Awra Amba RJ 300612 EN - Contacter un comité local d'Attac
Awra Amba RJ 300612 EN - Contacter un comité local d'Attac
Awra Amba RJ 300612 EN - Contacter un comité local d'Attac
You also want an ePaper? Increase the reach of your titles
YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.
አጭር መግለጫ

የሥራው ክፍፍያ የሚደረገው በፆታ ሳይሆን በችሎታ ብቻ ነው። እስካሁን የተካሄደው ጥናት እንደሚያመለክተው ፥ ባልና ሚስት

በምርትም ሆነ በማንኛውም ሀላፊነት ላይ እኩል ናቸው።

ጋብቻ የሠርገኞቹ ጉዳይ ነው ። ቤተሰቦቻቸውን የሚመለከት ነገር ምንም የለም ። የተመዘገበው እስታቲስቲክስ ግልጽ አድርጎ የአውራ

አምባ ወጣቶች በልጅነት እድሜአቸው ለጋብቻ እንድማይዳረጉ ያሳያል ። ባብዛኛው ሴቶቹ ከ 19 እስከ 20 ዓመታቸው ሲያገቡ ፥

ወንድቹ ደግሞ ከ20 እስከ 25 ባለው እድሜአቸው ያገባሉ ። በክፍለ ሀገር የሚገኘው አርሶ አደር ህዝብ ግን ፥ ከ10 እስከ 14 ዓመት

ካላቸው ልጅች መሀል ከወንድቹ 5 % ፡ ከሴቶቹ 8 % የሚሆነው በጋብቻ ኑሮ ተረማርተው ይገኛሉ ። በወሊድም ቢሆን የአውራ አምባ

ቤተሰብ ውስጥ የልጅ ብዛት ከሌላው በቁጥር አንድ ይቀንሳል ። መፋታትም ቢኖር ፥ በስምምነት ከመካሄዱም በላይ ባልና ሚስት

ንብረታቸውን በእኩል ይካፈላሉ ።

መተባበርና መከባበርን ልጆች በተለይ እንዲገነዘቡት ግዴታቸው በሶስት ይከፈላል ፥ ይኸውም ትምህርት ቤት መሄድ ፡ መጫወትና

የኅብረት ሥራ ማህበሩን በሥራ ማገዝ ። ይሁን ብንጂ በቤት ሥራም ሆነ በእርሻ ሥራ ተሳትፎአቸው በጣም አነስተኛ ነው ። ሁሉም

ለረዥም ዓመታት ትምህርት ቤት ይሄዳሉ ፡ ከትምህርት ቤትም ውጪ ጥናታቸውን እንዲከታተሉ ይጋበዛሉ ። የኅብረ ሰቡ ትብብር በወሊድ

ላይ ያሉ ሴቶችንም ሆነ በሽተኞችንና አዛውንቶችን ይንከባከባል ።

የቀብር ሥነስርአትን በሚመለከትም ፡ የአውራ አምባ ኅብረ ሰብ እንደአማራው በለቅሶና ሀዘን ብዙ ሀይልና ጊዜ አያጠፋም ፥ የነወሰኑ

ሰውች ተመድበው በተወሰነ ጊዜ ሥርአቱን ያካሂዳሉ ። የአውራ አምባ ኅብረ ሰብ ባህል ፡ ከሞቱ በኃላ ህይወት አለ ብሎ ስለማያምን

የምድርን ኑሮ ያበልጣል ።

በባልና ሚስትም ሆነ በኅብረተሰቡ መሀል የሚከሰተውን ችግር ለማቃለል የተወከሉት የተለያዩ የፍርድ ኮሚቴዎች ስኬታማ ውጤት

ያስገኛሉ ።

በመቀጠል ፡ የአውራ አምባ ኅብረተ ሰብ ልዩ የሆነ አመለካከት የሚሰጠውን የትምህርት ስነ ሥርአት በዝርዝር እናብራሪለን ። ትምህርት

ኅብረተ ሰቡን ወደ ፊት ሰማስኬድ ብቻ ሳይሆን እያንዳዱን ግለሰብ ከፍ የሚያደርግ ነው ። በመጀመሪያ አውራ አምባ ራስን በራስ

ማስተማር የሚቻልበትን ሁናቴ ለአዋቂዎች ብቻ ሳይሆን በተለይ ትምህርት ላልጀመሩ ለታዳጊ ልጆችና ለሌሎቹም ከትምህርት ቤት ውጪ

አመቻችቶአል ። ይህ ትምህርት የሚካህደው በእድሜ ጠና ባሉ ወጣቶችና በሰፈሩ አዋቂዎች ሲህን ፥ የህፃናት መዋያና የተመላ

መጽሐፍት ቤትን ያካተተ ነው።

ለትምህርት የደረሱ ልጆች ሁሉ ይማራሉ ። ንቁና አጥኚ ከመሆናቸውም በላይ ፡ የስብሰባ መድረክ ላይ ሀሳባቸውን ለመስጠት አያፍሩም ፥

ነገር ግን ከሌላ መንደር ልጆትች ጋር እምብዛም አይገናኙም ። አስተማሪዎቹም የአውራ አምባ ተማሪዎች ከሌሎቹ በጣም የላቁ ተጣጣሪና

ተባባሪ መሆናቸውን ይመሰክሩላቸዋል ። በዚህም ምክንያት የንምህርት ደረጃቸው ከሌሎቹ በጣም ከፍ ያለ ከመሆኑም በላይ ፡ በሴቶችና

ወንዶች መሀልም ብዙ ልዩነት አይታይም ።

ከዚህ በመቀጠል የምናተኩረው የአውራ አምባ አባላት ከአካባቢአቸው ነዋሪዎች ጋር ያላቸውን ጥርጣሬ የተመላበት ግኑኝነት ላይ ይሆናል

። የአውራ አምባ ነዋሪ በአካባቢው ህዝብ አቅጣጫውን እንድሳተ ሚስጥረኛ ጨካኝ ሰነፍና ሀይማኖተ ቢስ ሆኖ ይታያል ፥ የአውራ አምባ

ኅብረሰብም ከጎረቤቶቹ ጋር ቅርበት የለውም። ይህ ጥርጣሬ የተከሰተው በሁለቱ መሀል ከፍተኛ የባህል ልዩነት በመኖሩና ፡ ቀደም ሲል

መፍትሄ ያላገኘው አሰከፊ ያለመግባባት ነው ። በዛሬው ወቅት ችግሩ ቀዝቀዝ ያለ ይመስላል ። በሌላ በኩል ደግሞ አውራ አምባ ከክፍለ

ሀገሩና ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ያለው ግንኙነት በጣም የላቀ ነው ። አውራ አምባ ብዙ እንግዶችን ያስተናግዳል ፥ በብዙ ቦታም

እንደ ምሳሌ ይጠራል ።

በመደምደሚያ ማሳየት የምንሞክረው ፡ በአለም ላይ የሕልም እንጀራ መስሎ የሚታየው የሰዎች በእኩልነትና በክብር ተዋዶ የመኖርን

ስሜት በመከተል ፡ ይህ አመለካከት የሰው ልጅ ለነፃነቱ ለሚያደርገው ትግል አስተዋጽዎ እንዳለው ነው ። እየተገነቡ ያሉ ፡ ኃላ ቀር

የሚባሉት ሀገሮች ላይ ለሚደረገው ግንባታ ጭማሪ ያመጣል ። ሰለሆነም አውራ አምባ በብዙ መልኩ ፡ ለአካባቢውም ሆነ ለኢትዮጵያ፡

ከዚያም አልፎ ለአውሮፓና ለመላው ዓለም ለሚደረገው የነጻነት እንቅስቃሴ ምሳሌ ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል ። ይሁን እንጂ ፡ ይህ አስደናቂ

ኅብረተሰብ ዘለቄታማ ለመሆን ብዙ ችግሮችን መወጣት ይኖርበት ይሆናል። በተለይም ከኅብረተሰቡ ውጪ ጋብቻ ስለማይፈጸምና

ከክስሳቸው ውጪ ካለው ብኄረሰብ ጋር ግንኙነት ስለሌላቸው ። በመጨረሻ ይህንን የኑሮ ስልት የበለጠ ለመረዳትና ብሎም ለማስፋፋት

ይረዳ ዘንድ አንዳንድ ለጥናት የሚሆኑ ነጥቦችን ለማሳየት እንሞክራለን ።

የዚህ ዘገባ ዋና ኅትመት በፈረንሳይኛ ነው ።

9 / 85