነጋዴዎች በመሆን ተሰማሩ። ሌሎቹ ደግሞ እንደ

ገበሬ፣ የወንድ ነጋዴ፣ ባለሱቅና የህዝብ አስተናጋጅ ሆነው በጥሩ

ተሰማርተዋል። እንዲሁም ወንጀለኛ ያልነበሩት ስቶች በንግድ ሥራ

ደስተኞች እንደሆኑና ከእንግሊዝ አገር ካሉት ሴቶች ጋር ሲወዳደር

የተሻለ ነጻነት እንዳላቸው ነው።

ካሮሊን ቺሾልም/Caroline Chisholm

(1808 – 1877)

Caroline Chisholm

የተባሉት ቀደም ሲል በነበሩ

ቅኝ ግዛቶች ላይ የብቸኛ

ሴቶችን ሁኔታ ለማሻሻል ሲባል

ለማሕበራዊ መስራች አመራር

ሰጪ ነበሩ።

ካሮሊን/Caroline ከጦር

መኮንን ባላቸው እና አምስት

ህጻናት ጋር በመሆን በ1838

ዓ.ም ወደ አውስትራሊያ

እንደመጡ ነው። በስድነይ

መንገድ ላይ የሚተዳደሩትን

ማይግራንት/መጤ ሴቶች እረድተዋል። በጥቂት ዓመታት ውስጥ

እኒህ ሴት 16 የማይግራንት ሴቶች ሆስተሎችን በግዛቱ ውስጥ

አቋቁመዋል።

ካሮሊን/Caroline ከጦር መኮንን ባላቸው እና አምስት ህጻናት

ጋር በመሆን በ1838 ዓ.ም ወደ አውስትራሊያ እንደመጡ ነው።

በስድነይ መንገድ ላይ የሚተዳደሩትን ማይግራንት/መጤ ሴቶች

እረድተዋል። በጥቂት ዓመታት ውስጥ እኒህ ሴት 16 የማይግራንት

ሴቶች ሆስተሎችን በግዛቱ ውስጥ አቋቁመዋል።

በመርከብ አድርገው ወደ ቅኝ ግዛቶች ለሚጓዙ ሰዎች የኑሮ

ሕይወታቸው እንዲሻሻል ካሮሊን/Caroline በጣም ሠርተዋል።

እንዲሁም ለተቸገሩ ሰዎች ከጥገኝነትና ድህነት ለማላቀቅ የብድር

ማስገኛ እቅድ በማውጣት እንደረዱ ነው።

እዲስ ገዥን ማስታወቅ

ከገዥ ፊሊፕ/Phillip ጎን ለጎን የገዥ ላችላን ማኳሪ/Governor

Lachlan Macquarie አስተዳድር ቀደም ሲል ለነበረን

ታሪክ ጠቃሚ ቦታ ይሰጠዋል። የኒው ሳውዝ ዌልስን ቅኝ ግዛት

ከ1810 እስከ 1821 ዓ.ም አስተዳድረዋል። የግኝ ግዛትን እንደ

ነጻነት ያለው የሰፈራ ቦታ እንዲሆን እንጂ እንደ የወንጀለኛ

ቅኝ ግዛት ለማድረግ አልነበረም። የእርሻ ሥራ እንዲሻሻልና

አዲስ መንገዶችን በማነጽና ለህዝብ መገልገያዎች እንዲሻሻል

አድርገዋል። በአውስትራሊያ የተሻለ ግኝትን በማጥናት ኣግዘዋል።

እንዲሁም ማኳሪ/Macquarie ገንዘባቸውን በትምህርት ላይ

በማዋል የቀድሞ ወንጀለኞች መብት እንዲከበር አድርገዋል።

ለአንዳንድ ወንጀለኛ የነበሩ ሰዎች እንደ ዳኞችና የህዝብ

አገልግሎቶች መስክ ሥራ ሰጥተዋቸዋል።

ገዢ ማኳሪ/Macquarie በቅኝ ግዛት ላይ አወንታዊ የሆነ ለውጥ

በማስገኘታቸው ክቡርነታቸው በታሪክ የተመዘገበ ነው። በኒው

ሳውዝ ዌልስ የማኳሪ ዩኒቨርሲቲ/Macquarie University

በሳቸው ስም ይጠራል።

የወንጀለኛችን ቅርስ

ከማኳሪ/Macquarie’s አስተዳደር በኋላ የገዥው ስልጣን ለአንድ

ወንድ ይሰጣል የሚል ጥርጣሬ ስለነበር፣ ስለዚህ በ1823 ዓ.ም

ስለሚቀጥለው ገዥ መደብ ምክር ይሆን ዘንድ በኒው ሳውዝ

ዌልስ የህግ ምክር ቤት ህግ ደንብ አወጣ። ከዚያም የህግ ምክር

ቤቱ የቅኝ ግዛት ለመመስረት ሙከራ ተደጓል፣ ታዲያ ወንጀለኞች

በሚገባ ስለተቀጡ በጥሩ ሁኔታ እንዳልኖሩ ነበር። ስለሆነም

በመጀመሪያ 19ኛው ምእተ ዓመት ላይ በኒው ሳውስ ዌልስ

እናበአውስትራሊያ ዙያ በተቁቋሙ ቅኝ ግዛቶች ያሉትን የወንጀለኛ

ኑሮ እድልን ሊዘጋ እንዳልቻለ ነው።

በአጠቃላይ ከ160 000 በላይ የሚሆኑ ወንጀለኞች ወደ

አውስትራሊያ ተጉዘዋል። በ1840 ዓ.ም ታላቋ ብሪቴን

ወንጀለኞችን ወደ ኒው ሳውስ ዌልስ ከመላክ ስታቆም፣ በ1852

ዓ.ም ወደ ታዝማኒያ እና በ1868 ዓ.ም ወደ ዌስተርን

አውስትራሊያ መላክ አቆመች።

ብዙ ጊዜ ህጻናት ከወንጀል ነጻ ስለሆኑ ታዲያ ቀስ በቀስ

በወንጀለኛና ሰፋሪዎች ያለሁ ልዩነት ቀስ በቀስ ጠፋ። ከ1850 ዎቹ

ዓመታት ጀምሮ የቅኝ ግዛቶች በራሳቸው ማስተዳደር በመጀመር

ተከባባሪ የሆነ ሕብረተሰብ እንደፈለጉ ነው። የቅኝ ግዛቶች ቀደም

ብሎ ስለነበራቸው ወንጀለኞች ማፈር ጀመሩና ስለዚህ ጉዳይ

መናገር አይፈልጉም። ከአንድ ምእተ ዓመታት በኋላ የዚህ ዓይነቱ

ሀፍረት ተቀየረ። አውስትራሊያኖች በወንጀለኞች አጀማመር

እንደሚኮሩና በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰዎች የወንጀለኛ ትውልድ

ዘራቸውን ለማወቅ እንደሚፈልጉ ነው።

ይህንን ኣስተሳሰብ በመቀበል፣ አውስትራሊያዊ የሆነ ስለ ቤተሰብ

ሀረግ መቁጠር ወይም ስላለፈ መጥፎ ፀባይ እስከዚህ አይጨነቁም።

ከሰዎች ጋር ስንገናኝ መንከባከብና በጥሩ ሁኔታ ሰዎች እንዲቀጥሉ

እድል መክፈት ነው።

ክፍል 5 – የአውስትራሊያችን ታሪክ 57
ከአውሮፓ ሰፈታ በኋላ የአገር ተወላጁ ህዝብ

በአውስትራሊያ ውስጥ የአውሮፓ ሰፋሪዎች መምጣት ሲጀምሩ

በግምት ከ750 000 እስከ 1.4 ሚሊዮን የሚሆን የአቦርጂንና

የቶረስ ስትሬት አይላንደር ህዝብ ነበር። ቁጥራቸው እስከ 250

ነብስወከፍ አገሮችንና ከ700 በላይ የቋንቋ ቡድኖችን ያካተተ

ነበር።

በአውስትራሊያ መጀመሪያ ሰፈራ ሲካሄድ በብሪቴን መንግሥትና

በአቦርጂናል ህዝብ መካከል ስምምነት አልተደረገም። የአገሬው

ተወላጅ ህዝብ የራሱ የሆነ ኢኮኖሚ እንዳለውና የጥንት

ግንኙነታቸው ከመሬት ጋር የተያያዘ ነው። መንግሥት ይህንን

ግምት ውስጥ ማስገባት አልቻለም ምክንያቱም በአውሮፓ ውስጥ

የዚህ ዓይነት እምነት ስልት ባለመኖሩ ነው። የአቦርጂናል ህዝብ

ሰብል አያበቅሉም ነበር ወይም እንደ ብሪቴን በአንድ ቦታ

ተረጋግቶ ለመኖር ቤት ስለማይሠሩ፤ ስለዚህ ባለንብረት ስለመሆን

ግድየለሽ እንደሆኑ ይገምታል። መንግሥት መሬቱን ከነሱ

ለመውሰድ የሚሰጋ ነገር የለውም።

አደገኛ ግጭት

ቀደም ሲል የነበረው ገዥ መደብ አቦርጅናልን ላለመጉዳት ይናገር

ነበር፣ ነገር ግን የብሪቴን ሰፋሪዎች አቦርጅናል በሚኖሩበት መሬት

ላይ በመግባት ለብዙ የአቦርጂናል ህዝብ ሞት ምክንያት ሆኗል።

ብዙ ጊዜ ሰፋሪዎች ይህንን ወንጀል ሲፈጽሙ አይቀጡም ነበር።

አንዳንድ የአቦርጅናል ሰዎችና የአውሮፓ ሰፋሪዎች ሰላማዊ በሆነ

አብረው መኖር ይችሉ ነበር። አንዳንድ ሰፋሪዎች በበግን ከብት

እርባታ ሥራ ለአቦርጂናል ይቀጥርራል። ገዢ ማኳሪ/Macquarie

ለአቦርጂናል ህጻናት የሚሆን ትምህርት ቤት ለማሠራት

የራሳቸውን የእርሻ መሬት ለአቦርጂናል አበርክተዋል። ስለዚህ

ጥቂት የአቦርጂናል ሰዎች እንደ ሰፋሪዎች አኗኗር ዘዴ ለመኖር

ይፈልጋሉ። የራሳቸውን ባህልና ልምድ ማጥፋት አይፈልጉም ነበር።

በመሬት ላይ አለመስማማት ጦርነት ምን ያህል የአቦርጂናል

ሰዎች እንደሞቱ አናውቅም፣ ስለዚህ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ

አቦርጂናል እንደተገደሉ ነው። ለአብዛኛው የአቦርጂናል ሞት

መንስሄ በሽታዎች እንደነበሩና እነዚህም በአውሮፓኖች ወደ አገሪቷ

የገቡ በሽታዎች ናቸው። የአቦርጅናል ሕይወት ማለፍ ከፍተኛ ኪሳራ

ነበር። በ1830ዎቹ በቪክቶሪያ ውስጥ የአቦርጂናል ህዝብ ብዛት

ወደ 10 000 ህዝብ ነበር። በ1853 ዓ.ም ውስጥ የአቦርጂናል

ህዝብ ሲቆጠር 1907 ብቻ ነበር።

ታሪካዊ ድርጊቶች

በአገር ውስጥ ጥናት

መጀመሪያ ቅኝ ገዝዎች በኒው ሳውዝ ዌልስ ውስጥ ከባድ ችግር

አጋጥሟቸዋል። በአውስትራሊያ በጣም ጥቂት መሬት ነው ለም

አፈር። አቦርጂናሎች በዚህ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለማስተናገድ

ተምረዋል እንዲሁም በድርቅ ወቅት በጣም ተሰቃይተዋል።

በስይድነይ ሰፋሪዎች ካጋጠማቸው የመጀመሪያ ችግር በ50 ኪ.ሜት

ርቀት ያለን ተራራማ መሬት ወደ ምዕራብ ስይድነይ የሚወስደውን

ብሉ ማውንቴንስ/Blue Mountains ማግኘት ነበር። በ1813

ዓ.ም ሶስት ወንዶች፣ ማለት ብላክስላንድ/Blaxland፣ ወንትዎርዝ/

Wentworth እና ላውሶን/Lawson የተባሉት መጨረሻ ላይ

ተራራዎችን አቋረጡ። በBlue Mountains ማዶ የነበረው

አሁንም መስመሩን የተከተለ መኪና መንገድና ባቡር ሀዲድ

ይገኛል።

በነዚህ ተራራዎች ማዶ ላይ ተማራማሪዎች ለበግና ከብት ማርቢያ

የሚሆን ጥሩ ስክፍት የሆነ የገጠር መሬት እንዳገኙ ነው። ከዚያ

ቀጥሎ የደረሱበት መሬት ደረቅ፣ በርሀማ የገጠር ቦታ ነበር።

ለመኖር ውሀ ማግኘት እንደተቸገሩና በቂ የሆነ ምግብ መሸከም

እንዳልቻሉ ነው። የጀርመን ተወላጅ የሆኑት ተመራማሪ፣ ሉድዊግ

ሌችሀርድት/Ludwig Leichhardt, በ1848 ዓ.ም ከምሥራቅ

ወደ ምእራብ ያለውን አህጉር ለማቋረጥ ሲሞክሩ ጠፍተዋል።

በ1860 ዓ.ም ቡርክ/Burke እና ዊልስ/Wills ከመልበርን

ተነስተው ከደቡብ ወደ ሰሜን አውስትራሊያ ለማቋረጥ እቅድ

አወጡ። ብዙ የጉዞ ቡድኖችን እንደመሩ ሲሆን ነገር ግን

ለማቋረጥ በጣም እንደተቸገሩ ነው። ቡርክ/Burke እና ዊልስ/

Wills የጫካ ኑሮ ልምድስ አልነበሩም። ከአቦርጂናል

ያንድሩዋንድሃ/Yandruwandha ሰዎች የኤክስፐርት እርዳታ

አግንተዋል ነገር ግን ሁለቱም ተማራማሪዎች ሲመለሱ በመንገድ

ላይ ሞተዋል። ምንም እንኳን ቡርክ/Burke እና ዊልስ/Wills

የጉዟቸው ሁኔታ ባይጠናቀቅም ታሪካቸው በስነ-ጥበብና ጽሁፍ

ሲታወስ ይኖራል። የመሬታችን አስቸጋሪነት በዚህ አሳዛኝ ምሳሌ

ይታወቃል።

ቡርክ/Burke እና ዊልስ/Wills በአውስትራሊያ ዙሪያ የአሰሳ ጉዞ፣ 1860 ዓ.ም

58

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
ሰፋሪዎችና አቅኝዎች

ምንም እንኳን ሰፋሪዎች ጥሩ መሬት ቢኖራቸውም ኑሮ በጣም

አስቸጋሪ ነበር። ከድርቅና ጎርፍ ማእበል ጊዜ በኋላ ብዙጊዜ

ገበሬዎች እንደገና ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ። በ1838 ዓ.ም

የአውስትራሊያ ዋና ኤክስፓርት ወደ ውጭ የሚላክ ምርት ሱፍ

ሲሆን ድርቅ ከመጣ ወይም የሱፍ ዋጋ በውጭ አገር ከረከሰ

ስለዚህ በሰፋሪዎች የኑሮ ሁኔታ ላይ ችግር ይፈጥራል። ስለዚህ

ሰዎች እራሳቸው የመረጡት ሲሆን እራሳቸው ይታገሉበት። በዚህ

ዓይነት ችግር ለነበረ ሰው ‘አውዚ ታጋይ/Aussie battler’ የሚል

ስም ተሰጥቶታል። ‘አውዚ ታጋይ/Aussie battler’ ምሳሌነቱ

ለአውስትራሊዊ ታጋይነትና ማገገምን ያሳያል። ወንድና ሴት

አቅኝዎች በችግር ጊዜ ስለነበራቸው አበረታች ሥራቸው ይከበራሉ።

ወንዶች ርቀው በሚሄዱበት ጊዜ ወይንም ሲሞቱ ሴቶች የንግድ

ሥራውን ወይም እርሻውን ያካሂዳሉ።

የወርቅ ቆፋሪ ፈቃድ ለማውጣት በሚደረከው ክፍያ ላይ

የመንግሥት ወታደሮች በጣም ችግር ይፈጥሩባቸዋል። ህዳር/

November 11 ቀን 1854 ዓ.ም 10 000 ለሚሆን ህዝብ

መሰረታዊ የዲሞክራቲክ መብታቸውን እንዲያውቁ በባከርይ ሂል፣

ባላራት/Bakery Hill, Ballarat ላይ ተሰብስበዋል። ያለምንም

የፈቃድ ማውጫ ኪሳራ ወርቅ ለማውጣት መቆፈር እንደሚፈልጉ

ነው። በተጨማሪም በቪክቶሪያ ፓርሊያመንት ውስጥ እነሱን

መወከል የሚችል ሰው መምረት እንደፈለጉ ነው።

በኢረካ/Eureka ቁፋሮ ላይ በትንሽ ቡድን መሰባሰብ ተቃውሞ

በመፍጠር የተቃውሞ ባንዴራቸውን ሳውዘርን ክሮስ ላይ

አውለበለቡ። እነዚህን ተቃዋሚ ሀይሎች ለመዋጋት ታህሳስ/

December 3 ቀን 1854 ዓ.ም ጥዋት የመንገሥት

ባለሥልጣኖች ወታደሮችን ላኩ። ወዲያውኑ የወርቅ ቆፋሪዎች

ሀይላቸው ሲዳከም 30 የሚሆኑ ሞተዋል።

በነዚህ የመጀመሪያ አስቸጋሪ ዓመታት የአውስትራሊያ ጓደኝነት

የመቀራረብ መንፈስ ተጀመረ። ከከተማ ሩቅ፣ አብሮ ተሰባስቦ

በሚጓዙ ወንዶች መካከል መቀራረቡ በጣም የጠበቀ ሆነ።

እንዲሁም ሰፋሪዎች ከችግራቸው ለመላቀቅ ይረዳዳሉ።

በአውስትራሊያ ኑሮ አሁንም ይህ ባህል በጣም የተመደ ነው፤

ለምሳሌ፡ በየዓመቱ ለሚከሰተው የጫካ እሳትን ለማጥፋት በሺ

የሚቆጠሩ ፈቃደኛ ሰዎች ይዘምታሉ።

የወርቅ ቁፋሮ ጥድፊያ

በመጀመሪያ 1851 ዓ.ም በኒው ሳውዝ ዌልስ ወርቅ መገኘት እንደ

አገሪቷን የሚቀይር ግኝት ተደርጎ ተገለጸ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወርቅ

በቪክቶሪያ ውስጥ ስለተገኘ አዲስ እራሷን የቻለች ቅኝ ግዛት ሆነች።

በ1852 ዓ.ም መጨረሻ ላይ 90 000 የሚሆኑ ሰዎች ከሞላው

አውስትራሊያ እና ከሞላው ዓለም ወርቅ ፍለጋ ወደ ቪክቶሪያ ተጓዙ።

የኢረካ ባንዴራ/Eureka flag

በከፍተኛ ወንጀል የተቃዋሚ መሪዎች ለፍርድ ቀረቡ ይሁን እንጂ

የሚቀጡት በዳኞች ስብስብ በኩል አይደለም። የመንግሥት ጥፋት

ስለመሆኑ በሮያል ኮሚሽን በኩል ስለተጣራ የብዙዎች ማእድን

አውጭ ፍላጎት ተሟላ። እንዲሁም ለፖለቲካዊ ውክልና ለማግኘት

እንደ ፍላጎታቸው ተፈቀደ። በአንድ ዓመት ውስጥ ፐተር ላሎር/

Peter Lalor፣ የተቃዋሚ መሪ በቪክቶሪያ ፓርሊያመንት አባል

ሆኑ።

ከዓመታት በኋላ የኢረካ ተቃዋሚ እንደ ምሳሌ በመሆን እኛ

በአግባብ ለመጓዝ እምነት እሳደረልን።

ወርቅ የተገኘው በቅኝ ግዛቶች ማለት ኒው ሳውዝ ዌልስና ቪክቶሪያ በ1851 ዓ.ም

እንደነበር ነው

የኢረካ ተቃዋሚ/Eureka rebellion በአውስትራሊያ ታሪክ

ውስጥ ታላቅ የዲሞክራቲክ ንቅናቄ ስላሳየ ሲታወስ ይኖራል።

በ1854 ዓ.ም በባላራት/Ballarat የወርቅ ማውጫ ቦታ ላይ

በወርቅ ቆፋሪዎች አማካኝነት ስለ ወርቅ ማውጫ መጥፎ አያያዝ

በመንግሥት ባለሥልጣኖች ላይ ታላቅ የተቃውሞ ድምጽ

አካሂደዋል።

የወርቅ አወጣጥ ጥድፊያ የአውስትራሊያ በብዙ መንገድ

ቀይሯታል። በወርቅ አወጣጥ ጥድፊያ ዓመታት የአውስትራሊያ

ጠቅላላ ህዝብ ብዛት ጨምሯል ይህም በ1851 ዓ.ም ከ43 000

እንደነበርና ከዚያም በ1870 ዓ.ም ወደ 1.7 ሚሎዮን ሆኗል።

በ1850 ዎቹ ዓመታት እያደገ የመጣውን ህዝብ ለማገናኘት

የመጀመሪያ ባቡር ሀዲድና ተሌግራፍ ተመሰረተ።

ከሳውዝ አውስትራሊያ በስተቀር በሞላው የቅኝ ግዛቶች ውስጥ

ብዛት ያለው የወርቅ ክምችት ተገኘ። ኢኮኖሚ እያደገ በመምጣቱ

በውጭ የሚላክ ምርት ኤክስፖርት ላይ ወርቅ የሱፍን ቦታ

በመውሰድ በጣሚ ጠቃሚ የኤክስፖርት እቃችን ሆነ። በ1890

ዓ.ም ገደማ አውስትራሊያ በዓለም ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ

እንደሚኖራት ይገመታል።

ክፍል 5 – የአውስትራሊያችን ታሪክ 59
ያለፈቃድ መሬት ተጠቃሚዎችና ገበሬዎች

ከቅኝ ግዛቶች የመጀመሪያ ቀናት ጀምሮ ሰዎች ‘ያለፈቃድ

ተጠቃሚ/squatters’ በሚል ሲታወቁ እነሱም ስፋት ያለውን

መሬት ወስደው ለእርሻ ያውሉታል። ምንም እንኳን ለዚህ መሬት

ባይከፍሉበትም ግን ያለፈቃድ የወሰዱት መሬት እንደራሳቸው

ይቆጠራል። የመጀመሪያው የወርቅ ፍለጋ ጥድፊያ ሲያበቃ ታዲያ

እነዚህን ያለፈቃድ የተወሰዱ መሬቶች ለመመለስ ከፍተኛ ትግል

ነበር።

በ1860 ዎቹ ዓመታት እነዚህ ያለፈቃድ ጥቅም ላይ ያሉትን

መሪቶች መንግሥት በእርሻ ለሚሠሩ ወንዶችና ቤተሰባቸው ለመሽጥ

ፈለገ። ያለ ፈቃድ ተጠቃሚዎች መሬቱን በተቻለ መጠን ለመያዝን

በተለይ በጥሩ አካባቢ ያሉትን የኩንትራት ውል ጥያቄ በብዛት

ላማስገባት ይሞክሩ ነበር።

ከ1860 ዎቹ አመታት ጀምሮ ሰዎች ከኢራን፣ ግብጽና ቱርክ

በአውስትራሊያ ገጠር አካባቢ በግመል ‘ባቡሮች/trains’ ሥራ

እንዲሰማሩ መጥተዋል። ከህንዳውያን ግመል/cameleers

ተከታዮች ጋር ‘የአፍጋንን/Afghans’ በጣም ይመሳሰላሉ

ምክንያቱም ተመሳሳይ ልብስና የጋራ ሃይማኖት እስልምና እምነት

ስላላቸው ነው። እነዚህ cameleers እንደ ‘የአገር ውስጥ

ፈር ቀዳጅ ሰፋሪ’ ይባሉ ነበር። እስከ 4000 ህንዶችና 6000

የፓሲፊክ አይላንደርስ/Pacific Islanders ሲሆኑ እነሱም

በኩውንስላንድ ባሉ የስኳርና ሙዝ ፋብሪካዎች ውስጥ ይሰራሉ።

ከ1880 ዎቹ አመታት ጀምሮ ሰዎች ከለባቦን አገር ለሥራ

አውስትራሊያ ገብተዋል። ብዙዎቹ ሊባኖን በጨርቃጨርቅና

ልብስ ኢንዱስትሪዎች እንደገቡ ነው። የሊባኖን ቤተሰብ ሲመጡ

በአውስትራሊያ አገር የጨርቃጨርቅ ንግዶችን ለመያዝ ስለነበር

ዛሬም ባህልና ልምዳቸው እንደቀጠለ ነው።

የባቡር ሀዲድ እስኪዘረጋ ድረስ አዲስ የሆኑ ገበሬዎች ችግር

እንዳጋጠማቸውና ይህም ለገብያ ስለራቃቸው ነው። በከተማ ውስጥ

ከፍተኛ ደመወዝ የማግኘት እድል ሁልጊዜ ለትንሽ ገቢ ሲባል

በመሬት ላይ መሥራቱ የኑሮን ፍላጎት እንደማይስብ ነው።

በሳውዝ አውስትራሊያ ገበሬዎች ደህና እንደሆኑና ዘመናዊ የሆኑ

መሳሪያዎች የእርሻ ሥራን በቀላሉ ለመወጣት እዚህ ተጀሟሯል።

stump-jump plough (1870s) በተባለ ማረሻ መሳሪያ

ውሽንፍር ያለን መሬት ለሰብል እርሻ በቀላሉ ማዘጋጀት ይቻላል።

ማይግሬሽን በ1800 ዎቹ ዓመታት

በ1800 ዎቹ መጀመሪያ የእንግሊዝ፣ ስኮቲሽ፣ ወልሽ እና አይሪሽ

ሰፋሪዎች በቅኝ ግዛቶች ላይ ዋናዎቹ የሰፋሪ ቡድኖች ነበሩ። አዲስ

አገርን መመስረት የነሱ ቅርስ እንደነበረ ነው። በአውስትራሊያ

ያለፉ ጊዚያት፣ ባህላዊ እንቅስቃሴና ሃይማኖት መከተል ከዩናይትድ

ኪንግዶም/United Kingdom ካለው ጋር ተመሳሳይ ነበር። ይሁን

እንጂ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ የአውሮፓና ኤሽያ ሰፋሪ ቡድኖች

እንደነበሩ ነው። በ1800 ዎቹ ዓመታት ከአውሮፓ የመጡ ማለት

ጣሊያን፣ ግሪክ፣ ፖለስ፣ ማልተስንና ራሺያኖችን እንዲሁም

የፍረንችን ሰፋሪዎች ያካተተ በወይን ኢንዱስትሪ ውስጥ ይሠራሉ።

እነዚህም በአብዛኛው ወጣት ወንዶች ሥራ ፈላጊዎች ነበሩ ወይንም

ከመርከቦቻቸው የጠፉትን ነበር።

የቻይና ማይግራንትስ ወደ አውስትራሊያ መግባት የጀመሩት

ከ1842 ዓ.ም በኋላ ነው። የወርቅ ማእድን ከተገኘ በኋላ የቻይና

ቁጥር እንዳደገና በወርቅ ማምረቻ ቦታዎች ላይ የዘር ልዩነት

ጫና እንደነበረ ነው። አንዳንዴ ይህ በቻይናውያን ላይ አመጽ

እንዲፈጠር ሲደረግ እንደ በ1854 ዓ.ም በበንዲጎ/Bendigo

የተፈጸሙት አመጽ ይሆናል። የዘር ልዩነት ጫና የመጣው በ1855

ዓ.ም በቪክቶሪያ እና በ1861 ዓ.ም በኒው ሳውዝ ዌልስ በተደረገ

የመጀመሪያ የኢሚግሬሽን እቀባ ምክንያት ነው።

በ1850 ዎቹ ከወርቅ ማውጣት ጥድፊያ በኋላ አብዛኞቹ ቻይናውያን

ወደ አገራቸው ተመለሱ። ከቀሩት ቻይናውያን ውስጥ የቻይና ገበያ

አትክልተኞች ሲሆኑ ውሀ እጥረት ባለበት አካባቢ የሚፈለጉ ትኩስ

ፍራፍሬና አትክልቶችን ያቀርቡ እንደነበር ነው።

በአውስትራሊያ ውስጥ ‘አፍጋን/Afghan’ cameleers

ለአቦርጅናል የተጠበቀ

ስለመሬት መያዝ ጉዳይ በአቦርጂናልና ሰፋሪዎች መካከል የነበረው

ጦርነት ካለቀ በኋላ የአቦርጂናል ህዝብ ከሕብረተሰቡ ራቅ ብለው

ይኖራሉ። አንዳንዶቹ ከከተማ የራቀ የበግና የከብት እርባታ ጣቢያ

በጣም አነስተኛ በሆነ ደመወዝ ሠርተዋል። የቅኝ ገዥ መንግሥታት

ለአቦርጂናል መኖሪያ ብቻ የሚሆን ቦታ ሲመድቡ፤ ነገር ግን

እነዚህ አካባቢዎች አቦርጂናል የራሳቸውን ባህላዊ ኑሮ ለመከተል

አይፈቅዱም። እንደፈለጉት ማደንና መሰባሰብ አልቻሉም።

በ1800 ዎቹ መጨረሻ ላይ የአቦርጂናል መብቶች በቅኝ ገዥው

መንግሥት ተነጠቀ። የአቦርጂናል ህዝብ የት ቦታ ላይ መኖር

እንዳለባቸው ነገሯቸው። ማንን ማግባት እንደሚችሉ ነገሯቸው፣

እንዲሁም ብዙ የአቦርጂናል ህጻናት ከወላጆቻቸው ነጥቀው ወሰዱ።

እነዚህ ህጻናት ወደ ‘ነጭ/ፈረንጅ’ ቤተሰቦች ወይም መንግሥታዊ

ጉድፍቻ አሳዳጊ ድርጅቶች ተላኩ። እነዚህ ተግባራት ለረጅም ጊዜ

ባይቆዩም ነገር ግን በአቦርጅናል እና በብዙ አውስትራሊያን ለጥልቅ

ሀዘኔታ ምክንያት ሆኗል።

60

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
ለምርጫ መብት/Suffrage

‘ለምርጫ መብት/Suffragettes’ ይህ አባባል የሚጠቅመው በዓለም

ዙሪያ ላሉ ሴቶችና በህዝብ ምርጫ ዘመቻ ላይ ድምጽ የመስጠት

መብታቸውን ለማስከበር ነው። በ1880 ዎቹ እና 1890 ዎቹ ወቅት

እያንዳንዱ ቅኝ ግዛት ቢያንስ አንድ ሕብረተሰብ የራሱ የሆነ

የምርጫ መብት ይኖረዋል። በቅኝ ገዥዎቻቸው ፓርሊያመንት

ላይ እነሱን ለመወከል በሺዎች የሚቆጠሩ ፊርማዎችን በማሰባሰብ

የምርጫ መብትን ማስከበር ይሆናል።

በሳውዝ አውስትራሊያ የሚገኙ ሴቶች ለድምጽ መስጠት መብት

እንዳሸነፉና በ1895 ዓ.ም ለፓርሊያመንት ምርጫና ድምጽ

መስጠት መብት አገኙ። በዌስተርን አውስትራሊያ ውስጥ ያሉ

ሴቶች በ1899 ዓ.ም በምርጫ የድምጽ መስጠት መብት አገኙ።

በ1902 ዓ.ም ውስጥ ሴቶች በአውስትራሊያ ፓርሊያመንት

ለመምረጥና ለመመረጥ መብት በመስጠት አውስትራሊያ የመጀመሪያ

አገር ነች። የአገሬው ተወላጅ ሴቶች (እና ወንዶች) እስከ 1962

ዓ.ም ድረስ የመምረጥና የመመረጥ መብት አልተሰጣቸውም።

ኢዲት ኮዋን/Edith Cowan በ1923 ዓ.ም በዌስተርን

አውስትራሊያ ፓርሊያመንት እንደተመረጡና የመጀመሪያዋ

የፓርሊያመንት ሴት ሆኑ። ከዚያም በ1943 ዓ.ም ኢኒድ ልዮንስ/

Enid Lyons፣ እስከተመረጡ ድረስ የሴት አውስትራሊያዊት

ፓርሊያመንት አልተመረጠም።

በራሱ አስተዳደር የሚመራ/ፈደሬሽን

የቅኝ ግዛቶች እድገት በተናጠል እንደነበረና በ19ኛው ምእተ ዓመት

መጨረሻ ላይ በብሄራዊ ንብረት ላይ የጋራ ስሜት ተፈጠረ። ይህ

ስሜት ‘በደህና ለአውስትራሊያ እድገት/Advance Australia

Fair’ በሚለው መዝሙር ላይ ተገልጿል። ይህ መዝሙር በፐተር

ዶድስ ማኮርሚክ/Peter Dodds McCormick እንደተጻፈና

በ1878 ዓ.ም በስይድነይ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘምሯል።

በአሁን ጊዜ የብሄራዊ መዝሙራችን ነው።

በ19ኛው ምእተ ዓመት መጨረሻ ላይ የቅኝ ግዛቶችን ለማጣመር

ሁለት ሙከራዎች ተደርጎ ነበር። በ1889 ዓ.ም ሰር ሀንርይ

ፓርከስ/Sir Henry Parkes የተባሉት ጠንካራ አዲስ አገርና

መንግሥትን ለመመስረት ጥሪ አቅርበዋል። ስለ አውስትራሊያ

ፌደራዊ ማእከላዊ አስተዳደር ሃሳብ ለመወያየት ሲባል በ1890

ዓ.ም የአውስትራሊያ ፌደሬሽን ኮንፈረስ ስብሰባ ተካሂዷል።

ከጥቂት መጓተት በኋላ በ1893 ዓ.ም ላይ ስለ ፌደሬሽ የሚደረግ

ስብሰባ ተፋጠነ። ለሚቀጥለው ህገ መንግሥት ስብሰባ አባላት

በመራጮች ፍላጎት ይሆናል። ህገ መንግሥቱን ለማጽደቅ መራጮች

በሁለት ህዝባዊ ውሳኔ ላይ ድምጽ ይሰጣሉ። የህዝባዊ ውሳኔ አሰጣጥ

እውነታዊ አሰራር በህዝቡ ፍላጎት የተመሰረተ መሆኑ የሚያሳየው

ምን ያህል አውስትራሊያ እንደተሻሻለች ነው።

ካተሪን ስፐንስ/Catherine Spence

(1825 – 1910)

ካትሪን ስፐንስ/Catherine

Spence የተባሉት ጸሀፊ፣

ሰባኪ፣ ለሴቶች እኩልነት

ተከራካሪና ለምርጫ መብት

ተከራካሪ ሴት ነበሩ።

ካትሪን ስፐንስ/Catherine

Spence ወደ አውስትራሊያ

የመጡት ከስኮትላንድ አገር

ነው። ስለ ኑሮ በአውስትራሊያ

‘prizewinning novels’

በሚል አርእስት እንዲሁም

ለትምህርት ቤት መጽሐፍትን

ጽፈዋል።

የመጠለያ ቤት ለሌላቸው ህጻናትና አዲስ የመዋለ ህጻናት መርጃ

ድርጅት እንዲቋቋም እንዲሁም ለልጃገረዶች የመንግሥት ሁለተኛ

ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲከፈት እረድተዋል።

በፓርሊያመንት ለመጀመሪያ ጊዜ ምርጫ የቆሙ ሴት እንደሆኑና

ብዙ የምርጫ ድምጽ እንዳገኙ ሲሆን ነገር ግን ለፓርሊያመንት

መቀመጫ ወንበር አላሸነፉም። በ1891 ዓ.ም የሳውዝ አውስትራሊያ

ሴቶች ምርጫ መብት አስከባሪ ምክትል ፕሬዚደንት ሆኑ።

በችግር ጊዜም ቢሆን ሴቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለማሳየት

ካትሪን ስፐንስ/Catherine Spence ጥሩ ምሳሌ ናቸው።

በብሪስባን ውስጥ የፌደሬሽን ቀን፡ 1901 ዓ.ም

ክፍል 5 – የአውስትራሊያችን ታሪክ 61
አውስትራሊያ በራሷ አገዛዝ መመራት እንደምትችል የብሪቲሽ

መንግሥት በመስማማቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውስትራሊያ

መንግሥት፣ ጥር/January 1 ቀን 1901 ዓ.ም በስይድነይ

ሰንተኒያል ፓርክ/Sydney’s Centennial Park ቦታ በተሰበሰበ

ህዝብ ፊት ቃለ መሀላ አደረገ። የመጀመሪያ የአሀሪቷ ጠቅላይ

ሚኒስተር ኢድሙንድ ባርቶን/Edmund Barton ሲሆኑ በኒው

ሳውዝ ዌልስ ውስጥ የፌደራዊ ማእከላዊ አስተዳድርን መርተዋል።

አሁን አውስትራሊያ አገር ብትሆንም ነገር ግን በብሪቲሽ ንጉሳዊ

አገዛዝ ስር ናት። በመከላከያና የውጭ አገር ጉዳይ በተመለከተ

አውስትራሊያ እስከ 1931 ዓ.ም ሙሉ ስልጣን አላገኘችም።

ምንም እንኳን የብሄራዊ አንድነት ፍላጎት ቢዳብርም፣ ነገር ግን

አሁንም የብሪቲሽነት ፍላጎት የጠነከረ ነው።

የወዛደሩ ፓርቲ/Labor Party ሲያድግ፣ በ1910 ዓ.ም ሌሎች

ፓርቲዎች በመጣመር የሊብራል ፓርቲን/Liberal Party

መሰረቱ። ይህ ፓርቲ ብዙ ስሞች ነበሩት። ጦርነት ጊዚያት

የብሄራዊ ፓርቲ/Nationalist Party ከዚያም የተባበሩት

አውስትራሊያ ፓርቲ/United Australia Party ተባለ። በ1944

ዓ.ም የዛሬው ሊብራል ፓርቲ/Liberal Party ተመሰረተ። ከዚህ

በመቀጠል ብዙ የሠራተኛ ያልሆኑ ፓርቲዎች የተሳተፉበት ስብሰባ

በሮበርት መንሲስ/Robert Menzies ተካሄደ። ሰር ሮበርት/

Sir Robert Menzies በአውስትራሊያ ለረጅም ጊዜ በጠቅላይ

ሚኒስተርነት አገልግለዋል።

ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የገበሬዎችን ችግር ለመቅረፍ

የገጠር ፓርቲ/Country Party ተመሰረተ። ዛሬ ብሄራዊ ዜጎች/

Nationals ሲባል ይህም ብዙጊዜ ከሊብራል ፓርቲ ጋር

ለመቀናጀት ይንቀሳቀሳል።

የኢሚግሬሽን እቀባ ገደብ አንቀጽ ህግ 1901

ዓ.ም

ታህሳስ/December 1901 ዓ.ም የኢሚግሬሽን እቀባ ገደብ

አንቀጽ ህግ 1901 ሲተላለፍ ‘የነጭ አውስትራሊያ/White

Australia’ ፖሊሲ ወደ ህግ ተለወጠ። ይህ ማይግራንት/መጤዎች

በአውስትራሊያ ውስጥ እንዳይሠሩ ያግዳል እንዲሁም ‘ነጭ

ያልሆኑ’ ሰዎች እንዳይመጡ ያግዳል።

አውሮፓውያን ያልሆነ ማንኛውም ሰው 50 ቃላት በወያዘ ፈተና

በአውሮፓውያን ቋንቋ መውሰድ አለበት። የቻይና ንግድ ምክር

ቤት አባላት የሆኑት አንጋፋ የህግ ጠበቃ William Ah Ket

እና የቻይና ነጋዴዎች ህዝባዊ አመጽ ሲያካሂዱ፣ ነገር ግን ህጉን

ስለመቀየር ጥሩ ውጤት አላስገኙም።

ሰር እድሙንድ ባርቶን/Sir Edmund Barton

የፓለቲካ ፓቲዎች መፈጠር

በ1880 ዎቹ ዓመታት በአውስትራሊያ ውስጥ ጠንካራ የንግድ

ማሕበራት በሠራተኞች ተመሰረተ። በከባድ ኢኮኖሚ ውጥረትና

በድርቅ ችግር ጊዜ፤ የሠራተኛን ደመወዝና ሁኔታ ለመከላከል

ሲባል ማሕበራት አድማ ያካሂዳሉ። ከዚያም ሠራተኞች ወደ

ፖለቲካ ተቀይሯል። በ1891 ዓ.ም የወዛደሩ ፓርቲን/Labor

Party መሰረቱ።

የወዛደር ፓርቲ ቀዳሚ ተግባሩ የሠራተኛን ደመወዝና ሁኔታ

ማስመለስና ለማሻሻል ነበር። በማሀከለኛ መደብ ያሉት ሰዎች

ከወዛደር ሠራተኛው የተሻለ ይኖራል፤ ይሁን እንጂ የሠራተኛውን

ሁኔታ ይረዱት ነበር። ደመወዝና በማስተካከል አድማን ለለማቆም

ህጋዊ ቦርድ ተመሰረተ። በ1907 ዓ.ም በኮመንዌልዝ ማረጋጊያ

ፍርድ ቤት እና ሽምግልና በኩል አነስተኛ ደመወዝ በሥራ ደረጃ

ሲወስኑ፣ ታዲያ ሚስትና ሶስት ልጆቹ በቁጠባ ተደስተው መኖር

ይችላሉ።

የቻይና፣ ህንድ፣ ፓስፊክ አይላንደርስ እና ከሚድል ኢስት የመጡት

ሰዎች በአዲሱ ፌደራዊ አውስትራሊያ ከደቡባዊ ኢሮፕ በመጡ

ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ማይግራንትስ ቢተኩም ነገር ግን የነሱ

ባህላዊ አስተዋጽኦ ለአውስትራሊያ ማሕበራዊ ማንነት አንዱ ክፍል

ይሆናል።

በዓለም የአንደኛ ጦርነት/World War I,

1914 - 1918

በሰፋሪዎችና በአቦርጂናል መካከል ከተደረገ ጥቂት ጦርነቶች

በስተቀር አውስትራሊያ ሰላማዊ አገር እንደነበረች ነው።

በአውስትራሊያ የእርስ በርስ ጦርነቶች እና አብዮች የሚባል

ነገር አልነበረም። የመጀመሪያ ሰፋሪዎች ለብሪቲሽ ንግሥት በጣም

ታማኝና ታዛዥ እንደነበሩ ነው።

62

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
ይሁን እንጂ አውሮፓ ጦሯን ወደ ኤሽያ ማስፈር ሲጠጋ

ለአውስትራሊያ እንደምትጋለጥ ሰጋች፣ በተለይ ጃፓን ታላቋ ሀያል

ከሆነች በኋላ። አውስትራሊያ በብሪቲሽ ንግሥት የተመካችና እኛን

ለመከላከል ጠንካራ የሆነ ባህር ሀይል ስላላት ነው። የብሪቲሽ

ንጉሳዊ አገዛዝ ጠንካራ እንዲሆንና እኛን ለመከላከል ሲባል

አውስትራሊያ በሁለቱም ጦርነቶች ተዋግታለች።

በ1915 ዓ.ም የአውስትራሊያ ሠራዊት በአንደኛ ዓለም ጦርነት

ላይ በተፈጠረ ጥቃት ለመከላከል ከተባበሩ የጀርመንና ቱርከይ ጋር

ተዋግተዋል። የአውስትራሊያና ኒው ዚላንድ ክፍለ ቦታ የሆነውን

ጋሊፖሊ ፐኒሱላ/Gallipoli Peninsula ለማጥቃት ስለተሞከረ።

በስህተት የባህር ጠረፍ ቦታ ላይ ስለተቀመጡ የቱርክ ወታደሮች

በሚተኩሱባቸው ጊዜ በገደል ኮረብታ ላይ መውጣት አለባቸው።

ለማንኛውም ድንጋያማ የሆነን ተራራ በመያዝ ሲቆፍሩ ብዙ

ወጣት ወንዶች ሞተዋል። በAnzacs የወኔ መንፈስ ላይ

አውስትራሊያኖች ለአገራቸው በጣም ይኮራሉ።

ወደ ጋሊፖሊ የተደረሰበት ቀን (ሚያዚያ/April 25) ብሄራዊ

በዓል ነው። ይህ ለአውስትራሊያና ኒውዚላንድ የጦር ብርጌዶች

መታሰቢያ አንዛክ ቀን/Anzac Day ይባላል።

ጋሊፖሊ/Gallipoli ጦርነት በኋላ የአውስትራሊያ ሀይል

በምእራባዊ ፍራንስ ጦር ግንባር ተዋግታለች። በዚህ ጊዜ

‘ቆፍሪዎች/diggers’ የሚል ስም ተሰጣቸው ምክንያቱም ብዙውን

ጊዜ ያሳለፉት በመቆፈርና የምሽግ ቦታን በማስተካከል ስለነበር።

ከጀርመን ጋር በተደረገው የመጨረሻ ጦርነት ላይ የአውስትራሊያ

ቆፋሪዎች እንዳሸነፉና ይህም በክቡር ኮማንደር ጀኔራል ጆን

ሞናሽ/General John Monash መሪነት ነው።

እንዲሁም የአውስትራሊያ ሴቶና ወንዶች በመካከለኛ ምስራቅ

በማገልገል ሱዝ ካናል/Suez Canal ሲናይ ፐኒንሱላ/Sinai

Peninsula የተባበረ ወረራ ጊዜ ለመከላከል ተሳታፊ ሆነዋል።

ሲምፕሶን/Simpson እና አህዮቹ –

John Simpson Kirkpatrick

(1892 – 1915)

ጆን ሲምፕሶም ኪርክፓትሪክ/

John Simpson

Kirkpatrick የአገልግሎት

ሰራተኛ እንደነበሩና

በአውስትራሊያ ታዋቂ ሰው

ናቸው።

ፕራይቬት ጆን ሲምፕሶም

በጋሊፖሊ ውስጥ በአምቡላንስ

ህክምና ቡድን እንደ ቃሬዛ

ተሸካሚ ሆነው አገልግለዋል።

በኮረብታና ሸለቆ የቃሬዛ

አልጋን መሸከም በጣም ከባድ

ነበር። የቆሰለን የሰራዊት አባል አጓጉዙ ለማዳን ሲሉ ከጦሩ ትእዛዝ

ውጭ ዱፍይ/Duffy የተባለ አህያ ተጠቅመዋል።

ቀንም ሆነ ለሊት በየሰዓቱ በጦርነት ቦታና ባህር ዳርቻ ባለ ካምፕ

ሲጓዙ የሕይወት አደጋ እንደሚከሰት ነው።

በሚያዚያ/April 25 ቀን 1915 ዓ.ም ፕራይቬት ጆን ሲምፕሶም/

Private John Simpson ወደ ጋሊፖሊ/Gallipoli ደረሱ።

ከገቡ በአራት ቀናቸው በጠላት ማሽን ገን ጠበንጃ ተገደሉ። በባህር

ዳርቻ ካምፕ ለአገልግሎት ሰራተኛ አሳዛኝ ሁኔታ ጸሎት በዱፍይ/

Duffy ስም ሲደረግ አሁንም በጉዳተኛ ወታደር ሩጫ በባህር

ዳርቻው ያለ ወጣት አጃቢ ይደረጋል።

በአንደኛ ዓለም ጦርነት ጊዜ ጋሊፖሊ ፐንሱላ/Gallipoli Peninsulas

ክፍል 5 – የአውስትራሊያችን ታሪክ 63
የአንዛክ/Anzac አፈታሪክ

የአውስትራሊያና ኒው ዚላንድ ጦር ብርጌድ (ANZAC) ሚያዚያ/April 25 ቀን 1915 ዓ.ም ቱርክ ውስጥ ወደ ጋሊፖሊ ፐኒሱላ/

Gallipoli Peninsula አረፈ የሚለው የ(ANZAC) ልምዳዊ አባባል የውሽት ነበር።

ይህም የሚያመለክተው ለስምንት ወራት የፈጀ ዘመቻ እንደተደረገና በዚህ ረብሻ ላይ 25 000 የሚሆኑ አውስትራሊያን ንደተጎዱ ከዚህ

ውስጥ 8700 የሚሆኑት በቁስል ወይም በሽታ እንደተገደሉና እንደሞቱ ነው። በጋሊፖሊ ፐኒሱላ/Gallipoli Peninsula ላገለገሉ ጀግኖችና

የመንፈስ አፈታሪክን ለማስተካከል ሲባል ‘አንዛክ Anzac’ የአውስትራሊያና ኒውዚላንድ ቋንቋ አካል እንዲሆን ተደርጓል።

በአውስትራሊያ፣ ኒው ዚላንድና ኢንግላንድ እንዲሁም በግብጽ ወታደሮች በኩል ስለመድረስ የመጀመሪያ ዓመታዊ በዓል በ1916 ዓ.ም

ታይቷል። በዚያን ዓመት ሚያዚያ/April 25 ‘Anzac Day’ ተብሎ ተጠራ።

በ 1920 ዎቹ ዓመታት የአንዛክ ቀን/Anzac Day በሞላው አውስትራሊያና መስተዳድር ግዛቶች ውስጥ የአንዛክ ቀንን እንደ ህዝባዊ በዓል

ተመድቧል። በርእሰ ከተማዎች ላይ ዋናዎቹ የጦርነት መታሰቢያ ሀውልቶች ታንጸዋል፣ እንዲሁም በዚያን ጦርነትና ከዚያም በኋላ ለሞቱ

ወጣት ሴቶችና ወንዶች በአገሪቷ ርእሰ ከተማና ትናንሽ ከተማዎች ባሉ ሀውልቶች ሲታወሱ ይኖራሉ።

በጦርነት፣ በግጭትና በሰላም ኣስከባሪ ተግባር በመሰማራት ላገለገሉ ለማክበር በአሁን ጊዜ የአንዛክ ቀን/Anzac Day ይከበራል። ይህ ለጦር

ሰራዊት ብቻ የሚደረግ ክብረ በዓል አይደለም። ድል ላደረጉ የሚሰጥ ክብር አይደለም - የጋሊፖሎ/Gallipoli ዘመቻ ውድቀትን አሳይቷል።

የተራ አገልጋይ ሴቶችንና ወንዶችን ስራ ጥራት ያከብራል: ብዛት ያለው የተለያዩ ሰዎች ፊት ለፊት ሲገናኙ እንደ ጓደኛ መሆን፣ መቻቻልና

መከባበርን ያስሳሉ። ዛሬ የአንዛክ ቀን/Anzac Day በአውስትራሊያና በዓለም ዙሪያ ይከበራል። ከሁለተኛ ዓለም ጦርነትና ሌሎች ግጭቶች

እንዲሁም ከተባባሪ አገሮች የሰላም አስጠባቂዎችና በውትድርና ካገለገሉ ስዎች ጋር በአንዛክ ቀን በክብር ወታደራዊ ሰልፎች ያደርጋሉ።

በጋሊፖሊ/Gallipoli ላይ የአንዛክ ቀን ጅመራ አገልግሎት

64

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
ታላቅ የኢኮኖሚ ውድቀት፡ 1929 – 1932

ይህ ለአውስትራሊያ ህዝብ ከባድ ችግር የተከሰተበት ጊዜ ነበር። የኒው ዮርክ/New York የሽያጭ ገበያ ሲወድቅ በተመሳሳይ ጊዜ

አብሮ የጀመረ ሲሆን ነገር ግን ለዚህ የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ሌሎች ምክንያቶች ነበሩ። እነዚህም የኤክስፖርት ዋጋና ሽያጭ መቀነስ፣

በውጭ አገር ብድርና ለህንጻ የሚወጣ ብጀት ብበንግሥት መቀነስን ያካትታል። በ1932 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ከመቶ 32 እጅ የሚሆነው

አውስትራሊያዊ ሥራ አልነበረውም።

በኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት የአውስትራሊያ ሕብረተሰብ በጣም

አውድሞት ነበር። ብዙ ሰዎች ያለሥራና ያለ ቋሚ ገቢ መጠን

ቤታቸውን እንዳጡ ነው። የጤንነት ሁኔታ ባልተጠበቀ ወይም

ማሞቂያ በለለበት ጊዚያዊ መጠለያ እንዲኖሩ ተገደዋል። አንዳንድ

አባቶች ቤተሰባቸውን ትተው ወጥተዋል ወይም ወደ አልኮሆል ተገዥ

ሆነዋል። ህጻናት ለሥራ ሲሉ ትምህርት ቤት በ13 ወይም 14

ዓመት እድሜ አቁመዋል። ብዙ ስቶች መሰረታዊ በሆኑ ሥራዎች

ላይ ተሳትፈዋል እንዲሁም ልጆችንና ቤታቸውን በርሳቸው

ተንከባክበዋል።

በአውስትራሊያ የኢኮኖሚ ውድቀት በሚከሰትበት ጊዜ መንግሥት

ማእከላዊ የሆነ የሥራ አጥ ፕሮግራም አልነበረውም። እርዳታ

ከሚያደርጉ ድርጅቶች ባሻገር አንዳንድ የግል ድርጅቶች፣

ድሀ የሆኑ ሰዎች በሥራና ሰራተኛ ፕሮጀክቶችና በህዝባዊ ሥራ

ፕሮጀክቶች ላይ ይመኩ ነበር።

በ1932 ዓ.ም ኢኮኖሚው በብዙ መልኩ ሲሻሻል ነገር ግን

የቤተሰብ ጉዳት ሊያገግም አልቻለም። በታላቁ የኢኮኖሚ ውድቀት

ጊዜ የአውስትራሊያ በጎ አድራጊ ድርጅቶችና በፈቃደኛ ሠራተኞች

የተደረገ ጠቃሚ ድርሻ የሚደነቅ ነበር።

በኢኮኖሚ ውጥረት ጊዜ በኩሽና ሾርባ

ሰር ቻርለስ ኪንግስፎርድ ስሚዝ/Sir Charles Kingsford Smith (1897 – 1935)

ሰር ቻርልስ ኪንግስፎርድ ስሚዝ የተባሉት ደፋር አይሮፕላን አብራሪ፣ የበረራ አሳሽና የአውስትራሊያ

ጀግና ሰው ነበሩ።

በአንደኛ ዓለም ጦርነት ቻርልስ ኪንግስፎርድ ስሚዝ በጋሊፖሊ የተዋጉ እና ከብሪቴን የሮያል በራሪ

ብርጌድ ጋር ሆነው በረራ አካሂደዋል።

ከካሊፎርኒያ ተነስተው የፓስፊክ ውቂያኖስን አቋርጠው ኩዊንስላንድ በ1928 ዓ.ም መድረስ የመጀመሪያ

ታላቁ ስኬታማ ኣብራሪ ነበር። አይሮፕላናቸው ደቡባዊ ክልልን በማቋረጥ አውስትራሊያ ውስጥ ሲደርሱ

አንጠረኛ የሆኑ ጀግናቸውን በእልልታ ለመቀበል 25 000 ታማኝ ህዝብ ተገንቷል። በ1932 ዓ.ም በበረራ

አሳሽ ስይንስ የተመሰገኑ አገልጋይ ነበሩ።

በ1935 ዓ.ም ሳይታሰብ ከኢንግላንድ ወደ አውስትራሊያ ሲበሩ አይሮፕላናቸው እንደወደቀና እንዳልተገኙ

ነው።

ሰር ቻርልስ ኪንግስፎርድ ስሚዝ የዓለም ታላቁ የበረራ ሊቅ ይባሉ እንደነበርና በኢኮኖሚ ውጥረት ጊዜ ለህዝብ በመስጠት ትክክለኛ

የአውስትራሊያ ጀግና በመሆናቸው ሲታወሱ ይኖራሉ።

ክፍል 5 – የአውስትራሊያችን ታሪክ 65
ሁለተኛ የዓለም ጦርነት/World War II,

1939 - 1945

በሁለተኛ ዓለም ጦርነት ውስጥ አውስትራሊያኖች ከተባባሪ ቡድን

ጋር ሆነው በሰሜን አፍሪካ በርሀ እና በሌሎች ብዛት ባላቸው

ቦታዎች ላይ ተዋግተዋል። በሰሜን አፍሪካ ውስጥ ቶብሩክ/

Tobruk ከተማ ከጀርመንና ጣሊያን ጦር ጋር በመሆን ለረጅም

ጊዜ ተዋግተዋል። ጠላቶቻቸውን ‘የቶብሩክ አይጦች/Rats of

Tobruk’ ይሏቸዋል ምክንያቱም አደገኛ ቦታ ላይ ስለሚገኙና

ያገኙትን የምግብ ዓይነት ይበሉ ስለነበር ነው። አውስትራሊያኖች

በነዚህ ከባድ ሁኔታዎች ላይ ተዋግተው ያለፉ ስለሆነ ይህን ስም

ወስደዋል። እነዚህ ሰዎች በአንደኛ ዓለም ጦርነት ቆፋሪዎች ላይ

ለውጊያ ወኔ እንደነበራቸው በተተባባሪ ቡድን ላይ ታይቷል።

ወታደሮች የራሳቸው ልማዳዊ አኗኗር እንደነበራቸው ያውቃሉ።

ጃፓናውያን በነዚህ ወንዶች ላይ ያደረጉት ጭካኔ የተሞላበት

አቀባበል ከአውስትራሊያ ከፍተኛ ጦርነት መታሰቢያ ውስጥ አንዱ

ነው። ምንም እንኳን የአውስትራሊያ ጦር እስረኞች እርስ በርስ

ቢረዳዱም፣ ከመኮንኖችና ወንዶች አጋሮቻቸው ጋር በእኩልነት

መንፈስ ጥሩ አያያዝ ቢኖርም ብዙ አውስትራሊያኖች ሞተዋል።

በጸሎት የማስታወሻ ቀን

ከአንዛክ/Anzac Day ቀን ክብረ በዓላት ባሻገር በጦርነት

ሲያገለግሉ ለሞቱት አውስትራሊያውያን ለማስታወስ በጸሎት

ይከበራል። በየዓመቱ በህዳር/November 11 ቀን (በ11ኛው

ወር) ላይ ሰዓት 11am ጥዋት ሲሆን፣ በጦርነትና በግጭት ላይ

መስዋእትነትን ለከፈሉና ለሞቱ አውስትራሊያውያን ወንዶችና

ሴቶች በዚህ አጭር ጸሎት በኩል እናስታውሳቸዋለን። በዚህ ቀን

ቀይ የዱር አበባ እንለብሳለን።

ጃፓን ጦሩን በፓሲፊክ ውስጥ ካሰማራ በኋላ፣ የአውስትራሊያ

አገልጋይ ወንዶችና ሴቶች ወደ አገራቸው መጡ። ይሁን እንጂ

ከመመለሳቸው በፊት ለፓፑ ኒው ጉኒ/Papua and New

Guinea የመከላከል ሃይል አስፈለገ። ይህ ከባድ ተግባር በደንብ

ላልሰለጠኑ ምልምል ወታደሮች ተሰጠ። ጠላትን በጫካ፣ በገደል፣

በኮኮዳ/Kokoda Track በተባለ ጭቃማ እግር መንገድ ላይ

ተዋግተዋል። የጃፓን እንቅስቃሴ በአውስትራሊያ ብርጌድ

በመታገዱና የኮኮዳ/Kokoda Track መንገድ በጋልፖሊ

ከአንዛክ የባህር ወሽመጥ/Anzac Cove ጋር በመገናኘቱ ብዙዎች

አውስትራሊያኖች እንደ መንፈሳዊ መጓጓዣ ቦታ ኣድርገው

ይቆጥሩታል።

በኮኮዳ/Kokoda Track እግር ጉዞ ላይ ለቆሰለ ወታደር የፓፓውያን/Papuan

በሸክም እረድተዋል

በ1942 ዓ.ም በሲንጋፖር የሚገኘውን የታላቋ ብሪቲሽ ጦር ሠፈር

በጃፓን ሲወሰድ፣ ከነዚህ የጦር ብርጌድ 15 000 አውስትርሊያን

እንደነበሩና ወደ በThai-Burma Railway ባቡር ሀዲድ ላይ

እንዲሠሩ ተይዘው ተወሰዱ። ይህም በሁለተኛው ዓለም ጦርነት

ጃፓኖች የ Thai-Burma Railway ባቡር ሀዲድን በሚያሰሩበት

ጊዜ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ የብሪቲሽ ጦር እስረኞች ሞተዋል።

ከአንደኛ ዓለም ጦርነት ጊዜ ጀምሮ የነበረን ለማስታወስ በቀይ ዱር አበባ ማጌጥ

እንደ ምልክት ይሆናል

በቅርብ ጊዜ የአውስትራሊያ መከላከያ ሀይል ከኢስት ቲሞር/

East Timor፣ ኢራክ/Iraq፣ ሱዳን/Sudan እና አፍጋኒስታን/

Afghanistan ጋር ተዋግቷል እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት

(UN) ሰላም አስከባሪ ተግባር ላይ ተካፋይ ሆኖ በብዙ የዓለም

ክፍሎች ማለት አፍሪካ/Africa፣ መካከለኛው ምስራቅ/Middle

East እና በኤሽያ ፓስፊክ/Asia-Pacific አስተዳደር ክልልን

ያካትታል።

66

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
ሰር ኢድዋርድ ‘ዊርይ’ ዳንሎፕ/

Sir Edward ‘Weary’ Dunlop

(1907 – 1993)

በእስር ካምፑ ውስጥ ለአጭር ጊዜ ቢቆዩም ስለ መሬቷና ህዝቧ

ተምረዋል። ከጦርነት በኋላ ብዙዎቹ ኢሚግራንት/ስደተኛ ሆነው

ተመልሰዋል።

ሰር ኢድዋርድ ‘ዊርይ’

ዳንሎፕ/Sir Edward

‘Weary’ Dunlop የተባሉት

ጥሩና ተንከባካቢ የቀዶ ጥገና

ባለሙያና የአውስትራሊያ ጦር

ጀግና ነበር።

በሁለተኛ ዓለም ጦርነት ጊዜ

ዊርይ የጦሩ ቀዶ ጥገና ሀኪም

ነበሩ። እሳቸውና ተከታዮቻቸው

በጃፓናውያን ተይዘው

በታይ-ቡርማ/Thai-Burma

Railway ባቡር ሀዲድ እንዲሠሩ ወደ ቡርማ/Burma ተወሰዱ።

ይህም በጣም ረጂምና ከባድ ሥራ ነበር።

ዊይር የነሱ ኮማንዶር አዛዥ እንደመሆናቸው የነሱ ቃለ አቀባይ

ሆነዋል፤ እንደ ቀዶ ጥገና ሀኪም እነሱን ለማዳን ረጂም ሰዓታት

ያጠፉ ነበር። በካምፕ ውስጥ ተደብድበዋል ነገር ግን ያለምንም

ተቃውሞ ከማገልገል ወደኋላ አላሉም።

በ1969 ዓ.ም ስለ መድሀኒት ላደረጉት አስተዋጽኦ ተመስግነዋል።

በሚሞቱበት ጊዜ 10 000 ህዝብ በመልበርን መንገዶች ላይ

ተሰልፈው የክብር ቀብር ሥነ ስርዓት በማድረግ ቦታውን ‘የባቡር

ሀዲዱ ሀኪም/The Surgeon of the Railway’ ብለው ሰየሙት።

በመጀመሪያ 1900 ዎቹ ዓመታት ማይግሬሽን/

ስደት

በአንደኛና በሁለተኛ ዓለም ጦርነት መካከል በነበረ ጊዜ ወደ

አውስትራሊያ ገብቶ ለመቅረት የሚያግድ ቅድም ሁኔታ አለ። ይሁን

እንጂ የሚሰደደው የህዝብ እያደገ እንደመጣና፣ በተለይ ከደቡባዊ

አውሮፓ ወንዶች ነበሩ። ችሎታ/ሙያን፣ ትምህርትንና የራሳቸውን

ባህላዊ ልምድ ይዘው መጥተዋል። የአውስትራሊያ የገጠር ልማት

ኢንዱስትሪ፣ መንገዶችንና የባቡር ሀዲዶችን በማነጽ እድገት ላይ

እረድተዋል። በጣሊያን የሙያ ድንጋይ ጠራቢዎች በኩል ለህዝባዊ

ህንጻዎችና ለመኖሪያ ቤቶች ምስረታ ጠቃሚ የሆነ አስተዋጽኦ

አድርገዋል።

በ1930 ዎቹ ዓመታት፣ ከአውሮፓ የጀዊሽ ስደተኞች መግባት

ጀመሩ። እነሱም ከናዚ ጀርመን/Nazi Germany ፍርሀት

ለማምለጥ ነበር። ከጀርመን፣ አውስትሪያ/Austria፣ ቸኮዝሎቫኪያ/

Czechoslovakia፣ ሀንጋሪHungary እና ፖላንድ/Poland

እንደመጡ ነው። ብዙዎቹ ስደተኞች የተማሩና ጎበዝ ስለሆኑ

ለአውስትራሊያ ባህልዊ ሕይወት ከፍተኛ አስተዋስኦ አድርገዋል።

የአውሮፓ ስደተኛ/ማይግራንት አውስትራሊያ ውስጥ ስለመድረስ

ከጦርነት በኋላ ስደተኞች

አውስትርሊያ ከጦርነት በኋላ የህዝቧን ቁጥር ለመጨመር ከሌሎች

አውሮፓ አገሮች ስደተኞችን አመጡ። ብዙ ሚሊዮን ህዝብ ከናዚ

ጀርመን ለቀው ወጡ ወይም አገሪቱ በሶቪየት ራሺያ/Soviet

Russia ስለተያዘች ወደ ትውልድ አገራቸው መመለስ አልቻሉም።

በግምት 170 000 የሚሆኑት እነዚህ ተፈናቃዮች በአውስትራሊያ

ውስጥ አዲስ ኑሮን ለመጀር ተፈቀደላቸው።

እንዲሁም በአውስትራሊያ ውስጥ ከባድ የሠራተኛ እጥረት ነበር።

የህዝብ ብዛት ማደግ ለወደፊት የአገሪቷ እድል ጠቃሜታ አለው

በሚል የአውስትራሊያ መንግሥት አምኖበታል። እድሚያቸው ከ45

ዓመት በታች ለሆነ ጤናማ ጎልማሳ ስደተኞች ወደ አውስትራሊያ

ለመጓጓዝ £10 እንዲሁም ለህጻናት ጉዞ ያለክፍያ ነበር። ይሁን

እንጂ ከዩናይትድ ኪንግዶምና አውሮፓ ላሉ ብሄሮች እስከዚያን

ጊዜ ለመጓዝ አቀብ ገደብ ነበር።

አውስትራሊያን በበለጠ ለማጠናከር፣ ከበረዷማ ወንዝ ውሀ ወደ

ምስራቃዊ የቪክቶሪያ ባህር ከመፍሰሱ በፊት ለመያዝ ሲባል በ1949

ዓ.ም የአውስትራሊያ መንግሥት ግልጽ የሥራ ፕሮግራም ማካሄድ

ጀመረ። ይህ ውሀ ለመስኖና ለኤሌክትሪክ ማመንጫ ሀይል ጅነሬተር

እንዲውል የውሀ ፍሳሹ ወደ መሬት ተቀየረ። ትልቅ የፕሮጀክት ሥራ

ስለነበር ለማጠናቀቅ 25 ዓመታት ወስዷል። በዚህ ፕሮጀክት ውስጥ

ከመቶ ሰባ እጅ የሚሆኑት ሠራተኞች ስደተኞች ነበሩ።

በሁለተኛ ዓለም ጦርነት ላይ 17 000 የጣሊያን ወታደሮች

እንደተያዙያ በአውስትራሊያ በሚገኝ ጦር ካምፕ እስር ቤት

ገብተዋል። በአግባቡ መስተንግዶ ተደርጎላቸዋል።

ክፍል 5 – የአውስትራሊያችን ታሪክ 67
በበረዷማ ተራሮች የሀይድሮ ኤሌትሪክ አሰራር

እንደ በራስ መመራት፣ የመድብለ ባህላዊና በሀብት የበለጸገች አገር መሆን ለአውስትራሊያ ማንነት መግለጫ ጠቃሚ ምልክት ነው።

በአውስትራሊያ ውስጥ ይህ ትልቁ የኢንጅነሪንግ ፕሮጀክት ነው። እንዲሁም በዓለም ላይ ካሉት ትላቅ የሀይድሮ-ኤሌትሪክ ሥራ አንደኛው

ይሆናል።

በኒው ሳውዝ ዌልስ እና ቪክቶሪያ ባለ መሬት ላይ የእርሻ ኢንዱስትሪዎች ጠቃሚ የውሀ አቅርቦት በዚህ አሰራር ይቀርባል። እንዲሁም ከመቶ

10 እጅ የሚሆነው የኒው ሳውዝ ዌልስ ኤሌትሪክ ፍጆታ በዚህ ሀይል ማመንጫ ጣቢያዎች ይቀርባል።

የበረዷማ ተራራዎች አሰራር፣ ከመቶ 2 እጅ ብቻ በመሬት ላይ ይታያል። በዚህ አሰራር ላይ 16 ዋና ግድቦች፣ ሰባት የሀይል ማመንጫ

ጣቢያዎች፣ የማጣሪያ ጣቢያና 225 ኪሎ ሜትር መተላለፊያ ቀዳዳዎች፣ የቧንቧ መስመሮችና የውሀ ቧንቧዎች ይካተታሉ።

የአሰራር ዘዴው በ1949 ዓ.ም ጀምሮ በ1974 ዓ.ም አለቀ። ከ30 አገሮች በላይ የመጡና ከ100 000 በላይ ሰዎች በፕሮጀክቱ ላይ

ሠርተዋል። ከነዚህ ሠራተኞች ውስጥ ከመቶ ሰባ እጅ መጤ ስደተኞች ነበሩ። ፕሮጀክቱ ካለቀ በኋላ አብዛኞቹ አውሮፓውያን ሠራተኞች

በአውስትራሊያ ለመኖር እንደቀሩና ለአውስትራሊያ መድብለ ባህላዊ ሕብረሰተስብ ጠቃሚ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው።

የበረዷማ ተራራዎች አሰራር በኒው ሳውዝ ዌልስ፣ በኮስኩዝኮ ብሄራዊ መናፈሻ/Kosciuszko National Park ውስጥ ይገኛል። ፕሮጀክቱ

በአካባቢ ስለሚያስከትለው ችግር በቅርበት ክትትል ይደረጋል። የዚህ አሰራር ጥሩነት በአሁኑ ጊዜ በአንዳንድ ቦታዎች የበረዷማ ወንዝ/

Snowy River ቀደም ሲል ከሚሸከመው ውሀ ከመቶ 1 እጅ ብቻ ይሆናል።

ለጥሩ የአካባቢ ጥበቃ ሲባል ከመቶ 28 እጅ የሚሆነውን የወንዝ ፍሳሽ ለማጠራቀም የቪክቶሪያና የኒው ሳውዝ ዌልስ መንግሥታት

ተስማምተዋል።

በበረዷሟ ተራሮች ሥራ የተሰማሩ ሠራተኞች

68

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
ስለአገር ተወላጁ አያያዝ

በ1940 ዎቹ እና 1950 ዎቹ ዓመታት የአውስትራሊያ ፖሊሲ

ለውህደት የአቦርጂናል ህዝብ መቀየር ነው። ይህ ማለት የአገር

ተወላጅ ህዝብ እንደሌላው ህዝብ መኖር እንደሚገባ ተነግሯቸዋል።

የአቦጅንል ህዝብ ያላቸውን ባህላዊ ልምዶች ማጥፋት ስላልፈለጉ

ስለዚህ ፖሊሲው ተግባራዊ አልሆነም።

በ1960 ዎቹ ዓመታት ፖሊሲው ወደ ውህደት ተቀየረ።

በአውስትርያ ውስጥ ብዙዎች ወንዶች በ1850 ዎቹ የምርጫ

ድምጽ ለመስጠት መብት ሲያገኙ ነገር ግን ለህሉም የአገሬው

ተወላጅ እስከ 1962 ዓ.ም በኮመንዌልዝ መንግሥት ምርጫ

ድምጽ የመስጠት መብት አልነበረም። በአንድነት መዋሀዱ

ለአቦርጂናል ሲቪል ነጻነት ቢሰጥም ነገር ግን የአገሬ ተወላጅ

ያልሆኑትን የአውስትራሊያ ባህል መከተልና መላመድ ይኖርባቸዋል።

በ1967 ዓ.ም የበለጠ ለውጥ መጣ ይህም በህዝብ ቆጠራ

ላይ ለአቦርጂናል ህዝብ መቆጠር እንዲችሉ ከመቶ 90 እጅ

የአውስትራሊያ ህዝብ ‘አዎ/YES’ የሚል ድምጽ ሰጥተዋል።

ይህ የህዝብ ውሳኔ ታሪካዊ መግለጫ ነበር። ይህም የሚያሳየው

ለአቦርጂናል ህዝብ እንደማኛውም ሰው እኩል መብት እንዲሰጥ

አብዛኛው አውስትራሊያዊ ይፈልግ እንደነበር ነው።

የዚህ ዓይነት የአውስትራሊያዊ አስተሳሰብ እና በዚህ ጊዜ ጠንካራ

የአቦርጅናል ተቃውሞ ስለነበር በ1970 ዎቹ ዓመታት ለአገሬው

ተወላጅ በራስ የመወሰን ፖሊሲ እንዲወጣ መንገድ ከፈተ። የአገር

ተወላጅ በራሳቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚ፣ ማሕበራዊና ባህላዊ እድገት

ላይ መመራት እንዳለባቸው የአውስትራሊያ መንግሥት ተቀብሎ

ተስማምቷል።

ማይግሬሽን/መሰደድ - ቀስ በቀስ ለውጥ

በ1950 ዎቹ እና 1960 ዎቹ ዓመታት፣ የኢሺያ ማህበረሰብ፣

ቤተክርስቲያንና ማሕበራዊ ቡድኖች ‘የነጭ አውስትራሊያ/White

Australia’ ፖሊሲ እንዲያበቃ ተቃውሞ አድርገዋል።

በ1958 ዓ.ም የአውስትራሊያ መንግሥት አምባገነናዊ ጥያቄን

አስቆመ፤ በ1966 ዓ.ም በምርጫ አውሮፓዊ ላልሆነ እና ሙያተኛ

ኤሺያዊን ለማስገባት አውስትራሊያ በሮቿን ከፈተች። በማይግሬሽን

ፕሮግራማችን የተካተተውን የሞላው አገር ባህልና ልማድ ቀስ

በቀስ አውስትራሊያዊ በሁሉም ቦታ ላይ ተቀብሎታል። በ1973

ዓ.ም ‘የነጭ አውስትራሊያ/White Australia’ ፖሊሲ እንዳበቃና

አገሪቷም የመድብለ ባህላዊ መንገድ ተከትላለች።

እነዚህ ሰዎች አብዛኞቹ ከቬትናም እንደነበሩና በተጨማሪም ከቻይና

እና ከህንድ በብዛት መግባት ጀመሩ።

እስከ 1975 ዓ.ም አውስትራሊያ ከብዙ ጦርነት የዳሸቀው አገር

ስደተኞችን ትቀበል እንደነበርና ይህም ቦስኒያንና ሀርዘጎቪና/

Herzegovina፣ እንዲሁም ከመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ

አገሮችን ያካትታል። በዛሬ ቀን የእኛ መጤዎች/ስደተኞች

ከሞላው ዓለም ይመጣሉ።

አውስትራሊያ ሁሉም ዓይነት መሬት ስላላት ከዓለም ታላቅ ዘመናዊ

ከሆኑት አገሮች ውስጥ አንዷ ሆናለች። እስከ 1945 ዓ.ም ድረስ

6.5 ሚሊዮን ህዝብ ወደ አውስትራሊያ መጥተዋል። ከአንድ

አራተኛ በላይ የሚሆኑት የአውስትራሊያ ህዝብ ትውልዳቸው በውጭ

አገር ነው።

ማይግራንት/ስደተኖች ወደ አውስትራሊያ እንዲመጡ በመምረጥና

እዚህ መጥተው ያለንን ባህል/ልምድ በጋራ እንድንካፈል ነው።

ባለው የአውስትራሊያዊ የኑሮ ዘርፍ ላይ የእነሱንም ይጨምራሉ።

ማጠቃለያ

አሁን አውስትራሊያ የመድብለ ባህላዊ ሕብረተሰብ ስትሆን

የእያንዳንዱ ግለሰብ እምነት ለማካሄድ መብትና ባህላዊ ልምዶችን

ለመከተል በህጉ አሰራር መሰረት መከበርና መጠበቅ አለበት።

ዛሬ አውስትራሊያ ሁሉንም የሚያካትት ፖሊሲ እንዳላትና

እያንዳንዱ የብሄር ተወላጅ የሕብረተሰባችን አባል እንደሆነ

ይሰማዋል። የአውስትራሊያ ባህል ጉዳዮች በሞላ በዚህ ፖሊሲ

ይካሄዳል። ከመጀመሪያ የልጅነት እስከ ዩኒቨርሲቲ ባለ ስርዓተ

ትምህርታችን ላይ ይህ ፓሊስ አንዱ ክፍል እንደሆነና በሥራ

ቦታችንና በአገልግሎት ኢንዱስትሪ ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል።

በአውስትራሊያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነና በእያንዳንዱ መስተዳደር

ግዛትና ተሪቶሪ መንግሥታዊ የጸረ-አድልዎ ድርጅቶች እንደተገጸው

እያንዳንዱ ግለሰብ ያለምንም አድልዎ በእኩልነት የመስተናገድ

መብት ይኖረዋል። በዘር ልዩነት መፍጠር በህዝብ ተቀባይነት

እንደሌለውና በህጉ መሰረት ወንጀል ነው።

አውስትራሊያ ተስማሚና ተቀባይነት ያለው የመድብለ ባህላዊ

ሕበረተሰብ ሆነች። ማይግራንት/መጤዎች፣ አገር ተወላጁና ሌሎች

በአውስትራሊያ የተወለዱ ህዝቦች በሰላም የፈለጉትን ለማድረግ

ነጻነት ያለባት አገር ናት። ያለፉት ልዩነቶችና ቅሬታዎች ወደኋላ

መተው የሚቻልበት ቦታ ነው።

በ1973 ዓ.ም የአውስትራሊያ መንግሥት በኢሚግሬሽን ማንኛውም

የዘር መረጣ አስወገደ። በ1975 ዓ.ም ከቬትናም ጦርነት በኋላ

አውስትራሊያ በቁጥር ብዛት ያለው ከኤሺያ ስደተኞችንና

ማይግራንት መጤዎችን ተቀብላለች።

ክፍል 5 – የአውስትራሊያችን ታሪክ 69
ድ/ር ቪክቶር ቻንግ/Dr Victor Chang (1936 – 1991)

ዶክተር ቪክቶር ቻንግ የተባሉት ከታወቁት የልብ ሀኪሞች ውስጥ አንደኛው ነበሩ።

ቪክቶር ፐተር ቻንግ ፓም ሂም/Victor Peter Chang Yam Him በ1936 ዓ.ም በቻይና አገር

እንደተወለዱና እድሚያቸው 15 ዓመት ሲሆን ወደ አውስትራሊያ መጡ።

ስይድነይ በሚገኘው የሴንት ቪንሰንት ሆስፒታል/St. Vincent’s Hospital ውስጥ ይሠሩ እንደነበርና

በ1984 ዓ.ም በአውስትራሊያ የመጀመሪያ የልብ ቅየራ ቀዶ ጥገና ማእከልን ያቋቋሙ ሰው ናቸው።

በ1986 ዓ.ም ቪክቶር ቻንግ የአውስትራሊያ ህግ ስርአትን ያወጡ ስለነበር ከፍተኛ የአውስትራሊያ

ተሸላሚ ነበሩ።

ቪክቶር/Victor ስለ ልብ ለጋሽ እጥረት ስላሳሰባቸው፣ ስለዚህ የሰው ሰራሽ ልብ ለማውጣት አቀዱ፤

በ1991 ዓ.ም አሳዛኝ በሆነ መልኩ ሲገደሉ ይህ እቅድ ወድማለቁ ገደማ ነበር።

ለሳቸው ማስታወሻ ይሆን ዘንድ አዲስ የምርምር ጣቢያ ተመስርቷል። ባደረጉ የሙያ ኤክስፐርት፣ መልካም ቀናነትና የፈጠራ ችሎታቸው

ሲታወሱ ይኖራሉ።

አልበርት ናማትጂራ/Albert Namatjira

(1902 – 1959)

ኢዲ ማቦ/Eddie Mabo

(1936 – 1992)

አልበርት ናማትጂራ/Albert

Namatjira የተባሉት

በትምህርት ቤት ውስጥ የአሳሳል

ዘዴን ያስጀመሩና በአሁኑ ጊዜ

እንዲቀጥል ካደረጉት ታላላቅ

የአውስትራሊያ ሰአሊዎች

ውስጥ አንደኛው ሰው ናቸው።

አልበርት/Albert እንደ ወጣት

Arrernte፣ ስእል በመስራት

ያላቸው ተፈጥሮ ችሎታ

አሳይተዋል።

በጣም የተወሰነ መደበኛ ስልጠና ሲኖራቸው ነገር ግን

የአውስትራሊያን አገር በውሃ ህብረ ቀለማት በመሳል በጣም የታወቁ

እንደነበረና ሁሉም ስእሎች በቶሎ ይሸጡ ነበር።

እሳቸውና ባለቤታቸው ለአውስትራሊያ ዜግነት የተፈቀደላቸው

የመጀመሪያ አቦርጅናል ሰዎች ናቸው። ይህ ማለትም በምርጫ

ድምጽ መስጠት፣ በሆቴል ውስጥ መግባታ በፈለጉበት ቦታ ላይ

መኖሪያ ቤት መሥራት ይችላሉ። አልበርት የአውስትራሊያ ዜግነትን

ማግኘት የሚያሳየው ሌሎች አቦርጂናል ሰዎች ዜግነት ለማግኘት

መብት አልነበራቸውም።

ሚስታቸው ለአገሬው ተወላጅ ላልሆኑ አውስትራሊያውያን ስለወጣ

የዘረኛ ህጎች ኢ-ፍትሀዊ እንደሆነ በማሳየት ለአቦርጅናል ህዝብ

ለውጥ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ኢዲ ማቦ/Eddie Mabo

ስለ የአገሬው ተወላጅ መሬት

መብቶች ንቁ ተሳታፊና ቃለ

አቀባይ ነበሩ።

ኢዲ ኮኪ ማቦ/Eddie Koiki

Mabo የማቦ ጎሳ የጥንት

መሬት፣ ሙራይ ደሴት/Murray

Island ላይ ትእወለዱ።

ከልጅነታቸው ጀምሮ ስለ

ቤተሰባቸው መሬት ደንበር

በየትኛው ዛፎችና ድንጋዮች

እንደሚከለል ያስቡ ነበር።

በአውስትራሊያ ህግ የትውልድ ቦታቸው በነገስታት መሬት/

Crown land ስር እንደሚቆጠርና የቤተሰባቸው አለመሆኑን እስከ

ብዙ ዓመታት ኢዲ/Eddie አያውቁም ነበር። በዚህ ላይ በጣም

እንደተበሳጩና የሙራይ ደሴት/Murray Island ህዝብን ወክለው

ጉዳዩን ለመከራከር ወደ ፍርድ ቤት አቀረቡት።

ከብዙ ዓመታት በኋላ በ1992 ዓ.ም የኢዲ/Eddie ጉዳይ በከፍተኛ

ፍርድ ቤት አሸነፉ። የማቦ/Mabo ውሳኔ እንደሚለው የአገሬው

ተወላጅ ከመሬታቸው ጋር በተያያዘ ታሪካዊና ባህላዊ ልምዶች ካለ

ታዲያ ለዚያ መሬት ካልተያዘ በባቤትነት መጠየቅ ይችላሉ። ከዚህ

ውሳኔ በኋላ ትላልቅ መሬቶች ወደ መጀመሪያ ባለንብረት ተመለሱ።

ኢዲ ማቦ/Eddie Mabo ለአገሬው ተወላጅ የመሬት ማግኘት

መብቶች ላደረጉት አስተዋጽኦ ሲታወሱ ይኖራሉ።

70

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
የአገሬው ተወላጅ ህዝብ – የሁለት አስር

ዓመታት ለውጥ

በ1960 ዎቹ ዓመታት ስለመሬት መብቶች በሰሜናዊ ተሪቶርይ፣

ጉሪንድጂ ስትሪክ/Gurindji Strike በዋቭ ሂል/Wave Hill

cattle የከብት እርባታ ጣቢያ በተደረገ የአቦርጂናል ተቃውሞ

የህዝብን ፍላጎት እንደሳበ ነው። በቪንሰንት/Vincent Lingiari

የሚመራ የአቦርጂናል አርቢዎች ከእርባታ ሥራ ጣቢያ እንደወጡ

ነው። የተቃወሙት ስለ ክፍያና የሥራ ሁኒታዎች እንደነበረና

ከዚያም ወደ የመሬት መብቶች ጥያቄ ተቀየረ። ለአገሬው ተወላጅ

የመሬት መብቶች ትግል ሲያካሂዱ የኢዲ ማቦንና የሌሎችን ፈለግ

ተከትለዋል።

ዛሬ ለአውስትራሊያ መጠሪያ በአገሬው ተወላጅ የሚደረግ ጠቃሚ

አስተዋጽኦ ተቀባይነት በማግኘት ይከባራል። የአቦርጂናልና የቶረስ

ስትሬት አይላንደር ህዝብ በሞላው የአውስትራሊያ ያሉ ሥራ

ዘርፎች የመሪነት ሥልጣን ሲኖራቸው ይህም ማለት ፍትሃዊ

አሰራር፣ ፖለቲካዎች፣ የስነ-ጥበባት እና ስፖርትን ያካተተ ነው።

የአቦርጂናልን ንቃት በማሳየት MARVIN ፕሮግራም ብዙ

ሽልማቶችን እንዳገኘና ይህም በዓለም ዙሪያ ውስጥ ከሀያ አገሮች

በላይ ላሉ የትምህርትና የንግድ ተቋማት ይጠቅማል።

በአቦርጂናል የመሬት መብቶች (ሰሜናዊ ተሪቶርይ) ህግ አንቀጽ/

Act 1976 ዓ.ም መሰረት ከአውስትራሊያ ከተማ የራቀ ስፋት

ያላቸው አካባቢዎች ለአቦርጂናል ህዝብ እንደተሰጠ ነው። በ1990

ዎቹ ዓመታት መጀመሪያ ላይ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የማቦ ውሳኔ

እና የተወላጅ መብት/Native Title ህግ አንቀጽ/Act 1993

ዓ.ም የአገሬው ተወላጅ ባላቸው ባህላዊ ህጎችና ልምዶች በመነሳት

ለመሬት ማመልከት ይፈቀድላቸዋል። በአሁን ጊዜ የአውስትራሊያ

መሬት ከመቶ 10 እጅ በላይ የተያዘው በተወላጅ መብት ውሳኔ

ነው። እዚህ አሁንም የልማዳዊ ሕብረተሰብ ሥራ ጉዳይ ይኖራል።

የአገሬው ተወላጅ ባህል እየተንሰራፋ የሚሄድና ይህም ስፋት ባለው

ማህበረሰብ በጥልቅ ይሞገሳል።

ግንቦት/May 1997 ዓ.ም፤ ‘ወደ ቤታቸው ስለማምጣት/Bringing

them home’ የሚል ሪፖርት በአውስትራሊያ ፓርሊያመንት

ጠረጴዛ ላይ ቀረበ። የሪፖርቱ ይዘት ብዛት ስላለው የአቦርጂናልና

የቶረስ ስትሬት አይላንደር ህጻናትን ከቤተሰባቸው ነጥሎ መውሰድ

ጥያቄ ነበር። እነዚህ ህጻናት ‘የተሰረቀ ትውልድ/Stolen

Generations’ በሚል ስም ይታወቃሉ። ከዚህ ሪፖርት በኋላ

በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አውስትራሊያን ድጋፋቸውን በ1998

ዓ.ም የመጀመሪያ ብሄራዊ ‘የይቅርታ ቀን/Sorry Day’ ሰልፍ ላይ

በጋራ ገለጹ።

ለተሰረቀ ትውልድ ይቅርታ መጠየቅ፣ 2008

ዓ.ም

ጥር/February 13 ቀን 2008 ዓ.ም በአውስትራሊያ

ፓርሊያመንት ፊት ለተሰረቁ ትውዶች ብሄራዊ የይቅርታ ጥያቄ

የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስተር አቅርበዋል። እሳቸውም ሁሉንም

አውስትራሊያዊ ወክለው ተናግረዋል። በአለፈው ጊዜ በአገሬው

ተወላጅ ስለተደረገው የአቀራረብ ሁኔታ ይቅርታ ብለዋል። በተለይ

ለአገሬው ተወላጅ ህጻናት ከወላጆቻቸ በመንጠቅ ስለተደረገው ሁኔታ

ይቅርታ ብለዋል።

የጽህፈት ሊቅ/Skywriter ስለ ስይድነይ ‘የይቅርታ መጠየ’ ተጽፏል

ማጠቃለያ

በነዚህ ገጾች በኩል የአውስትራሊያ ታሪካችንን ጨረፍ

ያደርግልዎታል። በዚህ አዲስ መረጃ ስለ አካባቢዎ ያለዎን

ግንዛቤ በር ሊከፍትልዎ ይችላል። በአሮጌ ህንጻዎች ላይ ተጽፎ

ያለን ቀን ማየት ይጀምሩና ታዲያ በየትኛው የታሪክ አምድ ላይ

እንደተመደበ ያገናዝቡታል። በጦርነት ግንባር ሲያገለግሉ የሞቱትን

ወንዶችና ሴቶች ለማስታወስ ህዳር/November 11 ቀን የዱር

ቀይ አበባ እንዲለብሱ ሲቀርብልዎ ያውቁታል። ከአገሬው ተወላጅ

አውስትራሊያዊ ጋር ሲገናኙ ጥንት ስለነበረ ባህላቸው ስሜት

ያሳድርብዎታል። የአካባቢ መገልገያን እየተጠቀሙና ከቦታ ቦታ

እየተጓጓዙ ያለዎትን እውቀት እንዲያስፋፉት እናስገነዝባለን። በበለጠ

ሲያውቁ የበለጠ ያስታውሳሉ።

ለአውስትራሊያ ዜግነት እንኳን ደህና መጡ እንዲሁም ሰላም

በሰፈነባት ዲሞክራቲክ አገር ውስጥ ስሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ

ተጋብዘዋል።

ያደረጉት ንግግር በተሌቪዥንና በራዲዩ ጣቢያዎች ተላልፈዋል።

‘የይቅርታ’ ጥያቄ ንግግርን ለማዳመጥ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ

አውስትራሊያን በህዝብ አደባባይና በሥራ ቦታቸዎች ላይ

ተሰብስበዋል። በይፋ ንግግሩ የተመዘገበው ያለፈው ኢፍትሃዊነና

ለእነሱ ይቅርታ መተየቅ በሚል ነው። ይህ የአለፈን ተወላጅ ቁስል

ለማገገም ጠቃሚ እርምጃ ሲሆን እነዚህ ኢፍትሃዊ የሆኑ ድርጊቶች

ዳግም እንዳይከሰት ለማረጋገጥ ይሆናል። የይቅርታ ጥያቄ ንግግሩ

ለሁሉም አውስትራሊያዊ ጠቃሚ እርምጃ ነበር።

ክፍል 5 – የአውስትራሊያችን ታሪክ 71
መመዘን የማያስፈልገው ቃላት ፍቺ ክፍል

አምባሳዶር

ለአገር ወይም ለእንቅስቃሴ እድገት ተወካይ ሰው

ቦርድ

ውሳኔ ለመስጠት በህዝብ የሚመረጥ ቡድን፤ ለምሳሌ፡ እንዴት አንድ ኩባንያ መስተዳደር እንዳለበት

አዳሪ ትምህርት ቤት

ተማሪዎች የሚኖሩበት ትምህርት ቤት ሲሆን በሞላው ትምርት ፈረቃ ጊዜ ወደ ቤታቸው አይመለሱም

ጫካ

የአውስትራሊያ ገጠሩ ክፍል አሁንም ተፈጥሮን አልቀየረም

የከብት እርባታ

ከብቶች ለሥጋ ማደለቢያ የሚሆን ትልቅ እርሻ ነው

ህገ ደንብ

ስለ መብቶችና ሃላፊነቶች የጽሁፍ ህጋዊ መግለጫ

ጎሳ

በደም ወይም በጋብቻ የተዛመዱ ቡድኖችና በተመሳሳይ ተሪቶርይ የሚኖሩ

የጋራ መድረክ

በፍላጎት አብሮ የሚሳተፉት

የግዳጅ ወታደር

በመከላከያ ሀይል ለመሳተፍ ያልመረጠ ነገር ግን በጦርነት ጊዜ የሚሳተፍ

የንጉሳዊ መሬት Crown land

የመንግሥት መሬት

ስርአተ ትምህርት

የትምህርታዊ ይዘት

የቸገረው

ገንዘብ የሌለው ወይም የማግኛ ዘዴ

የሙዚቃ መሳሪያ/didgeridoo

በአውስትራሊያ አቦርጂናል ሰዎች ከረጅም ቀዳዳ የሚሰራ የሙዚቃ መሳሪያ

በአግባቡ መጓዝ

እያንዳንዱ ጥሩ እንዲሠራ ተገቢ ወይም እኩል እድል መስጠት

በአግባብ መጫወት

በቡድን ተግባር ሲሳተፉ ለእያንዳንዱ ጥቅምና ጥሩ የቡድን ሥራ ደንቦችን መከተል

በጦርነት ሲያገለግሉ የሞቱ ወንዶችና ሴቶች

በጦርነት ላይ እያሉ ለሞቱ ወንዶችና ሴቶች

ማስመሰል

ለማነጽ ወይም ለመፍጠር

ጠቅላላ ዓመታዊ አገር ምርት

በዓመት ውስጥ በአገሪቷ ውስጥ የእቃና አገልግሎት ምርት ዋጋ

የሙቀት ነበልባል

ለሁለት ቀናት በተከታታይ የሚቆይ በአም ሞቃት የአየር ጠባይ

ከፍተኛ የአገር ጥላቻ

መንግሥትን ለመገልበጥ የሚደረግ ጥረትና ከባድ ወንጀል

72

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
ለአገር ተወላጅ ስእላዊ ምስል

የአገሬ ተወላጁን የሚያሳይ ልዩ ስነ-ጥበብ

ግዙፍ መሬት

የመሬት ስፋት

ታሪካዊ ድርጊት

በታሪክ ጠቃሚ ድርጊት

የተወላጁ መብት

ስለተወላጁ መሬትን ውሀ ማግኘት ልማዳዊ መብቶች፤ በአውስትራሊያ ህጋዊ አሰራር የተወሰነ

አፈ ታሪክ

በአለፉት ጊዚያት ምን እንደተደረገ ሰዎች በማስታወስ የሚናገሩት

አሳሽ ሰፋሪ

በቅኝ ገዥ በመጀመሪያ ቀናት ከሰፈሩት ውስጥ አንደኛው ይሆናሉ

ፖለቲካዊ ውክልና

በፓርሊያመንት ውስጥ በፖለቲካ ሰዎች ውክልና ማግኘት

የተያዘ መሬት

ለአቦርጂናል ሰዎች መኖሪያ ተብሎ በመንግሥት ለብቻ የተከለለ ቦታ

እስራት

ወንጀለኛ እንደ ቅጣት የእስራት ጊዜ

የተወሰነ ደመውዝ

ተቀጣሪዎች ለሠሩበት ምን ያህል መከፈል እንዳለበት መወሰን

ማሕበራዊ ለውጥ

በአንድ ጊዜ ሳይሆን ቀስ በቀስ ለሕብረተሰብ ማሻሻል

ስርዓተ ቀብር ሰልፍ

ለአገሪቱ ጠቃሚ አስተዋጽsኦ ላደረገ ጀግና ዜጋዊ በሚሞትበት ጊዜ መንግሥት የስርዓተ ቀብር ሰልፍ ያደርግለታል

ምሽግ

በእንጨት ምሰሶና ችካል የተከበበ መከላከያ ቦታ

እረኞች

ከብቶችን ለመጠበቅ የተቀጠሩ ወንዶች

ማደም

ተቀጣሪዎች ሥራ ሲያቆሙ፣ ለምሳሌ በቀጣሪ ውሳኔ ላይ ተቃውሞ ማሰማት

የምርጫ መብት

በህዝብ ምርጫ ላይ ድምጽ የመስጠት መብት

በመሀላ የጸና

መደበኛ በሆነ ስነስርአት ላይ በህዝብ ቢሮ ተቀባይነትን ማግኘት

ሪፖርት ማቅረብ

በፓሪያመንት ላይ ለመወያየት ወይም ሪፖርት ለማቅረብ በህግ መወከል ለምሳሌ፡ ሪፖርት መድረክ ላይ ማቅረብ

አኗኗር ደረጃ

ማሕበራዊ ደረጃ ወይም መነሻ፣ ሥራ፣ ማእረግ

መፈተሽ የማይገባው የቃላት ፍቺ ክፍል 73
ለበለጠ መረጃ

የአውስትራሊያ ዜግነት

የአውስትራሊያ ዜጋ እንዴት እንደሚሆኑ በበለጠ መረጃ ለማግኘት የአውስትራሊያ ዜግነት የሚለውን በድረገጽ www.citizenship.gov.au

ይጎብኙ።

አውስትራሊያ

በአካባቢዎ ቤተመጽሐፍ ስለ አውስትራሊያ በበለጠ መረጃ ማግኘት ይችላሉ። እንዲሁም ከዚህ በታች ያሉት ድረገጾች የበለጠ መረጃ

ሊያቀርቡ ይችላሉ:

• አውስትራሊያ በአጭሩ

• የባህልና መዝናኛ መግቢያ በር

www.dfat.gov.au/aib

www.cultureandrecreation.gov.au

የአውስትራሊያ መንግሥት ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች

ስለ አውስትራሊያ መንግሥት ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች መረጃ ከድረገጽ፡ www.australia.gov.au ላይ ማግኘት ይችላሉ።

የፌደራል ፓርሊያመንት አባል/MP ወይም የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል

ስለ የአውስትራሊያ መንግሥት ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች በተመለከተ የተለያየ መረጃ በአካባቢዎ ፌደራል ፓርሊያመንት አባል/MP ወይም

ለመስተዳድር ግዛትዎ ወይም ተሪቶርይ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል በኩል ይገኛል።

የፓርሊያመንት አባል/MPs እና ምክር ቤት አባላት ዝርዝር በድረገጽ www.aph.gov.au ላይ ማግኘት ይቻላል።

የአውስትራሊያ መንግሥት ድርጅቶች

ስለ አውስትራሊያ መንግሥት ድርጅቶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ባሉት ድረገጾች ላይ በመገልገያ መጽሀፍ ውስጥ ማግኘት

ይቻላል:

• የአውስትራሊያ መከላከያ ሀይል/

Australian Defence Force

• የአውስትራሊያ የምርጫ ኮሚሽን/

Australian Electoral Commission

• የአውስትራሊያ ፌደራል ፖሊስ/

Australian Federal Police

• የአውስትራሊያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን/

Australian Human Rights Commission

• የአውስትራሊያ ስፖርት ኮሚሽን/

Australian Sports Commission

• የአውስትራሊያ ግብር ጽህፈት ቤት/

Australian Taxation Office

• የአውስትራሊያ ጦር መታሰቢያ/

Australian War Memorial

• የአውስትራሊያ ቁጠባ/ረዘርቭ ባንክ/

Reserve Bank of Australia

www.defence.gov.au

www.aec.gov.au

www.afp.gov.au

www.humanrights.gov.au

www.ausport.gov.au

www.ato.gov.au

www.awm.gov.au

www.rba.gov.au

74

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች

ስለ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ባሉት ድረገጾች ላይ በመገልገያ መጽሀፍ ውስጥ ማግኘት

ይቻላል:

• በአውስትራሊያ የብራድማን የእርዳታ ድርጅት/

Bradman Foundation Australia

• በዓለም አቀፍ ያልተለመደ የሃምሊን ፊስቱላ/

Hamlin Fistula International

• የአውትራሊያ ሮያል የበረራ ሀኪም አገልግሎት/

Royal Flying Doctor Service of Australia

• በአየር መተላለፊያ ት/ቤት/School of the Air

• በረዷማ ተራሮች የሀይድሮ ኤሌትሪክ ባለሥልጣን/

Snowy Mountains Hydro-Electric Authority

www.bradman.com.au

www.fistulatrust.org

www.flyingdoctor.net

www.schoolair-p.schools.nsw.edu.au

www.snowyhydro.com.au

• የፍረድ ሆሎውስ እርዳታ ድርጅት/The Fred Hollows Foundation www.hollows.org.au

• የዓለም ቅርስ ማእከል/UNESCO World Heritage Centre

• የተባበሩት መንግሥታት/United Nations

• ቪክቶር ቻንግ ካርዲክ/Victor Chang Cardiac የምርምር ተቋም

• አውስትራሊያ በፈቃደኝነት/Volunteering Australia

whc.unesco.org

www.un.org

www.victorchang.edu.au

www.volunteeringaustralia.org

ሌሎች

ስለሚከተሉት አርእስቶች በበለጠ መረጃ ለማግኘት በሚከተሉት ላይ በድረገጽ ላይ መፈለግ:

• የአውስትራሊያ ህገ መንግሥት

• በአውስትራሊያ የዓመቱ ሽልማቶች

• ‘ወደ ቤት አምጧቸው/Bringing them home’ ሪፖርት

• በኮመንዌልዝ የመናፈሻና የተከለከሉ ቦታዎች

• ዝነኛ አውስትራሊያኖች: የአውስትራሊያ መዝገበ ቃላት

በሰው ህይወት ታሪክ ጽሁፍ በመስመር ላይ የተዘጋጀ ጽሁፍ

• ለፓርሊያመንት የቀረበ የወቅቱ ህግ ማሽሻያ ጥያቄ

• የአውስትራሊያ ፓርሊያመንት

• ፓርሊያመንታዊ የትምህርት አገልግሎት

• የህዝብ በዓታት

• ለተሰረቁ ትውልዶች ይቅርታ ጥያቄ

www.aph.gov.au/senate/general/

constitution

www.australianoftheyear.org.au

www.humanrights.gov.au/social_justice/

bth_report/index.html

www.environment.gov.au/parks/index.html

http://adbonline.anu.edu.au/adbonline.htm

www.aph.gov.au/bills/index.htm

www.aph.gov.au

www.peo.gov.au

www.australia.gov.au/topics/australianfacts-andfigures/public-holidays

www.abc.net.au/news/events/apology/

text.htm

ለበለጠ መረጃ 75
የቀረበ ምስጋና

የሚከተሉት ታሪካዊ ጽሁፎች ለአውስትራሊያ ብሄራዊ መዝገብ ቤት ይሆን ዘንድ ተሰጥተዋል:

p42 - በNSW ህጻናት በበግ ንብረት ላይ – በአየር መተላለፊያ ት/ቤት፣ ፎቶግራፍ የተወሰደው በ1962 ዓ.ም

(ለተጨማሪ መረጃ: A1200:L42511)

p51 - ታዋቂነት ያለው ሰው – Dick Smith, የሲቪ አቪየሽን ባለሥልጣን ሊቀ መንበር 1991 ዓ.ም (ref: A6135:K23/5/91/1)

p56 - በአውስትራሊያ የታዝማኒያ ማፕ ካርታ፣ 1644 ዓ.ም (ref: A1200:L13381)

p59 - በአውስትራሊያ የወርቅ ማውጣት ጥድፊያ በ1851 ዓ.ም ውስጥ (ref: A1200:L84868)

p60 - በአውስትራሊያ ምድር ውስጥ ‘የአፍጋንስ/Afghans’ እና ግመሎቻቸው መሥራት (ref: A6180:25/5/78/62)

p67 - ታዋቂነት ያለው ሰው - ሰር ኢድዋርድ/Sir Edward በቢሮ ሥራቸው ‘የደከሙ/Weary’ 1986 ዓ.ም ሰው ናቸው

(ref: A6180:1/9/86/12)

p67 - ኢሚግሬሽን – በአውስትልሊ ውስጥ የመጤ ማይግራንት መድረስ - ጣሊያኖች በኬርንስ/Cairns ውስጥ ባለች ፍላሚኒያ ላይ

ወረዱ 1955 ዓ.ም (ref: A12111:1/1955/4/97)

የአውስትራሊያ ብሄራዊ ቤተመጽሐፍ ክብርነት ከዚህ በሚከተሉት ተገልጸዋል:

p18 - በህዝብ መሰብሰቢያ ሲቪክ፣ ካንበራ/Canberra፣ በጋረማ ቦታ/Garema ላይ ስለ ፀር-ጦርነት ከተናጋሪዎች ሃሳብ ለመስማት

የክቲት/February 15 ቀን 2003 ዓ.ም በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ ፎቶግራፍ በግረግ ፖወር/Greg Power ተወስዷል

(ref: nla.pic-vn3063592)

p44 - የጁዲት ውሪይት/Judith Wright አገላለጽ፤ የታተመው በ1940 ዎቹ ዓመታት ውስጥ (ref: nla.pic-an29529596)

p52 - ከተፈጥሮ እልቂት/tsunami በኋል ታህሳስ/December 30 ቀን 2004 ዓ.ም በኢንዶነሺያ ውስጥ አሰህ/Aceh ላይ በአውስትራሊያ

መከላከያ ሀይል የተደረገውን የችግር ማስወገጃ እርዳታ የኢንዶኖሺያ ሴቶች ሲያሞግሱ ፎቶግራፍ በዳን ሁንት/Dan Hunt

ተቀርጿል (ref: nla.pic-vn3510861)

p56 - በሲድነይ ባህር ወሽመጥ የመጀመሪያው ጦር መርከብ፣ ጥር/January 27 ቀን 1788 ዓ.ም፣ በጆን አልኮት/John Allcot 1888

– 1973 በኩል የወጣ (ref: nla.pic-an7891482)

p57 - የካሮሊን ችስሆልም/Caroline Chisholm አገላለጽ፤ ህትመት በቶማስ ፊርላንድ/Thomas Fairland 1804 – 1852

(ref: nla.pic-an9193363)

p58 - የበርክ መመለስ/Return of Burke እና የኩፐርስ ክሪክ ምኞት/Wills to Coopers Creek፣ በኒኮላስ ቸቫሊር/Nicholas

Chevalier 1828 – 1902 የወጣና ህትመት በ 1868 ዓ.ም ተካሄደ (ref: nla.pic-an2265463)

p61 - የካተሪን ሀለን ስፐንስ/Catherine Helen Spence ክብርነት አገላለጽ፣ ህትመት በ 1890s ዓ.ም (ref: nla.pic-an14617296)

p63 - ጆን ሲምፕሶም ኪርክፓትሪክ/John Simpson Kirkpatrick እና የሳቸው አህያ፣ ጋሊፖሊ/Gallipoli, 1915 ዓ.ም

(ref: nla.pic-an24601465)

p65 - የሰር ቻርለስ ኢድዋርድ ኪንግስፎርድ ስሚዝ/Sir Charles Edward Kingsford Smith አገላለጽ፣ ህትመት በ1919 እና 1927

መካከል (ref: nla.pic-vn3302805)

p70 - በሀርማንስቡርግ ሚሽን/Hermannsburg Mission, ኖርዝ ተሪቶርይ/Northern Territory፤ የአርበርት ናማትጅራ/Albert Namatjira

አገላለጽ፣ ህትመት በ 1946 ወይም በ1947 በአርተር ግሩም/Arthur Groom ታትሞ የወጣ (ref: nla.pic-an23165034)

ለአካባቢ፣ ውሀ፣ ቅርስ መምሪያ ጽህፈት ቤትና ለስነ-ጥበባት እና ለሚከተሉት ሰዎች የሚያደንቅ በአስራ አራት የዓለም

ቅርስ ማሳያ ቦታዎች በኩል ይቀርብል:

p40 - የአውስትራሊያ ጡት አጥቢ ቅሬተ አካል ቦታዎች ፎቶግራፍ በኮሊን ቶተርደል/Colin Totterdell ተነስቷል

p40 - የሰማያዊ ተራሮች/Blue Mountains ብሄራዊ መናፈሻ ፓርክ ፎቶግራፍ በማርክ ሞሀል/Mark Mohell

p40 - ፍራሰር ደሴት/Fraser Island ፎቶግራፍ በሽኖን ሙር/Shannon Muir

p40 - በአውስትራሊያ የጎንድዋና የበርሀ ጫካ/Gondwana Rainforests ፎቶግራፍ በ Paul Candlin

p40 - ካካዱ/Kakadu ብሄራዊ ፓርክ ፎቶግራፍ በ Sally Greenaway

p40 - የ Lord Howe ደሴት ፎቶግራፍ በ Melinda Brouwer

76

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
p40 - የማኳሪ ደሴት/Macquarie Island በማሊንዳ ብሮወር/Melinda Brouwer

p41 - የፑርኑሉሉ/Purnululu ብሄራዊ ፓርክ ፎቶግራፍ በ Rod Hartvigsen

p41 - ይሮያል ኢግዚቪሽን ህንጻ እና የካልቶን አትክልት ቦታ ፎቶግራፍ በ Michelle McAulay

p41 - የሻርክ የባህር ወሽመጥ/Shark Bay ፎቶግራፍ በክካይ ምሙን/Kelly Mullen

p41 - በታዝማኒያ የአውሬ ልቅነት/Tasmanian Wilderness ፎቶግራፍ በኒኮል ብርይደን/Nicola Bryden

p41 - ዩሉሩ-ካታ ትጁታ/Uluru-Kata Tjuta ብሄራዊ ፓርክ ፎቶግራፍ በአንድሩ ሁትችንሶን/Andrew Hutchinson

p41 - በኩዊንስላንድ እርጥበት ያለው የሀሩር ቦታ/Wet Tropics of Queensland ፎቶግራፍ በኮሊን ቶተርደል/Colin Totterdell

p41 - የዊላንድራ ድሴት ክፍል/Willandra Lakes Region ፎቶግራፍ በ Mark Mohell

ከዚህ የሚከተሉት ስለ ስቶክ ፎቶ/iStockphoto የክብር አድናቆት ገጽታ ይቀርባል:

በፊተኛው ሽፋን ላይ - ዋትል/Wattle, ©iStockphoto.com/Ressy (ref: 3322510)

p14 - የአውስትራሊያ ጥቁር ኦፓል/Australian black opal, ©iStockphoto.com/Alicat (ref: 8323912)

p22 - የፓርላማ መቀመጫ/Parliament House, ©iStockphoto.com/Tim Starkey (ref: 2256743)

p22 - የዳኛ መዶሻና መጽሐፍ/Gavel and book, ©iStockphoto.com/Dem10 (ref: 2397687)

p27 - በፋይናንስ ግራፍ ላይ ሳንቲም/Coins on finance graph, ©iStockphoto.com/Robyn Mackenzie (ref: 2335549)

p27 - የዶክተር ጽህፈት/Doctor writing, ©iStockphoto.com/Carlos Arranz (ref: 6498434)

p38 - የቦንዲ ባህር ዳር/Bondi Beach, ©iStockphoto.com/Edd Westmacott (ref: 3048786)

p51 - በብረት ማእድን ማውጫ ላይ መብት ጠያቂ/Reclaimer on iron ore mine site, ©iStockphoto.com/Christian Uhrig

(ref: 9819736)

p54 - ዲገሪዱስ/Didgeridoos, ©iStockphoto.com/Adam Booth (ref: 834207)

p55 - የአቦርጅናል ድንጋይ ላይ ስነ-ጥበብ/Aboriginal rock art – ሳራቶጋ አሳ/Saratoga fish, ©iStockphoto.com/Alpen

Gluehen (ref: 2761924)

ከዚህ ለሚከተሉት ድርጅቶች/ሰዎች ያላቸውን የክብር አድናቆት በሌላ አገላለጽ ቀርቧል:

p8 - በባህር ዛፍ የተከበበ የቡሩዋንግ ዘንባባዎች/Spotted gums with a floor covering of Burrawang palms)፤ የሙራማራንግ/

Murramarang ብሄራዊ ፓርክ NSW ፎቶግራፍ በ Dario Postai

p20 - እያንዳንዱ ግለሰብ በድምጽ ካርድ ሳጥን ውስጥ ለሚመርጡት ድምጽ ማስገባቱ የሚያሳየው የቪክቶሪያ ምርጫ ኮሚሽንን ክብርነት

ይገልጻል

p24 - የኮመንዌልዝ አውስትራሊያ ህገ መንግሥት አንቀጽ ህግ/Act 1900 ዓ.ም: ከህዝብ መዝገብ ዋና ላይ ቅጂ፣ ስጦታን በማሰባሰብ

ክብርነትን መግለጽ፣ በፓርላማ መቀመጫ የስነ- ጥበባት ስብስብ፣ በፓሪያመንታሪ አገልግሎት መምሪያ ካንበራ/Canberra ACT

p27 - ህጻናት ተሰልፈው መቀመት የሚያሳየው የገትይ ገጽታ/Getty Images ክብር ታዋቂነት ሲሆን ፍቶግራፉ በመል ያትስ/Mel Yates

ይሆናል

p28 - የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚያሳየው የአውስትራሊያን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክብር ታዋቂነትን ይሆናል

p40 - የቢግ በን ሂርድ/Big Ben Heard ደሴት የሚያሳየው በኮመንዌልዝ አውስትራሊያ ውስጥ የአውስትራሊያን አንታርቲክ ክፍልን

አድናቆት ክብርነት ሲሆን ፎቶግራፍ በ L. E. Large (ref:1892A2)

p40 - ታላቁ ሀምራዊ የድንጋይ የባህር ጠረፍ/Great Barrier Reef የሚያሳየው በታላቁ ሀምራዊ የድንጋይ ጠረፍ ያለውን የማሪን

ፓርክ ባለሥልጣን Great Barrier Reef Marine Park Authority ክብርነት ይሆናል

p41 - የስይድነይ ኦፐራ ሃውስ/Sydney Opera House የሚያሳየው የስይደይ ከተማን አድናቆት ክብር ሲሆን ፎቶግራፍ በፓትሪክ

ቢንግሃም-ሃል/ Patrick Bingham-Hall ይሆናል

ምስጋና 77
የቀረበ ምስጋና

p43 - የአውስትራሊያ ስፖርት ኮሚሽንን ክብር ለማድነቅ ከአውስትራሊያ ብሄራዊ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን (Matildas) የቡድን አባል

ምሳሌነት

p44 - የብራድማን ክሪከት ሙዚየምን ለማድነቅ በ Sir Donald Bradman ገለጻ። ሰር ዶናልድ ብራድማን በአውስትራሊያ 1931-32

ዓ.ም ወቅት ለተደረገ ውድድር የሳቸውን ቡድን የሚያሳይ ለብሰው እንደነበር ነው

p45 - ስለ ፕሮፈሰር ፍረድ ሆሎውስ የክብር አድናቆት በፍረድ ሆሎውስ ፋውንዴሽን፣ በፍራንክ ቪዮሊ/Frank Violi በተድውረገ ፎቶግራፍ

ይታያል

p50 - የሲድነይ ከተማ አድናቆትን በቅድመ አዲስ ዓመት ምሽት በስድነይ ሃርቦር/Sydney Harbour ላይ በሚደረግ የእሳት ርችት ይገለጻል

p52 - የ Dr Catherine Hamlin AC ክብር ታዋቂነት በሃምሊን ፊስቱላ ሪሊፍ/Hamlin Fistula Relief እና በእርዳታ ገንዘብ/Aid

Fund ይገለጻል

p61 - ሎርድ ላሚንግቶን/Lord Lamington በፈደሬሽን ቀን ስለ መሰባሰብ በብሪስባን/Brisbane፣ በ1901 ዓ.ም ለህዝብ ንግግር

በማድረግ የክብር ታዋቂነታቸው በኩውንስላንድ መስተዳድር ግዛት ቤተ መጽሐፍ፣ በ H.W. Mobsby (ref: 47417) በተካሄደ

ፎቶግራፍ በኩል ይገለጻል

p65 - የማድቤት ሾርባ/ Soup kitchen ክብር ታዋቂነት በኒው ሳውዝ ዌልስ (ሚትቸል/Mitchell Library) የመስተዳደር ግዛት

ቤተመጽሐፍ በኩል ይገለጻል። በኒው ሳውዝ ዌልስ፤ በልሞረ ሰሜናዊ የህዝብ ትምህርት ቤት/ Belmore North Public School,

NSW፤ ነሐሴ/August 2 ቀን 1934 ዓ.ም የትምህርት ቤት ህጻናት በነጻ ሾርባና ቁራጭ ዳቦ ለማግኘት ሲሰለፉ በሳም ሁድ/Sam

Hood (ref: H&A 4368) በኩል ፎቶግራፍ ተቀርጿል።

p66 - የኮዳክ ትራክ/Kokoda Track ክብር ታዋቂነት በአውስትራሊያ ጦርነት መታሰቢያ ሀውልት ይገለጻል (ref: 014028)

p66 - በአውስትራሊያ ጦርነት መታሰቢያ ላይ በቀይ አበባ ማጌጥ ቀይሕ/Red poppies ፎቶግራፍ በቶሪ ብሪምስ/Torie Brims በኩል

ተካሂዷል

p70 - የዶ/ር ቪክቶር ቻንግ/Dr Victor Chang ክብር ታዋቂነት በVictor Chang Cardiac የምርምር ተቋም ይገለጻል

p70 - የኢዲ ማቦ/Eddie Mabo ሃሳብ የሚገለጸው ከበሪንታ/Bernita እና ጋይል ማቦ/Gail Mabo ፈቃድ ሲገኝ ነው

78

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን
ማስታወሻ
ማስታወሻ
ማስታወሻ