07.11.2014 Views

Awra Amba RJ 300612 EN - Contacter un comité local d'Attac

Awra Amba RJ 300612 EN - Contacter un comité local d'Attac

Awra Amba RJ 300612 EN - Contacter un comité local d'Attac

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

Awra Amba, a current experiment of utopian socialism

መግለጫ

አውራ አምባ፡ ወቅታዊው ኅብረተ ሰብአዊ አንዋንዋር፡፡

በበኅብረትና በእኩልነት ለመኖር ሲደረጉ ከቆዩት ሙከራዎች ሁሉ፡ ኢትዮጽያ የሚገኘው አውራ አምባ ተብሎ የሚሰየመውና በአማራው

ክፍለ ሀገር ውስጥ የሚገኘው ህብረተ ሰብ በእኩልነትና በኅብረተሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ ነው ።

ይህ ጽሁፍ፡ ስለ ኅብር ሰቡ የተጻፉትን ልዩ ልዩ ጥናቶችን ፡ ማለትም አራት የማስተሬት የምርምርም ዘገባዎችን (አጥናፉ 2005 ፥ ይርጋ

2007 ፥ ያሲን 2008 ፥ መኮንን 2009) ያቀነባበረ ሲሆን ፥ በተጨማሪም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የጋዜጣ ዘገባዎችንና

ምስክሮችን ያካትታል ። በመጀመሪያ የራሳችንን አቀራረብና አመለካከት ፡ ማለትም የተመሮከዝንባቸውን የተለያዩ ምንጮችን የግል

አስተያየትና ትችታችንን እያከልን እናቀርባለን ፥ አዚያም ከተለያየ አቅጣጫ የሰበሰብናቸውና የንደዚህ አይነቱን የአንዋንዋር ዘዴ

በትክክል እንድናቀርብ ያገዙንን መረጃዎች እነዘረዝራለን ። ይህም ሲሆን አመቺ በሆነ ጊዜ ሁሉ አካባቢው ካለው የአማራ ኅብረተሰብ ጋር

ለማስተያየት እንሞክራለን ።

ኅብር ሰቡ የተጠነሰሰው በዙማ ኑሩ በ1972 ዓ/ም ነው። ገና በጨግላነቱ፡ ይህ ደሀ የባላገር ልጅ አርቆ አሰተዋይ በመሆኑ ፥ አካባቢውም

ሆነ እቤተሰቡ ውስጥ የተመለከታቸው ጎጂና ከሀቅ የራቁ ድርጊቶችን በመቃወም ለእኩልነት ይታገል ጀመረ ። በክፍለ ሀገሩም እየዞረ

ሀሳቡን የሚደግፉ ሰዎችን መፈለግ ጀመረ ። በመጨረሻም፡ ወደ ሃያ የሚጠጉ ሰዎችን ሰብስቦ ፥ የአውራ አምባ ህብረ ሰብን በህምሳ

ኤክታር ላይ ያቅዋቁማሉ ። ይሁን ብንጂ፥ ከአካባቢው ነዋሪዎች ከፍ ያለ ቅዋሜ ይደርስባቸዋል ። ምክንያቱም የአውራ አምባ ህብረ ሰብ

ከሀይማኖት ነፃ ከመሆኑም በላይ ፥ የሴትና ወንድ እኩልነትንም ሆነ የልጆችን መብት የሚያስከብር በመሆኑ ። ከዚያም በኢተዮጰያ ውስጥ

የተከሰተው ለውጥ ህብረ ሰቡን ከመበታተኑም በላይ ፥ ዋና መሪውን እስር ቤት በማስገባትና ለብዙ ዓመታት ርቀው በስደተኝነት እንዲኖሩ

ያስገድዳቸዋል ። በ1993 ዓ/ም ህብረ ሰቡ ተመልሶ አሁን የሚገኝበት ቦታ ላይ ከንደገና ይደራጃል ።

በተለያዩ ደራሲያን የመዘገቡትን ቁጥር ስንመለከት የአውራ አምባ ህብረ ሰብ ሲጀመርና በስደት ጊዜ ከሃያ በታች የነበረው በአሁኑ ወቅት

ከአራት መቶ በላይ መሆኑን ያስገነዝባል ። አቀነባበራቸውን በፆታና በእድሜ አካባቢው ከሚገኘው ከደቡብ ጎንደር ህዝብ ጋር

እናስተያያለን ። ከዚያም በኢትዮጵያ ውስጥ የአውራ አምባ ኅብረ ሰብ ምን አይነት ቦታ እንደያዘ እናሳይና ፥ በቦት አቀማመጥ በህዝብ

ቁጥርና በኢኮኖሚ ረገድ ያለውን ልዩነት እናመለክታለን ።

የአውራ አምባ በባህልና በአስተሳሰብ አንድነት የሰፈነበት መንደር ሲሆን ፥ አካባቢው ከሚገኘው የአማራ ብኄረ ሰብ በጣም የተለየ ነው ።

በመጀመሪያ ኅብረ ሰቡ ብዙ ዕሴቶች አሉት ፥ በአውራ አምባ መኖር ማለት ዕሴቶቹን ማክበርና ማስከበር ነው ። የተለያዩ ደራሲያን

የጠቀሱአቸው ዕሴቶች በርካታ ቢሆኑም ፡ ዋንኞቹን በተደጋጋሚ የሚጠቀሱት ሀቀኛነት፡ እኩልነት በተለይም የሴትና ወንድ እኩልነት፡

ኅብረተሰብአዊነት፡ ሥራና የሀይማኖት አለመኖር ናቸው ። ይህንኑ የአውራ አምባ ኅብረተሰብ እንዴት እንደሚያከብርና እንደሚያስከብር

በቅድመ ተከተል ደራሲያን የመዘገቡት ጽሁፍ ላይ በመመርኮዝ እናብራራለን ።

በመቀጠልም የኅብረ ሰቡን የረቀቀ አቀነባበር እናሳያለን ። በቅድሚያ የኅብረ ሰቡን ግንባታና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንመዘግብና ከዚያ

የኅብረ ሰቡን የአንዋንዋር ስልት በሚመለከት የሚከተሉትን እንዘረዝራለን ፡፡ ይኸውም በሥራ መስክ ላይ ያለውን የሴቶችና ወንዶችን

እኩልነት ፥ ጋብቻና ፍችን በሚመለከት ፥ ለልጆች የሚሰጠው የተወሰነና ልዩ ቦታ ፥ ከአቅም ደካሞች ጋር ያለው ትብብር ፥ የቀብር

ሥርአትና በመጨረሻም በኅብረ ሰቡ ውስጥ የሚከሰተውን ችግር አፈታት ይሆናል።

የአውራ አምባን አደረጃጀት በሚመለከት፥ ኅብረ ሰቡ በሁለት ይዋቀራል ። አንደኛው አጠቃላዩ ተከባብሮና ተደጋግፎ የሚኖረው ኅብረ

ሰብ ሲሆን ፥ ሁለተኛው በሥራ መስክ ተሳትፎ የሚያደርገው የኅብረ ሰቡ ሦስት አራተኝ ነዋሪ ይሆናል ። የኅብረ ሥራ ማህበሩ ዋና ዋና

ውሳኔዎች በአጠቃላይ ጉባዔው ይወሰናሉ ። ይህ ጉባዔ የሚመርጣቸው ኮሚቴዎች በየመስካቸው የተለያየውን ሥራ ጉባዔው በወሰነው

መሰረት በህብረት ያካሂዳሉም ይቆጣጠራሉም ። 44 % የኮሚቴው አባላት ሴቶች ናቸው ፡ አሰፈላጊ በሆነ ጊዜም ይቫራሉ ።

የአውራ አምባ ማህበር ኤኮኖሚ በከፊል ግብርና ነው ። ይሁን እንጂ ያላቸው የእርሻ መሬት ከአካባቢው መሬት ጋር ሲነጻጸር በጣም

አነስተኛ ነው ፡ ከተለያዩ ጽሁፎች እንደምንረዳው ፡ የአውራ አምባ ነዋሪዎች በቤተሰብ ከ0,2 እስክ 0,4 ሄክታር ሲኖራቸው ፥ የአካባቢው

በቤተሰብ 2,1 ሄክታር ይኖረዋል ። ዋናው የእርሻ ምርት ጤፍ ቦቆሎ ማሽላና ቦሎቄ ሲሆን በተጨማሪም አነስተኛ የከብት እርባታም

ይገኝበታል ። ውጤታቸው ከአካባቢው በአንድ አራተኛ ከፍ ይላል ። ይሁን እንጂ ምርታቸው ለፍጆታቸው ሰለማይበቃ ወደ ተለያዩ እንድ

ሸማኔ የወፍጮና ንግድ መስክ ተሰማርተዋል ። ባብዛኛው ሥራው የሚካሆደው በኅብር ሥራ ማህበሩ ውስጥ ነው ፥ ነገር ግን ዋናውን

የሽመና ሥራ እያንዳንዱ በቤቱ ስለሚሠራ የግል ሥራ ሆኖ ይገኛል ።

እኒህ የተለያዩ የገቢ ምንጮች ለኅብረ ሰቡ ካካባቢው የተሻለ ገቢ የሚያስገኝ ቢመስልም ፥ የተመዘገበው ቁጥር አስተማማኝ ካለመሆኑም

በላይ አንዳንድ ቦታ ላይ ተቃራኒ ሆኖ ይታያል ። ሆኖም የነዋሪው የእለት ምግብ አመቱን ሙሉ የተማላ ይመስላል ። አካባቢው ያለው

አማራው አርሶ አደር ግን የሚሸፍነው ባመት የዘጠኝ ወር ቀለቡን ብቻ ነው ።

ከዚህ በመቀጠል እያንዳንዱ የኅብረ ሰብ አባል በተለያየው የሥራ መድረክ ላይ የሚያደርገውን አስተዋጽዎ እናብራራለን ። ባብዛኛው

8 /85

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!